ህገመንግስቱ ደንግጓል፡፡ ይህን መብት ዜጎች እንዳይጠቀሙ ያፈነው መንግስት፣ ኢህአዴግን የሚደግፉ አልያም በራሱ ከተጠሩ ሰልፎች ውጪ ዜጎች እንዳይሳተፉ በአሰራር ከልክሏል፡፡ ይህ የመብት ረገጣ ከመሆኑም በላይ በዜጎች መካከል 1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ዜግነትን ያስቀመጠ ነው፡፡ የኢህአዴግን ባናውቅም፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዢዎች የተዋረደ ስነልቦና የለንም፡፡ ሆኖም የግል ጥቅማቸውን ለማደላደል ሲሉ ለቅኝ ገዢ ጠላቶቻችን ያደሩ ባንዳዎች እንደነበሩ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ ሸክፎታል፡፡ ይህን አሳፋሪ ተግባር በጣሊያን ወረራ ወቅት የፈፀሙ ኢትዮጵያውያን ለልጅ ልጆቻቸው የሚያስተላልፉት አንገት ቀና የሚያደርግ ታሪክ አይኖርም፡፡ በዚህም ዘመን ተመሳሳይ ክህደት የሚፈፅሙ አካላት መኖራቸው አይጠረጠርም፡፡ የኢህአዴግ መንግስት በይፋ ለጦር ወንጀለኛውና ለፋሺሽቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን ሀውልት በይፋ ካለማውገዝ ባለፈ ለተቃውሞ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በግፍ የማሰሩን ምክንያት ስንመረምር አንድ መራራ እውነት እንረዳለን፤ ይኸውም ጣሊያን ለኢህአዴግ መንግስት ዋንኛዋ ለጋሽ ሀገር መሆኗ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ መንግስት ተግባር በስልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያዊነት ላይ ከፈፀማቸው ክህደቶች እኩል በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ (ምንጭ፡ ፍኖተ ነጻነት)
Monday, April 1, 2013
ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?

Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment