Tuesday, April 9, 2013

Civil resistance – an effective strategy to remove the Woyanne junta in Ethiopia


Civil resistance – an effective strategy to remove the Woyanne junta in Ethiopia

Elias Kifle | April 9th, 2013
The fastest way to remove the brutal tribal junta in Ethiopia is through civil resistance. Civil resistance is an internationally accepted form of struggle against dictatorship. Therefore, Woyanne cannot define it as terrorism.
Key definitions:
Non-violent Sabotage: It is a disruption of the functioning of government and make “a country ungovernable.” Sabotage is anything that makes the country ungovernable by “removing the authority of the ruler.”
High-value Target (HVT): It is social, political or economic target the dictatorship requires for the successful accomplishment of its repression. The highly publicized loss or black-out of high-value targets can seriously degrade, destabilize and disintegrate his pillars of support.
Ethiopians can organize themselves locally and carry out an effective civil resistance campaign by sabotaging the Woyanne junta’s pillars of power, such as blockading roads, disabling communication lines, and sabotaging Woyanne-owned business enterprises.
Who will replace the Woyanne junta when it falls down because of civil resistance? The answer is: Transitional Government. It is imperative for patriotic Ethiopians to come together and start the process of creating a transitional government.

ESAT Daily News Amsterdam April 09 2013 Ethiopia

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ


የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ


ናፍቆት ዮሴፍ (ከፍኖተ ሰላም)
“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት ቤንሻንጉል ክልል ያቀናሉ፡፡ ኑሮአቸውንም በቤኒሻንጉል ክልል ካደረጉ በኋላ ተጨማሪ አራት ልጆችን አፍርተው የቤተሠባቸውን ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት ቀን ከሌት እየሠሩም ኑሮአቸውን መምራት ይቀጥላሉ፡፡ ለዓመታት ከኖሩበት መንደር በድንገት እንዲለቁ ሲገደዱ ግራ የተጋቡት አዛውንት የስምንት ልጆች አባት በመኾናቸው ሲፈናቀሉ ከፍተኛ ውጣ ውስጥ ከተታቸው፡፡
በቀላሉ የሚሳካላቸው አልኾነም፡፡ ‹‹ ከያሶ ወረዳ ውጡ ተብለን ድብደባና እንግልት ሲደርስብን እንደ ሌሎቹ እመር ብዬ መሸሽ አልኾን አለኝ፡፡ ልጆቼንና ባለቤቴን እንዴት ላድርጋቸው? ከአንድ ቤት ዘጠኝ ሰው የትስ ነው መውደቂያችን? ስል ጭንቀት ገባኝ›› የአዛውንቱ ዐይኖች እንባ አቀረሩ፡፡ አሁን አዛውንቱ ብዙ ስቃይ አልፈው በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ከሌሎች 3500 ተፈናቃዮች ጋር ከእነ ቤተሠባቸው በችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ ባለማግኘታቸው የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ኑሮአቸውን ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያዛወሩ የአማራ ተወላጆች ካለፉት ሦስት ሣምንታት ጀምሮ በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ከቀያቸው ተፈናቅለው በምስራቅ ጎጃም በጀቢጠናን ወረዳ ፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኝ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ወደዚያው አመራን፡፡
ከመጠለያው ወዲህ ከንፈሯ ክው ብሎ ደርቋል በጥቁር መናኛ ሻሽ እራሷን ጠፍንጋ አስራዋለች፡፡ የለበሠችው ቀሚስ ዳር ዳሩ ተተልትሏል፣ የተጫማችው ላስቲክ ጫማ ብዙ ቦታ ተበሣስቷል፡፡ በጠይም መልኳ ላይ ድካምና ተስፋ መቁረጥ ይነበብባታል- በፍኖተ ሰላም ከዳሞት ሆቴል ጀርባ ከአውቶብስ መናህሪያ ዝቅ ብሎ ባለው ‹‹ፍቶተ ሠላም›› ክሊኒክ መግቢያ በር ላይ ያገኘኋት የ27 ዓመቷ ወጣት የአራት ወር ነፍሰ ጡር ናት፡፡ በጉዞዋ በደረሰባት እንግልት በመታመሟ ከመጠለያው ለህክምና ወደ ክሊኒኩ እንደመጣች ነገረችኝ፡፡ “ራሴን ያዞረኛል፣ ሰውነቴን በጠቅላላ ይቆረጥመኛል፣ ያስለኛል፣ በተለይ ሌሊት ሌሊት እንቅልፍ የለኝም” የምትለው ነፍሠ ጡሯ፤ ባደረገችው ምርመራ ደም ማነስ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳጋጠማት ተነግሯታል፡፡

