Thursday, March 21, 2013

የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሳዑዲ አረቢያ ሚዲያዎችን ሊከስ ነው


በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ‹‹የዜጎቼ ሰብአዊ ክብር ተደፍሯል›› ሲል የሳውዲ ሚዲያዎችንና አንዳንድ ግለሰቦችን ሊከስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በአገሪቱ የሚፈፀሙ ማናቸውም በመሳሪያ የታገዙ የዘረፋዎች፣ የውንብድናና የማጭበርበር ድርጊቶች ‹‹ኢትዮጵያውያን ፈፀሙት›› እያሉ ማውራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ከመሆኑ በተጨማሪ በአገሪቱ የተለያዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና በሌሎች ጋዜጦች ላይ ይህንኑ ስሜት ማንፀበረቅ እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደሌባና አጭበርባሪ እየታየ መሆኑንና ዜጎችም ስራ ለመቀጠር አስቸጋሪ ሁኔታዎች እየገጠማቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሳውዲ አረቢያ ላሉ ሚዲያዎች ገለፁት ሲል ዢንዋ ጨምሮ ባስነበበው ዜና እንደገለፀው በህገወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ ገብተው እና በውንብድና ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ምንም አይነት ራሳቸውን የሚገልፅ መታወቂያም ሆነ ፓስፖርት የሌላቸው ዘራፊዎች በተገኙ ቁጥር ‹ኢትዮጵያውያን ናቸው› እያሉ መግለጫ መስጠት እየተለመደ መምጣቱ ኤምባሲውን እንዳስቆጣና ይመለከታቸዋል ያላቸውን አካላትም ለመክሰስ ምክንያት እንደሆነው አምባሳደሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
‹‹በህገ ወጥ መንገድ የገባና በወንጀል ድርጊት ላይ ተሳትፎ የተገኘ ኢትዮጵያዊ ቢኖር እንኳ እንደ ግለሰብ ሊጠየቅ ይገባል እንጂ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ሊወክል አይገባም›› ያሉት አምባሳደር መሐመድ ሀሰን ሚዲያዎች በንፁህ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍ ያለ በደል እየፈፀሙ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
‹‹በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ለህግ ተገዢ የሆኑና ሰርተው ለማደር የሚጥሩ ኢትዮጵያውያን ክብር ያጎደፈ ነው›› ያሉት አምባሳደሩ በሚዲያዎች ዘገባ የተሳሳተ ግንዛቤ የያዙት የአገሪቱ ዜጎችም ኢትዮጵያውያኑን ሲያንጓጥጡ መታየት በሳዑዲ አረቢያ የተለመደ ጉዳይ ሆኗል፡፡
እግዚአብሔር ህዝቦቿን ከስደት ይታደግ!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

የትግራይ ህዝብ ስማ!! (ርዕሰ አንቀጽ)


mekelle


ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን።
ለማን?
ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት የትግራይ ክልል በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በደን፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ ወዘተ ከሌሎች ክልሎች ሁሉ ርቃ መሄዷን ይፋ አድርጓል። በዚህም ደስ ይለናል። አይከፋንም። ከዚህ በላይ እንዲሆን እንመኛለን። ነገር ግን አንድ መልዕክት አለን።
ለማን?
አሁንም ለትግራይ ህዝብ!!
ሓውዜን የትግራይ ወጣቶች ለትግል ግልብጥ ብለው እንዲወጡ አደረገ። ሓውዜን የደረሰው የቦንብ ድብደባ ማንና እንዴት እንደተቀነባበር ብዙ የሚባልለት ቢሆንም የምሬት ጫፍ ሆኖ ህዝብን አሸፍቷል። ዛሬ መጨቆን ያንገፈግፋል ብለው ለትግል በተነሱና በተሰው ታጋዮች ደምና አጥንት ላይ የቆሙ ሌሎች ሓውዜኖች እንዲፈጠሩ አድርገዋል። እያደረጉም ነው።

Wednesday, March 20, 2013

Remembering the end of Melese Zenawi Era



Remembering the end of Melese Zenawi Era

ኢትዮጵያና የግለሰቦች ስለላ በኢንተርኔት - ጥናት፣ ክስና ምላሽ


የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት ማልዌር እየተጠቀመ በተቃዋሚዎች ላይ ስለላ ያካሂዳል ሲሉ በካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲና በዩናይትድ ስቴትሱ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለዶክትሬት ዲግሪ የሚዘጋጁት ዊልያም ማርዣክ እና ሞርጋን ማርኪስ-ቧር ያወጧቸው የክትትል ሪፖርቶች ለሕትመት በቅተዋል፡፡

​​ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ፓሪስ-ፈረንሣይ የሚገኘው ዓለምአቀፍ ቡድን ኢትዮጵያ ያንን የርቀት መከታተያ ሶፍትዌር ግለሰቦችን ለመሰለል ጉዳይ እንደምትጠቀም እንደሚያውቅ ቢገልፅም አንድ የኢትዮጵያ የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባለሥልጣን የሚባለውን ክስ አስተባብለዋል፡፡


የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን ካለፈው ታኅሳስ 6 እስከ 10 የሃይማኖት ነፃነትን ሁኔታ ለመገምገም በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርጎ የጉብኝቱን ውጤት የያዘ ዘገባ ይፋ አድርጓል።
ባለፈው ሰኞ መጋቢት 2 የወጣው ይህ ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት የሃይማኖት አክራሪነት ሥጋት ቢኖርበትም በነፃነት ማምለክንና ሌሎችም መሠረታዊ መብቶችን ማፈኑ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ሊያባብስ ይችላል የሚል ሃሳብ ያቀርባል።
ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና በዋልታ የመረጃ ማዕከል ይፋ የሆነ አንድ የሕዝብ ሃሳብ መለኪያ ጥናትም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት አክራሪነት እንደሚሰተዋል በመግለፅ ማሳሰቢያ አውጥቷል።

« ሪፖርተር » ጋዜጣ በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንደተቋቋመ ያውቃሉ?


(ከኢየሩሳሌም 

.)E-Reporter
አዲስ አበባ አየር ማረፊያ፣ ነሃሴ 13 ቀን 1997ዓ.ም ፣ ምሽት 2 ሰዓት…ለእረፍት መጥቶ የነበረ ጓደኛዬን ለመሸኘት በስፍራው ተገኝቻለሁ። ..እንዳጋጣሚ በቅርብ ርቀት የ<ሪፖርተር> ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊን አየሁት፤ ወደርሱ አምርቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ < ወደ አሜሪካ ለእረፍት የላከውን ልጁን ለመቀበል እንደተገኘ > ገለፀልኝ። …ከዛም ወደ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት በመግባት ወሬ ቀጥልን፤ በመሃከሉ አማረ ፥ « ..ሲሳይና እስክንድር የጋዜጠኝነት ካባቸውን አውልቀው ለምን በግልፅ ፖለቲከኛ አይሆኑም? » ሲል በሹፈት አይነት ጠየቀኝ። « ምን ማለት ነው?» ስል መልሼ ጠየቅኩት፤ ..« በግልፅ የሚፅፉትን አታይም እንዴ?..የቅንጅት ዋና አቀንቃኞች ሆነዋል እኮ..» ካለ በኋላ አያያዘና « ..ይህችን አገር ልደቱና ሃይሉ ሻውል እንዲመሯት ነው የሚፈልጉት?…ልደቱ ነው አገር ለመምራት የሚቀመጠው?..» ሲል ያቺ የማውቃት የአማረ ፌዝና ሹፈት ፈገግታ በስሱ እያሳየኝ፤ …በዛ ሰሞን አማረ <አቋሙን> ይፋ አውጥቶ በቅንጅትና በጋዜጦች በተለይም በኢትኦጵና ምኒልክ ጋዜጦች ላይ በየሳምንቱ ..ለገዢው ፓርቲ የወገነ የቃላት ጦርነት የገጠመበት ወቅት ነበር።
አዳምጬው ሳበቃ እንዲህ አልኩት፥ « አማረ በምርጫው ማግስት ምን ብለህ ነበርየፃፍከው?..የሽግግር መንግስት ይቋቋም..ብለህ አልነበር?.. አሁን አቋምህን ለምን እንደቀየርክ አውቃለሁ!..» ስለው አይኑን በልጥጦ፥ « ምንድነው የምታውቀው?» አለኝ።.. < አዜብ መስፍን በቢቲ ማስታወቂያ ባለቤት ፀጋዬ በኩል አስጠርታህ ሌላ አራተኛ ሰው ጭምር ባለበት ምንድነው የተነጋገራችሁት?..አዜብ ከባለቤቷ የተላከ መልክት ነገረችህ፤ እንዲህ ስትል፥ « ሁሉም ጋዜጦችና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠራርገው እስር ቤት ይገባሉ። አንተም መግባት ትፈልጋለህ ወይ?..በማለት መለስ ንገሪው ብሎኛል፤» ብላ ነግራሃለች። ከዛም አቋምህን ቀየርክ፤ » አልኩት።…ግንባሩን አጨማዶ ገላመጠኝ። ..አያያዝኩና፥ « ደግሞስ አገሪቷን ማን ይምራ ነው የምትለው?..ሕዝብ የመረጠው ማንም ይሁን ማን…ድምፁ መከበር አለበት። አንተ ግን ካለ ሕወሐት/መለስ ሌላ ሊመራ አይችልም ..እያልክ ነው..» አላስጨረሰኝም..ጥሎኝ ሄደ። በወቅቱ ጉዳዩን በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ ፃፍኩት..
አማረ፥ ከማስታወቂያ ሚ/ር ለምን፣ እንዴትና በማን ተባረረ?…« ሪፖርተር » ጋዜጣ በመለስ ዜናዊ <ልዩ> ትእዛዝ እንደተቋቋመ ያውቃሉ?..አሁን የቲቪ ስርጭት እንዴትና በማን ትእዛዝ ሊጀምር ቻለ?…ከነደብረፂዮን ጀርባ በምስጢር የሚሰጠው ድጋፍና ለፓርቲው የሚያደርገው ስውር ተጋድሎ….በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እመለስበታለሁ።
የአማረ ገመና ሲገለጥ!

Tuesday, March 19, 2013

“ፀላእትና ክንከራታትሞም ኢና” “ህወሓትን እናስቀድም … ‘ጠላቶቻችንን እናውድም’!”

tplf


“ፀላእትና ክንከራታትሞም ኢና”
“ህወሓትን እናስቀድም … ‘ጠላቶቻችንን እናውድም’!”
ሦስት ቀናት የፈጀው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ትናንት ተጠናቋል። ለጉባኤው የሚሆን ኣጀንዳ ለመለየትና ልዩነታቸው ለማጥበብ ህወሓቶች ሲነታረኩ ቆይተው ቀጣዩ 11ኛ የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በሰላም ለማጠናቀቅ የተስማሙ ይመስላሉ ሲል ኢትዮ ሚዲያ መድረክ የመቀሌ ዘጋቢውን አብርሃም ደስታን ጠቅሶ ዘገበ።
የስብሰባው ተሳታፊዎች በሁለት ተከፍለው ዘለፋና የጠብ መንፈስ የተሞላበት ጭቅጭቅ ከተካሄደ በኋላ ሌላ ሦስተኛ ቡድን ተፈጥሮ “ህወሓትን እናስቀደም፣ ልዩነታችን ወደ ጎን ትተን የጋራ ጠላቶቻችንን እንታገል፣ ሁለታቹ (ቡድኖቹ) የህዝብ ድጋፍ የላችሁም፤ ስለዚህ በሁለት ከተከፈልን ህወሓት ህልውናው ያበቃል።” በሚል ተማጽኖ ማሰማታቸውን ድረገጹ አመልክቷል። በዶ/ር ቴድሮስ ኣድሓኖም የተመራ የሽምግልና ጥረት ታድያ ሁለቱም ቡድኖች ልዩነታቸው አጥብበው አብረው በጉባኤው እንዲሳተፉና በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸው እንዲተባበሩ ስምምነት ላይ መደረሱንም አመልክቷል።
ልዩነታቸው የከረረ ጠብ እንደወለደና እስካሁን ‘የእግዚሄር ሰላምታ’ እንኳ እንደማይለዋወጡ የገለጸው ዘገባ ከልዩነታቸው መግዘፍ የተነሳ አንዳቸው ሌላኛው ቡድን ቢያሸንፍ እንኳ ለብቻው ህወሓትን ለማስቀጠል የሚያስችል የህዝብና ካድሬ ድጋፍ ሊኖራቸው እንደማይችል ገልጿል። የሚቀጥለው የህወሓት 11ኛ ድርጅታዊ (ዉድባዊ) ጉባኤ “ጉባኤ መለስ” (የመለስ ጉባኤ) ተብሎ ተሰይሟል። መለስ የሁለቱም (የሁሉም) ቡድኖች የጋራ ነጥብ መሆናቸውም ተጠቁሟል። ከጉባኤው በኋላ “ጠላቶች” ያሉዋቸውን አካላት እንደሚመቱ (እንደሚጨፈልቁ) ዝተዋል። ‘ፀላእትና ክንከራታትሞም ኢና!’ የሚል መግለጫ አውጥተዋል፡፡

''መሪዎች ፈራን ካሉ፤ ተመሪዎችስ ምን ይሁኑ?" የፍርሀት ሁሉ - ፍርሀት እሚባለው ካሉት በታች አ’ርጎ በቁም እሚገለው፤ እንደጥላ ሆኖ - የማይርቅ ቢርቁት ከራስ መሸሽ ነው ፍርሀት የሚሉት

አላማ ያለው ሰው አይፈራም። ፍርሀት ብዙውን ግዜ ከአላማ ቢስነተና ካለመተማመን ጋር የተያያዘ ነው። አላማ ያለው ሰው ግብ
አለው። ስለዚህም አላማ ያለው ሰው ከወዲሁ ሊገጥመው የሚችለውን ነገር ጠንቅቆ ያውቃልና ይዘጋጃል። ለያዘው አላም ሙሉ
ግዜውን፣ ሀብቱን፣ እውቀቱንና የሚያስፈልገውን ሁሉ ይጠቀማል። አስፈላጊም ከሆነ ህይወቱን ሳይቀር መሰዋዕት ለማድረግ ዝግጁ
ነው። እርግጥ ነው አላማን ለማስፈጸም ኢሰባአዊነትን መጠቀም ግፍ ነው፤ ወ ያኔያዊነት ነው።
የህዝብን ብሶት አንግቦ ከገዥዎች ጋር ለመታገል የፈለገ ወይም የተመረጠ መሪ፤ ተከታዮችና ደጋፊዎች ለማፍራት አርዕያ መሆን ብቻ
አይደለም፤ ለያዘው ሀገራዊ አላማ እንደአስፈላጊነቱ በድፍረትና በመተማመን ፊት ለፊት መጋፈጥ አለበት። መሪነት አስትማሪነት ነው።
መሪነት ሀላፊነት ነው። በተለይም የነጻነትና የአንድነት ትግል መሪ መሆን ደግሞ ጀግንነትንና ቆራጥነትን ይጠይቃል፤ መከራም ነው፤
ግን ደግሞ ለራስ የህሊና የክብር አክሊል መቀናጀት ሲያድል፤ የሀገርና የወገን ኩራት መሆንም ነው።
እንደወያኔ ያለውን አገዛዝ ለመታገል የሚነሳ ግለሰብ ሆነ ቡድን ወይም ድርጅት ከወዲሁ ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር እስራት፣ ድህነት፣
ግርፋት፣ ውርደት፣ ሞት፤ በአጠቃላይ ለሰው ልጅ ስቃዮችና መከራወች የተባሉ ሁሉ እንደሚፈጸምበት ነው። ወያኔ ከአፈጣጠሩ
ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለው በመግደልና በማስገደል፤ ብሎም ለኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያን ይጠቅማሉ ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች
ሁሉ በማፍረስ፣ በማጥፋት፣ በመሸጥና በማውደም ነው። ግን እንደ ዶ/ር መረራ ጉዲና የመሳሰሉ ተቃውሚዎች እድሜ ልካቸውን
ከወያኔ ጉያ ውስጥ እንዳልመሸጉ ሁሉ፤ "እኛ የኢህአዴግን ጠመንጃ እንፈራለን፤ ኢህአዴግ ደግሞ የ97 ቱን የህዝብ ጎርፍ ይፈራል…..."

