Monday, April 8, 2013

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ ተቋረጠበት


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ ተቋረጠበት


3 ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ” ከእንግዲህከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለንአለ
እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ልእልና ጋዜጣበመንግስት ጫና እንዳድታተም ከታገደች በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ”የንግድ ሚኒስቴር በልእልና ጋዜጣ የቀድሞ ባለቤትና በአዲሱ ባለቤትመካከል ህገወጥ የሆነ የስም ዝውውር ተደርጓል በማለት የንግድ ፈቃዱ  ”እንዲሰረዝ መደረጉን ተነግሯል።
ፍትህ ጋዜጣ በህገወጥ መንገድ እንዳይታተም ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛውአዲስ ታይምስ መጽሄትን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ለተወሰኑ ሳምንታትሲያሳትም ቆይቷል።
መጽሄቷ በተመሳሳይ መንገድ እንድትዘጋ ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛተመስገን እንደገና ልእልና ጋዜጣን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ስራውንለመስራት ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጅ 100  ብር በላይ በሆነ ወጪየገዛው ጋዜጣ  ከመንግስት በተላለፈው ጫና እንዳይታተም በድጋሜታግዶበታል
ተመስገን በራሱ ስም ፈቃድ አውጥቶ መስራት ከተከለከለ፣ ከእንግዲህ ወዲያስለሚኖረው አማራጭ ሲጠየቅ፣ “ያለኝ አማራጭ ከሲቪክ ተቋማት ጋርበመተባበር  ከጫካ ትግል በመለስ ያሉትን የሰላማዋ ትግል አማራጮችበመጠቀም  አስገዳጅ ሁኔታ በመፍጠር መብታችንን እናስከብራለንብሎአል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ሰሞኑን በገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ከፍተኛ ወከባሲደርስበት እንደነበር  ይታወሳል።  ተመስገን፣ 106 ያላነሱ ክሶችምእንዳሉበት ይታወቃል።

Sunday, April 7, 2013

Ginbot7 Press release- በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ

SEATTLE - Human rights activist Tamagne Beyene wrapped up his global fundraising tour for ESAT, and shared his memorable encounters with Ethiopians in several countries. Tamagne said Ethiopians from South Africa to Australia, New Zealand to across Europe showered him with outpouring love and support as he raised a record sum of money for the up-and-coming Ethiopian Satellite TV - ESAT.