ባለቤቷም የታዘዘላትን መድሀኒት ሊገዛ ሄዷል፡፡ “ቀን ፀሀዩ፤ ማታ ብርዱ በዚያ ላይ ያለ ምንጣፍ ጠጠር ላይ እየተኛሁ ነው ለበሽታ የተጋለጥኩት፡፡ ከዚህ ቦታስ በሕይወት የምገኝ አይመስለኝም” አለች፡፡ ባለቤቷ ተመልሶ ሲመጣ ጨዋታው አላማረውም፡፡ ማንነቴን ጠይቆኝ ከተረዳ በኋላ፤ “እዚህ ያሉ የከተማው አስተዳደሮችና የክልሉ ኃላፊዎች አሁን ያለው ችግር እስኪፈታ ለማንም አትናገሩ ብለውናል” አለኝ፡፡ ‹‹አንዳንድ ጋዜጦች ከመካከላችሁ ያልሆነ መረጃ እየወሠዱና እየጻፉ ጋዜጣ ማሻሻጫ አድርገዋችኋል፤ ስለዚህ ዝም በሉ ተብለናል” የሚል ምላሽ ሠጠኝ፡፡ ችግሩን እንዲነግረኝ ለማግባባት ሞከርኩ፤ “ዋ! ለሠው ቢያወሩት መፍትሄ ካልመጣ ምን መላ አለው እህቴ?” በማለት መልሶ ጠየቀኝ፡፡ በእግራችን እየተጓዝን መጠለያው አካባቢ ደርሰን ነበርና ባለቤቱን ወደመጠለያው አስገብቶ አቧራማው ሜዳ ላይ ተቀምጠን ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታ ገባን፡፡

Monday, April 8, 2013

ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ድርጅት ሲፒጄይ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆነውና በተለያዩ ምክንያቶች ለታሰሩ ግለሰቦኖች የሚሟገተው ድርጅት «ፍሪደም ናው» ዛሬ ባወጡት መግለጫ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ አሰምተዋል።

                 

                              ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲለቀቅ መጠየቁ


ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ድርጅት ሲፒጄይ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆነውና በተለያዩ ምክንያቶች ለታሰሩ ግለሰቦኖች የሚሟገተው ድርጅት «ፍሪደም ናው» ዛሬ ባወጡት መግለጫ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ አሰምተዋል።
ዋና ፅህፈት ቤቱን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው «ፊሪደም ናው» የተሰኘው አምስት ጠበብትን ያቀፈው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት አጥኚ ቡድን እስክንድርን ለዕስር የዳረገው በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብትን በመጠቀሙ እንደሆነ በዘገባው ገልፅዋል። ቡድኑ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ የጠየቀበትን ምክንያት «በፍሪደም ናው» ድርጅት አቃቢ ህግ የሆኑት-ፓትሪክ ግሪፊዝ ያስረዳሉ፤ « በቡድኑ አስተያየት መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት አቶ እስክንድር ነጋን ያሰረው በመሰረታዊ መብቱ በመጠቀሙ ነው። በዓለም አቀፉ ህግ የሚፈቀድለትን በርካታ የፍርድ ሂደትንም ነፍጎታል። እስራቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መብቶችን ለማክበር የገባችውን ግዴታ የሚጥስ ካለፍርድ ሂደት በዘፈቀደ የተፈፀመ ነው። በዚህም የተነሳ ነው ጉዳዩን የተከታተለው ቡድን አቶ እስክንድርን አሁኑኑ እንዲፈታ የጠየቀው።

ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄይ እና ሌሎች ድርጅቶች በተደጋጋሚ ለታሰሩ ጋዜጠኞች ይቆማሉ። ሆኖም እስክንድር አሁንም በእስር ላይ ነው የሚገኘው፤ ታድያ ቡድኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ምንድን ነው የሚጠብቀው?
« ተስፋ የምናደርገው ወይንም ተስፋ ያደረግነው የኢትዮጵያ መንግስት አሰባስበን ጉዳዩን ለሚመለከተው ቡድን ለላክነው ፊርማ መልስ ይሰጣል ብለን ነበር። ነገር ግን ያሳዝናል መልስ አልሰጡም። የተባበሩት መንግስታት አስተያየትን የያዘ ነበር አዲስ የስክንድርን ጉዳይ በተመለከተ። በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አሉ እንዲፈታ የጠየቁ ። እንዲሁ በርካታ ቁጥር ያላቸው አለም አቀፍ ተቋማትም ጉዳዩ እንደሚያሳስባቸው አሳውቀዋል። ይህ ግን የመጀመሪያው ነበር አንድ አለም አቀፍ አቋም መጥቶ መፈታት አለበት ሲል። ይህንን በዚህ ሳምንት ሊያደርግ ይችላል። በዚህ ሳምንት ውስጥ ብይን እንደሚሰጥ ቀጠሮ ነበር። እና ትኩረት ሰጥተው የፊርማውን ጉዳይ ይመለከታሉ እና ይፈቱታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። »
ከእስክንድር ነጋ ሌላ ሌሎች ጋዜጠኞችም በእስር ላይ እንደሚገኙ በዘገባው ተካቷል። የሌሎቹስ ጉዳይ ምን ይመስላል? በምን ሁኔታ ላይ ነው ያሉት?
« በሌሎቹ ጉዳዮች ላይ ራሴን ባለሙያ አድርጌ መቁጠር አልሻም ምክንያቱም እኛ ህግን ተከትለን የምንሰራ እና ለግለሰብ ደንበኞቻችን የቆምን ነን። እርግጥ ሌሎች እንደ ርዕዮት ያሉ እንዳሉ አውቃለሁ። እስክንድር ፤ በጥልቀት የሚያተኩር ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የታወቀ ጋዜጠኛ ነው። እናም በአሸባሪነት ተከሰው ጋዜጠኞች በእስር ላይ ጊዜያቸውን እንዲገፉ ማድረግ በእርግጥ የሚያሳስብ ጉዳይ ነው። የእስክንድር መታሰር በተናጥልም ቢሆን ቢያዩት እንደሚመስለኝ የኢትዮጵያ መንግስት በሰፊው በሚነቀፈው አሻሚነት ባለበት የፀረ ሽብር ደንብ የሚያከናውነውን ተግባር በሰፊው የሚያመላክት ነው።»
ሀሳብን በነፃ በመግለፅ ሂደቱ የአለም አቀፍ ጫና መፍትሄ ስለመሆኑ ፓትሪክ ግሬፌዝ አክለው ሲገልፁም፤ እንደ ዮናይትድ እስቴትስ ያሉ መንግስታት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋ የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ቅርብ ትስስር ስላላቸው መንገዱ ይኖራቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች መከራ ያለዉ እያስላከ ሲከፍል፥ የሌለዉን አጋቾቹ ይደበድቡ፥ ይደፍሩት ገቡ።ኢትዮጵያዊዉ ዱላ መደፈሩን መቋቋም አቅቶት ሞተ።«ከሞተ በሕዋላ አስከሬኑን እኛን ባሰሩበት ክፍል ዉስጥ ተዉት፥ አስከሬኑ ከበሰበሰ በሕዋላ ትላትሎች ሲወሩት አዉጥተዉ እንድጥለዉ አስገደዱን» ይላል ትረፍ ያለዉ ኤርትራዊ።


08 04 13
የኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች ሥቃይ-ሰቆቃ፥ ለዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾ ድርጅቶች፥ ለርዳታ ሰጪ ተቋማትም ያለፍ አገደም ርዕሥ ነዉ።ለጋዜጠኞች በተለይም ለትላልቆቹ መገናኛ ዘዴዎች እንደ ሊቢያዉ ጦርነት የሐያሉን ዓለም ትኩረት ካልሳበ ከቁብ የሚገባ አይደለም።የደራሲዎች ብዕር፥ የፊልም አንሺዎች ካሜራ ቃኝቶታል፥ ግን ከወግ ማጣፈጪያነት አላለፈም።ለነሱ የዕለት ከዕለት ጩከት፥ ሥቃይ፥ ሲከፋም ሞት ነዉ።ሰሚ ያጣዉን የደካሞች ተደጋጋሚ፥ ደማቅ ጩኸት ላፍታ ዳግም እንስማ።አብራችሁኝ ቆዩ።
      ዓለም፥ ሥለ ፍትሕ፥ ዲሞክራሲ፥ ሥለ ሰዉ እኩልነት፥ ሥለ መብት ነፃነት፥ ሥለ ሥደተኞች፥ ሥለ ጋዜጠኞች፥ ሥለ ሴቶች፥ ሥለ ሥደተኞች ሌላ ቀርቶ ሥለ ዉሻ-ድመቶች፥ ሥለ አሕያ-ፈረሰች፥ ደሕንነት የሚሟገቱ ዕልፍ-አዕላፍ ድርጅት፥ ተቋማት አሏት።
የኢትዮጵያዊቷ የቤት-ሠራተኛ ሸዋዬ ሞላ ሊቢያ ዉስጥ የተፈፀመባት ግፍ ከዓለም ጆሮ የደረሰዉ ግን ቀጣሪ፥ ደብዳቢ፥ ገራፊ፥ አሰቃይዎቿ ከዓለም ሐያላን ጋር ሲጋጩ እንጂ ዓለም የብዙ ጉዳይ ተከራካሪ ብዙ ድርጅት ተቋማት ሥላሏት አልነበረም።አሁንም የሐኒባል ቃዛፊ ባለቤት ኢትዮጵያዊቷን በማሰር፥ መደብደቧ፥ በፈላ ዉሐ ወይም ዘይት በማንጨርጨሯ በሕግ የጠየቀታት አካል ሥለመኖር አለመኖሩ እስካሁን የምናዉቀዉ የለም።