Ethiopia 'blocks' Al Jazeera website The leading website Ethiomedia.com has been blocked since 2007 By Aljazeera; March 19, 2013

Al Jazeera’s English and Arabic websites are reported to have been blocked in Ethiopia, raising fresh fears that the government is continuing its efforts to silence the media. Though the authorities in Addis Ababa have refused to comment on the reported censorship, Google Analytics data accessed by Al Jazeera shows that traffic from Ethiopia to the English website had plummeted from 50,000 hits in July 2012 to just 114 in September. Traffic data revealed a similar drop for the Arabic website, with visits to the site dropping to 2 in September from 5,371 in July. A blogger, who cannot be identified for his own safety, said Ethiopian censors had been targeting Al Jazeera since the Qatar-based network began airing coverage of ongoing protests against the way in which spiritual leaders are elected in the Horn of African nation. The steep decline in web traffic began on August 2 last year, the same day that Al Jazeera Mubasher aired a forum with guests denouncing the government's "interference" with Muslim religious affairs, and three days after Al Jazeera English published an article detailing deadly ethnic clashes between two of the country's southern tribes.

ኢትዮጵያ የጀርመን ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት


የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚቴና በጀርመንኛው «ፔን ሴንትሩም ዶይችላንድ» ተቋም የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ስለሠብዓዊ መብትና ስለመናገር ነፃነት መገደብ በይፋ እንዲናገሩ በደብዳቤ ጠየቁ። በጀርመን ምክር ቤት የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ እንደራሴና በምክር ቤት የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ ም/ሊቀመንበርም ተመሳሳይ ነጥብ አንስተዋል።
እጅግ የተከበሩ የጀርመን ፕሬዚዳንት፤ ስለነፃነት መጠየቁ ተሸላሚው ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ሀገርን በከፍተኛ ሁኔታ መክዳትና ሽብርተኝነት በሚል ለ18 ዓመታት እስር ዳርጎታል ይላል ይፋዊው ደብዳቤ ሲንደረደር። ደብዳቤውን ለጀርመኑ ፕሬዚዳንት ጽፈው ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚቴና በጀርመንኛው «ፔን ሴንትሩም ዶይችላንድ» የተሰኘው ተቋም በአንድነት ነው። የተቋሙ ምክትል ፕሬዚዳንትና በእስር ቤት ለሚገኙ ፀሀፊዎች የሚሟገተው ተቋም ሃላፊ ዛሻ ፎይሸርት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮኣሒም ጋውክ በኢትዮጵያ ጉዟቸው ወቅት ግልፅና ይፋ በሆነ መልኩ ሊያስተላልፉት የሚገባ መልዕክት አለ ይላሉ።

Monday, March 18, 2013

Ethiopia: Journalism under anti-terrorism law


How the US 'war on terror' has provided cover for laws that are being used to silence dissident journalists.
When the Paris-based media watchdog group, Reporters Without Borders released its annual Press Freedom Index, 
few were surprised that Ethiopia had dropped 11 places to 137.
Journalists in the country have never truly been free to report however developments in the region over the last few years have had a detrimental effect on the media environment.
With the disputed 2005 general election, the continued conflict with separatist groups and the spectre of the Arab Spring arriving in the country – the government in Addis Abba has been cracking down on the media
And one of its most effective tools is a vague, far reaching anti-terrorism law that has sentenced at least 11 journalists to harsh prison terms.