Tamagne Beyene: Report on Worldwide Tour for ESAT 
Ethiomedia; April 6, 2013

የሲፒጄውን ተሸላሚ” ዳዊት ከበደን መጨረሻ ማየት ናፈቀኝ


የሲፒጄውን ተሸላሚ” ዳዊት ከበደን መጨረሻ ማየት ናፈቀኝ


የሲፒጄውን ተሸላሚ” ዳዊት ከበደን መጨረሻ ማየት ናፈቀኝ

ክፈሌ ስንሻው አኔሳ
ዳዊት ከበደ ያለተቀናቃኝ አውራምባ ታይምስ የተባለ ጋዜጣን ሲያስትም ቆየ። እንደ ዳዊት ለ2 አመታት ታስረው የተፈቱት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና እስክንድር ነጋ የጋዜጣ
Journalist Dawit Kebede, Awramba Times editor
ከፌስ-ቡክ የተገኘ
ህትመት ፈቃድ ተከልክለው ለእሱ  ተፈቀደ። ለምን ለእሱ ተፈቀደ ብሎ የጠየቀ አልነበረም፤ በእስር ቤት ተፈትኖ የወጣ በመሆኑ ለወያኔ ያድራል ብሎ የሚጠረጥር  ሰው አልነበረምና። ዳዊት  አውራምባን ማሳተም ቀጠለ። ጋዜጣው ጥሩ ስራ እየሰራ ባለበት ጊዜ ዋና አዘጋጁ “ልጁን አላምነውም ብሎ” ጥሎት ጠፋ። ዋና አዘጋጁ በወቅቱ ይናገር የነበረውን ማንም አላመነውም ነበር፤ ቀጥሎም ተረበኛው አቤ ቶክቾው ድርጅቱን ለቀቀ።
አውራምባም፣  ሄደች ሄደችና  ገበያዋ ሲደራ፣ መሀል መንገድ  ቀረች ቆማ ተገትራ ተባለች፤ “ጠንካራ ዘገባዎችን” ማውጣት አቆመች፣ ዜናዎቿ ሁሉ ” ጁነዲን ምሳ በላ፣ አባዱላ ውቅሮን ጎበኘ” ወዘተ ሆነ ። “ዳዊት ከበደ መፍራት ጀምሯል” ተብሎ በአዲስ አበባ መወራት ጀመረ፤ በመሀሉ ሲፒጄ የሚባል ድርጅት የአመቱ ምርጥ ሰው አድርጎ ሸለመው፤ የዳዊትም ስም እንደገና  ከፍ ከፍ አለ። ሁላችንም ዳዊት በመሸለሙ (የመጀመሪያው የሲፒጄ ኢትዮጵያዊ ተሸላሚ በመሆኑም) ደስ አለን፤ እኔ በግሌ በጣም ተደሰትኩ። ዳዊት ግን አንድ ፈተና

መኢአድ ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ጉዳይ ለአለም ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ነው *ሁለት ነፍስጡር ተፈናቃዮች መኪና ላይ ወልደዋል


መኢአድ ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ጉዳይ ለአለም ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ነው *ሁለት ነፍስጡር ተፈናቃዮች መኪና ላይ ወልደዋል

በመስከረም አያሌው 

በቤኒሻንጉል ክልል የሚኖሩ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ያፈናቀለውን አካል ጉዳይ ለአለም ፍርድ ቤት ለማቅረብ ማቀዱን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቀ። 
የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ወንድማገኘኝ ደነቀ እንደገለፁት በቤኒሻንጉል ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆናቸው ብቻ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመባቸው በመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ክስ ለመመስረት ታስቧል። ባለፈው ሳምንት ከቤኒሻንጉል ቡለን ወረዳ ብቻ 5ሺ 530 የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ ባህርዳር፣ ጐንደር፣ ደጀን እና ቻግኒ እንደተሰደዱ የገለፁት አቶ ወንድማገኝ፤ ከትናንት በስትያም ከከማሼ ዞን ያርሶ ወረዳ 2ሺ 500 ተጨማሪ ሰዎች ተሰደው ፍኖተሰላም ሰፍረዋል ብለዋል። እነዚህ የአማርኛ ቋንቋ በመናገራቸው ብቻ ከ30 አመት በላይ ከኖሩበት አካባቢያቸው እንዲሰደዱ የተደረጉ ሰዎችም ከሆቴል ባለቤት እስከ የቀን ሰራተኛ የሚደርሱ መሆናቸው ተገልጿል። በተለይ በከማሼ ዞን እነዚህ ሰዎች የኖሩበት ነባር አካባቢያቸው መሆኑን እና አንዳንዶቹም አማራ ብቻ ሳይሆኑ ቅልቅል መሆናቸው ተገልጿል። 
በተለይ ከትናንት በስትያ ወደ ፍኖተ ሰላም እንዲሰደዱ ከተደረጉት ሰዎች መካከል ሁለት ነፍሰጡሮች መኪና ላይ መውለዳቸውንም አቶ ወንድማገኝ ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች ኃላፊነት በጐደለው ሁኔታ በአንድ መኪና እየታጨቁ እና እየተደበደቡ ወደነዚህ አካባቢዎች በመጓዝ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ለረጅም አመት የኖሩበትን ቀዬ እና ሀብት ንብረት ትተው ወደ ሌላ አካባቢ እንዲሰደዱ የተደረጉት እነዚህ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ ከመሆናቸውም በላይ ህፃናት እና ታዳጊዎች ለጐዳና ህይወት እየተዳረጉ መሆናቸው ተገልጿል። 

በየጊዜው በዜጐች ላይ እየተከሰተ ያለውን ከቀዬ የማፈናቀል ሂደት ለማስቆም የፓርቲው አመራሮች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። የውይይቱ ዋና አላማ እነዚህ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጐች አስቸኳይ እርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነበር። ለተፈናቃዮቹ ከተለያዩ አካላት ገንዘብ የማሰባሰብ እና የተሰበሰበውን ገንዘብም በአግባቡ አገልግሎት ላይ ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪም በእነዚህ ሰዎች ላይ በቋንቋቸው ምክንያት ብቻ እየተወሰደባቸው ያለው እርምጃ የዘር ማጥፋት እርምጃ በመሆኑ በአለም አቀፍ ህግ ለመጠየቅ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። 

የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ፣ በሚል ርእስ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫው ላይ እንዳሰፈረው ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ መጀመሩን አውስቱአል፣ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በዚሁ መግለጫ ማጠቃለያው ላይ በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በማነጣጠር እየተፈጸመ ያለው የማፈናቀልና የማጥቃት እርምጃ በአገሪቱም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ሁሉ በዘረኝነት ወንጀል የሚያስጠይቅ ከፍተኛ በደል ነው ብሎአል።


የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ


የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ፣ በሚል ርእስ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫው ላይ እንዳሰፈረው ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ  በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ መጀመሩን አውስቱአል፣  የግንቦት ሰባት ንቅናቄ    በዚሁ መግለጫ ማጠቃለያው ላይ በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በማነጣጠር እየተፈጸመ ያለው የማፈናቀልና  የማጥቃት እርምጃ በአገሪቱም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ሁሉ  በዘረኝነት ወንጀል የሚያስጠይቅ ከፍተኛ  በደል ነው ብሎአል።
የፕሮግራማችን ተከታታዮች የዚህን መግለጫ ሙሉ ቃል ከዜናው በማስከተል የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ይህ በንዲህ እንዳለ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች፣ ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ባደሩ ሆድ አደር ባለስልጣናት አሁንም ግፍና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አመለከተ። የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከባህር ዳር ባስተላለፈልን በዚሁ ሪፖርት ላይ እንዳመለከተው እነኝህ ተፈናቃዮች እያቀረቡ ላለው ጥያቄ  የክልል ባለስልጣናት ተብየዎች ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጡአቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውንና ከዚህም አልፎ ከህዝብ እይታ ለመሰወር በሚል ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን  ገለጹአል።

ዘጋቢያችን እንደገለጠው እነኝኝህ በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከመሀል ከተማ እንዲወጡ ተደርገው፣ ጃቢ ጣህናን ወረዳ ውስጥ ባከል እየባለች በምትጠራ ገጠራማ ቀበሌ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መገደዳቸውን ገልጹአል።
ህጻናት፣ እርጉዝ ሴቶች እና በሽተኞች ሳይቀሩ ቀን በጸሀይ፣  ሌሊት በብርድ እያንዳንዷን ቀን እንዲያስልፉ መገደዳቸውን የገለጠው ዘእጋቢያችን በመጀመሪያው ዙር ተፈናቅለው በባህርዳር ከተማ ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል አንድ አርሶአደር የክልሉ ባለስልጣናት ጉዳዩ የክልል ስድስት ጉዳይ በመሆኑ ክልል ሶስት አያገባውም የሚል ምላሽ የሰጡአቸው መሆኑ ታውቁአል።



መግለጫ
በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ  ያለው ግፍ አካል ነዉ!
የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው  ጥላቻና የበቀል ስሜት  እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ  መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ከወጣትነት ግዜያቸዉ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ጥርሳቸዉን የነከሱ የወያኔ  መስራቾች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለቻዉ ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም።

ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ


ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!!
ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ 
በተደጋጋሚ ፓርቲያችን እንደሚገልፀው አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምና የስርዓቱ አራማጆች ካላቸው የስልጣን እድሜን የማራዘም ጉጉት ተደማምረው ለሃገራችን እንዲሁም ተቻችሎ፣ ተዋልዶ፣ ተዛምዶና ተዋድዶ ለዘመናት ይኖር ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅና አስፈሪ አደጋ ወደ መሆን እንደደረሱ በግላጭ እየታየ ነው፡፡
ያ ለዘመናት አብሮን የቆየው በጋራ የመኖር ዕሴት እየተደመሰሰ በምትኩ የሚያጋጩ ስልቶች እየተፈጠሩና እየተተገበሩ ወደ ሰቆቃ ተለውጠው ይገኛሉ፡፡ የዜጎች ሰዋዊና ህጋዊ መብት እየተጣሰም ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ውስጥ አብሮ የመኖር፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና በፈለጉት ቦታ ሃብት የማፍራት ህልውና እያከተመ መጥቷል፡፡ ለዚህ ክፉ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆነው ደግሞ የዜጎችን መዘዋወር መብትና ሃብት የማፍራት መብት ማረጋገጥ የተሳነው መንግስትና መንግስት ብቻ ነው፡፡

የከዚህ በፊቱን የማፈናቀል ግፍ ትተን በቅርቡ እንኳ በጉረፈርዳና በሌሎች አካባቢዎች በቀጥታ በክልሉ ባለስልጣናት በተፃፈ ደብዳቤ ይሄ ሀገራችሁ አይደለም ተብለው፣ ሃብትና ንብረታቸው ተዘርፎ፣ የወለዱ አራሶች እንኳን የማገገሚያ ጊዜ ሳይሰጣቸው ደማቸውን እያዘሩ ሲባረሩ ከመንግስት የተሰጠው ምላሽ ‹‹ሞፈር ዘመቶች ናቸው (ማረሻውን ብቻ ተሸክሞ ወደ ሌላ ሀገር የሚሰደድ ለማለት ይመስለናል)›› የሚል ነበር፡፡ ይሄም ቢሆን የማንኛውም ዜጋ መብት ነው፡፡ መንግስት እነዚህ ዜጎች ‹‹ሃገራችን የት ነው?›› በማለት ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ የለውም፡፡
ገዥው ፓርቲ ሃላፊነትን መዘንጋትንና ስህተትን በማረም ፈንታ አፋፍሞ በመቀጠል ዜጎች ሃብትና ንብረታቸው እየተዘረፈ መባረራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይህም በጋምቤላና ቤኒሻንጉል በከፋ መልኩ ቀጥሏል፡፡ በተለይ ከቤኒሻንጉል ክልል የአማራ ተወላጅ የሆኑትን ዜጎች የዘመናችን ሹመኞች ከኢ-ሰብዓዊነት ባፈነገጠ መልኩ ከእቃ ለሚሰጥ ክብር ባነሰ ሁኔታ ንብረታቸውን ሳይሰበስቡ በጅምላ እየተጫኑ መጣላቸውን ቀጥለዋል፡፡ በርካታ ህፃናትም የዚህ ግፍ ሰለባ ሆነዋል፤ እየታፈኑ የሚሞቱትም ቁጥራቸው በርካታ ነው፤ በጣም የሚያሳቅቀው ደግሞ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት 59 ሰዎች ሞት ጉዳይ ነው፡፡ ካላግባብ በጭካኔ  ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት፣ ከወለዱበትና ከከበዱበት ስፍራ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በአንድ መኪና እየታጨቁ እንዲወጡ በማድረግ ገደል ውስጥ ገብተው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው ዜጎችን ህይወት እንዲቀጠፍ ያደረገውም በቸልታ እየገዛ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ነው፡፡ መንግስት በነዚህ ዜጎች ላይ ለደረሰው ኢ- ሰብዓዊ ድርጊትና ህይወት ማጣት ተጠያቂ ነው በማለት ፓርቲያችን ያምናል፡፡