One of the seventy survivors of an incident where over forty others suffocated to death in a truck container, is treated in the regional hospital in the capital Dodoma, Tanzania Wednesday, June 27, 2012. An official in Tanzania says that 43 Ethiopian and Somali nationals suffocated in the truck they were being smuggled in and Tanzania's state television said the bodies were thrown off the truck and dumped in the bush after the driver of the truck realized some of the people he was smuggling had perished. (Foto:Khalfan Said/AP/dapd)
ታንዛኒያ፤ ከብረት ሰንዱቁ ሞት የተረፉ ኢትዮጵያዉያን


ያኔ ግን ምዕራባዉያን ያዘመቱት ጦር የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊን ሥርዓት ማፍረሱ፥ቃዛፊና ታማኞቻቸዉን መግደሉ ለሸዋዬ የሥቃይ፥ ሰቆቃዋ መቃለል-ሰበብ፥ ከሞት ደጃፍ የመመለ- ምክንያት፥ ብሥራትም ጭምር ነበር።ሊቢያ የዘመተዉን የአሜሪካ-አዉሮጶችን ጦር አጅበዉ የዘመቱት የሐያል-ሐብታሙ ዓለም፥ ጋዜጠኞች ጉዳያቸዉ ባያደርጉት ኖሮ በሸዋዬ ላይ የተዋለዉን ግፍ ጉዳዬ የሚለዉ መገኘቱ ሲበዛ አጠራጣሪ ነበር።

የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!


የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከመንግስት ሸሽተው ተሰደዱ!


ከአቤ ቶክቻው
የፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነችው ማስተዋል የህትመት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የነበረው ማስተዋል ብርሃኑ እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የሆነው አርአያ ጌታቸው መንግስትን ሸሽተው ከሀገር ተሰደዱ!
ማስተዋል ብርሃኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚያዘጋጃት ፍትህ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ ሲሆን በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ፍትህ፤  ”ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱስ ለምን ሞቱ ትላለች…” ተብላ ከሰላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ቢደረግም መንግስታችን በቅጡ ስላልተደሰተ በአዘጋጁ ተመስገን እና በአሳታሚው ማስተዋል ብርሃኑ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ (የማይታወቅ ከሆነ አሁን ይታወቅ)
እነ ማስተዋል ብርሃኑ በተከሰሱበት በዚህ ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀው ለሚያዝያ 17 2005 የተቀጠሩ ሲሆን በክሱ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስራ ሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል፡፡ ማስተዋል ሸሽቶ ከመውጣቱ በፊት የመንግሰት ደህነነት ሰዎች በተደጋጋሚ እየተከታተሉ የእጅ ስልኩን በመንጠቅ ከማን ጋ እንደተደዋወለ እና ምን አይነት መልዕክት (ሜሴጅ) እንደተለዋወጠ በግድ ያዩበት እንደነበር ነግሮኛል፡፡