In 2009, former Prime Minister Meles Zenawi's government passed the anti-terrorism proclamation. In August last year Zenawi died but the legislation survived under his successor Hailemaraiam Desalegn.
Much of the reporting on Ethiopia these days is done at a safe distance. According to media watchdogs, 49 journalists fled the country between 2007 and 2012 to get away from a government that does not want to talk about this issue. The Listening Post made several interview requests but were denied.
The government did tell us that those in prison are there for their terrorist activities and not for being journalists. With convictions stacking up however, terrorism and critical journalism in Ethiopia are starting to look like one in the same.

Sunday, March 17, 2013

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው! ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡

መንግስት በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ነው። መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ!

ድርጅቱ ( በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው። በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ) ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል ፣ በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን የወያኔ ካድሬዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ ከፈረሱ እና እየፈረሱ ካሉ ቤቶች አብዛኞቹ የአማራ ተናጋሪዎች መኖሪያ መሆናቸውን መታዘቡን ” ገልጿል። በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተማዎች የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የባንክ ብድርን ጨምሮ መሬት እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ ከፍተኛ ግብር እየተጫነባቸው በመሆኑ ከንግድ ስርአቱ እንዲወጡ ተድርጓል ብሎአል መኢአድ። በአሁኑ ጊዜ ከ200 በላይ ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በባህርዳር ያለመጣለያ በጎዳና እየኖሩ መሆኑን መኢአድ በመግለጫው አመልክቷል።

ከዳር ቆሞ ለዉጥን መጠበቅ የህልም እንጀራ!!

በሀገራችን ያለዉን ሁኔታ ስንመለከተዉ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል ይቻላል። ይህም ከድጡ ወደ ማጡየሚለዉ በጥሩ ሁኔታ የሚገልጸዉ ይመስለኛል። አበዉ ጉልቻ ቢለዋወጥ እንደሚሉ አፈናዉ፤ ስለላዉ፤እስሩ፤ ግድያዉ፤ ስደቱ፤ ዘረፋዉና፤ ማናለብኝነቱ ሳይቋረጥ ቀጥሏል። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትርናአጋሮቻቸዉም ደግመዉ ደጋግመዉ አስረግጠዉ እንደተናገሩት ለዉጥ የሚባል ነገር እንደማይታሰብናየነበረዉ ሁኔታ ባለበት እንደሚቀጥል ነዉ። ከዚህ አንጻር የለዉጥ የተስፋ ጭላንጭል እንደሌለ በወሬ ብቻሳይሆን በተግባራቸዉም አሳይተዉናል። ምንም መራር ቢሆንም እዉነታዉ ግን ስርአቱ መሪዉን ቢያጣእንኳን፤ በአላማ፤ በአቅም፤ በድርጅትና፤ በስነልቦና፤ ፍጹም የበላይነቱን ተጎናጽፎ  ይገኛል።

ኧረ የፍትህ ያለህ !! ያለ ነፃነት መኖር በቃን! በቃን መኖር ሰለቸን ! ለውጥ ያስፈልጋል!

ከዘካሪያስ አሳዬ
                                                 
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር እና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ዜጎች በእኩልነት ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስቡ፣ የሚናገሩ፣የሚፅፉና የሚቆረቆሩ በጠቅላላው ለእነዚህ ፅንስ ሐሳቦች ዘብ የሚቆሙ በሙሉ የስርዓቱ ጠላቶች ተደርገው በመቆጠር ላይ ናቸው::
   ለአገሪቱ አንድነትና ሉአላዊነት ብልፅግና በጣም ከሚቆጠሩ መሪዎቿና የፓርቲአቸው ጠባብ ጎሰኛ ፖሊሲ የተለየ የሚያስቡ ዜጎችና ቡድኖች ሁሉ ጠላትና ሽብርተኞች ወይንም አሽባሪዎች ወይም በዘመኑ አባባል ጽንፈኛ ተደርገው ይቆጠራሉ።