በነገራችን ላይ የፍትህ አሳታሚ እና ፍትህ ጋዜጣ በቀጠሮ ከተያዘው ክስ በተጨማሪ ወደ አርባ የሚጠጉ በይደር የተያዙ ክሶችም አሉበት፡፡
በተጨማሪም ከስድስት አመታት በፊት የተቃውሞውን ጎራ የተቀላቀለው ወጣት አርአያ ጌታቸው በበኩሉ በተለይ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽን ማሰናዳት ከጀመረ ወዲህ የበረታ ክትትል እና ማስፈራሪያ ከመንግሰት የስጋ ዘመዶች እንደደረሰበት ይናገራል፡፡
ከዚህ በፊት አንድ የፌደራል ፖሊስ ኮማንደር በመኪና አፍኖ የማያውቀው ቦታ ከወሰደው በኋላ ለተመስገን ደሳለኝ ከውጪ ሀገር ያሉ አሸባሪ ዲያስፖራዎች የሚያደርጉለት የገንዘብ እርዳታ መኖሩን እና በመሃል ሆኖ ገንዘቡን የሚያቀባብለው ደግሞ እርሱ እንደሆነ ነግሮት፤ ይህንን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በእህትህ እና በእናትህ ላይ ፈርደሃል ማለት ነው… የሚል ዛቻ አድርሶበታል፡፡
ከአመት በፊት ይህ ማስፈራሪ የደረሰው አርአያ፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ሲል ቤት ተከራቶ መኖር ቢጀምርም፤ ከአመት በላይ የዘለቀው ይኸው ማስፈራሪያ አሁንም እጅግ ተባብሶ “ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም ብለንህ እስካሁን አላቆምክም ስለዚህ እንገድልሃለን!” በሚል ቃል በቃል ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው “ገዳዮቹን” መሸሹን ይናገራል፡፡ አርአያ የፍትህ ጋዜጣ ድረ ገጽ አዘጋጅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱት ግንባር ቀደም ወጣቶች አንዱ ነው፡፡
በፍትህ ምክንያት የተሰደዱት ማስተዋል ብርሃኑ እና አርአያ ጌታቸው አሁንም የደህንነታችን ነገር ስጋት ላይ ነው፤ ብለው ያሉበትን ቦታ እንዳልናገር አደራ ብለውኛል፡፡ የምናገረው ነገር ግን አለኝ፤ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፤
እንደዚህ እያባረሩ እና እንደዚያ እያማረሩ ስንት አመት መዝለቅ ይቻላል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለው ከጥቂት እርምጃ በኋላ እግራችሁ እግራችሁን ጠልፎ ይጥላችኋል!

በፌስ ቡክ “ስም አጉድፈሀል” የተባለው ተማሪ በ5 ሺ ብር ዋስ ተፈታ


በፌስ ቡክ “ስም አጉድፈሀል” የተባለው ተማሪ በ5 ሺ ብር ዋስ ተፈታ


መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንትቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ አመትተማሪ የሆነው  ማንያዘዋል እሸቱ ለኢሳት እንደገለጠው ከአንድሳምንት እስር በሁዋላ፣ የአርባ ምንጭ ፍርድ ቤት “ስትፈለግትመጣለህ” በማለት  ብር ዋስ ለቆታል። ወደ ፈተናለመግባት ሲዘጋጅ ሶስት ፖሊሶች መጥተው የፍርድ ቤት ማዘዣበማሳየት እንደወሰዱትና በአርባ ምንጭ እስር ቤት አንድ ሳምንትማሳለፉን ተማሪ ማንያዘዋል ገልጿል።

ተማሪ ማንያዘዋል፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በሙስና መዘፈቁንእንዲሁም በአገሪቱ ያለው የመብት አፈና መጨመሩን የሚገልጽጽሁፍ በድረገጽ አውጥተሀል ተብሎ መያዙን ገልጿል 
አቃቢ ህግ በቂ ማስረጃ አላገኘሁም በማለቱ እንደተለቀቀ የገለጠውተማሪ ማንያዘዋል፣ ይሁን እንጅ 5  ብር በሁለት ሳምንት ውስጥእከፍላለሁ ብሎ ቃል በመግባት በመፈታቱ፣ ይህን ገንዘብ ካልከፈለወደ እስር ቤት እንደሚመለስ ተናግሯል። የደሀ ልጅ በመሆኑገንዘብ መክፈል እንደማይችል የገለጠው ተማሪ ማንያዘዋል፣ ፍርድቤቱ ቶሎ ውሳኔ ቢሰጠው ከጭንቀት እንደሚገላገልም ገልጿል።አሁን ከአሁን መጥተው ይወስዱኝ ይሆን” በማለት  ትምህርቱንተረጋግቶ መማር እንዳልቻለም ተናግሯል።
በጠባብ ክፍል ውስጥ 25  ሰዎች ታስረው እንደነበር፣ ከሙቀቱበተጨማሪ ቱሁዋን አስቸግሮት እንደነበር አልሸሸገም። ተማሪማንያዘዋል ፖሊሶች እና ፍርድ ቤቱ ላደረገለት ትብብርም ምስጋናአቅርቧል።
ተማሪ ማንያዘዋል 4 ነጥብ በማምጣት ዩኒቨርስቲ መግባቱምታውቋል። በሚማርበት ዩኒቨርስቲም እንዲሁ ከፍተኛ ውጤትእያስመዘገበ አለ 21 አመት ወጣት ነው።