Friday, October 10, 2014

ሕወሓትና በትግርኛ ተናጋሪዎች ሙሉ ቁጥጥር ስር የወደቀዉ መከላከያ ሠራዊት ከአራት አመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ


  • 928
     
    Share
Ginbot-7-Top-logo_4
ሕወሓትና በትግርኛ ተናጋሪዎች ሙሉ ቁጥጥር ስር የወደቀዉ መከላከያ ሠራዊት
ከአራት አመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ
መስከረም  26 2007 ዓ..
ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ ትግራይ (ሕወሓት) ምን ያክል የኢትዮጵያን የፖለቲካ መዋቅሮች እንደሚቆጣጠር ለማወቅ በአገሪቱ የመከላከያ፣ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች ዉስጥ ዋና ዋና የትዕዛዝ ሰጪና ቁጥጥር ቦታዎች ላይ በሀላፊነት የተቀመጡትን የትግራይ ተወላጆች ብዛት መመልከቱ በቂ ይመስለናል። የሕወሓት መሪዎች ስልጣን በያዙባቸዉ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት ዉስጥ እየገነቡት ላይ ያለዉን ስርዐት መልካምና ሁሉን አቀፍ ስርዓት ለማስመሰል አንዳንድ ከነርሱ ቁጥጥር ዉጭ መተንፈስ እንኳን የማይችሉ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆችን አልፎ አልፎ ስልጣን ላይ አስቀምጠዋቸዉ ነበር። ዛሬ ሕወሓቶችን እራሳቸዉን እጅግ በጣም በሚያሳፍር መልኩ እነዚህ በጥንቃቄ ለቅመዉ ያመጧቸዉንም የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች ወደመጡበት መልሰዋቸዉ በሁሉም መስክ ቁልፍ የሆኑ የአገሪቱን  የስልጣን ቦታዎችን የሚቆጣጠረዉ የትግራይ ተወላጅ ሕወሓቶች ብቻ ሆነዋል። አያሌ ኢትዮጵያዉያን የህወሓትን አገዛዝ “ዘረኛ” አገዛዝ ነዉ ብለዉ የሚጠሩት ይህንን ሙልጭ ያለ በዘር ላይ የተመሰረተ ጭፍን አገዛዝ ተመልክተዉ ይመስለናል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ ለፈጠረዉ ዘረኛ ስርዓት ብቸኛ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የሚችለዉ ደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ነጮች የፈጠሩት ዘረኛ (Apartheid) ስርዓት ብቻ ነዉ። በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ በተለይ በቁጥሩ ከፍተኛ ብልጫ ያለዉና ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነዉ ሠራዊት እጅግ ያኮረፈ፤ የተቆጣና ያመረረ ሠራዊት ከመሆኑ የተነሳ እራሱን የሚመለከተዉ እንደ አገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሳይሆን አንደ ህወሓት የቤት ዉስጥ አገልጋይ ባሪያ ነዉ። ይህ የሕወሓት ዘረኞች በሠራዊቱ ላይ የፈጠሩት የመገዛትና የበታችነት ስሜት በየቀኑ ከፍተኛ ቁጣና የዉስጥ ለዉስጥ ተቃዉሞ የሚገጥመዉ ቢሆንም ህወሓት በዘረጋዉ ከፍተኛ የአፈና መረብ የተነሳ የህዝብ መነጋገሪያ አርዕስት መሆን አልቻለም። የህወሓት መሪዎችም ቢሆኑ ይህንን ቁጣና ተቃዉሞ በሚገባ ስለሚያዉቁ “ግምገማ” እያሉ በሚያዘጋጇቸዉ መድረኮች ላይ እንደዚህ አይነቶቹን በእነሱ የበላይነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ማስተናገድ ቀርቶ ጥያቄዎቹ እንዲነሱም አይፈቅዱም። አንዳንዴ ደፍረዉ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሱ ግለሰቦች ሽብርተኛ፣ የደርግ ስርዐት ናፋቂዎች፣ ጠባብ ብሄረተኞች ወይም የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች የሚል ተቀጽላ ስም ይሰጣቸዋል። ዛሬ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዉ በተለያዩ የወያኔ እስር ቤቶች ዉስጥ የሚሰቃዩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ የበቁት በመከላከያ ተቋሞች ዉስጥ ሠራዊቱን በየትኛዉም እርከን የሚመሩ መኮንኖች አመዳደብ ወታደራዊ አመራር ችሎታን፤ ልምድንና የብሄር ስብጥርን ያካተተ መሆን አለበት ብለዉ ደፍረዉ በመናገራቸዉ ነዉ።
ዛሬ የወያኔን መከላከያ ሠራዊት እየለቀቁ ከአገር የሚወጡ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል። እነዚህ ወታደራዊ መሪዎች፤ የበታች መኮንኖች፤ ባለሌላ ማዕረጎችችና ተራ ወታደሮች ከጠላት እንከላከላን ብለዉ የማሉላትን እናት አገራቸዉን እየለቀቁ የሚወጡት በወያኔ ጦር ዉስጥ ስር የሰደደዉ ዘረኝነትና በዚህ ዘረኝነት ላይ የተመሰረተዉ አመራር የሚያደርስባቸዉ በደል አንገፍግፏቸዉ ነዉ። በየጎረቤቱ አገር ተሰድደዉ በችግር ላይ የሚገኙ ምርጥ የኢትዮጵያ የወታደራዊ ሳይንስ አዋቂዎች ሁሉም በአንድ ድምፅ የሚናገሩት ሠራዊቱ ዉስጥ ይደርስባቸዉ የነበረዉ ንቀትና ዉርደት የሰዉ ልጅ መሸከም ከሚችለዉ በላይ መሆኑን ነዉ።
ሕወሓትን ለረጂም ግዜ የመራዉ መለስ ዜናዊና ጓደኞቹ ሥልጣን በያዙባቸዉ በመጀመሪያዎቹ ሁለትና  ሦስት አመታት ጊዜያት ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች  ሰዎች መያዛቸዉን አስመልክተዉ ሲናገሩ ህወሓት ለ17 አመታት የደርግን አምባገነናዊ ስርዓት ሲዋጋ የፈጠረዉ ወታደራዊና ድርጅታዊ ግዝፈት አብዛኛዉ የወታደራዊና የደህንነት አመራር ቦታ በህወሓት ታጋዮች አንዲያዝ ምክንያት ሆኗል ብለዉ ከተናገሩ በኋላ ይህ አሰራር በሂደት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይርና የኢትዮጵያ የፖለቲካና ወታደራዊ የሥልጣን ክፍፍል የአገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች ጥንቅር ያገናዘበ ይሆናል ብለዉ ተናግረዉ ነበር። ሆኖም ዛሬ ይህ ከተነገረ ከሃያ አመታት በኋላና ይህንን የተናገረዉ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ከሁለት አመታት በኋላ የሕወሓት የሥልጣን ቁጥጥር ጭራሽ አጋሽቦ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከትግርኛ ቋንቋ ዉጭ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ ሥልጣን አይመጡም የሚባልባት አገር ሆናለች። በኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ በገነባዉ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የዕዝ፤ የክፍለጦርና የመምሪያዎች አዛዥ ለመሆን ዋነኛዉ መለኪያ የትግራይ ብሄረሰብ ተወላጅና የሕወሓት ታማኝ አገልጋይ መሆን ነዉ እንጂ ችሎታ፤ ልምድ፤ ብቃትና የወታደራዊ ሳይንስ ክህሎት አይደለም። ችሎታ፤ ልምድና ብቃት መመዘኛ ሆነዉ የሚቀርቡት በመጀመሪያ ለሹመት የታጨዉ መኮንን የትግራይ ተወላጅ እና የሕወሓት ታማኝ አገልጋይ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ብቻ ነዉ።
የሕወሓት የስልጣን ሞኖፖሊ በወታደራዊ ደህንነት ተቋሞች ላይ ብቻ ተወስኖ አያበቃም። አብዛኛዉን የአገሪቱ የኤኮኖሚና ማህበራዊ ተቋሞችም ወይ ከላይ አለዚያም ከታች ሆነዉ የሚቆጣጠሩት የሕወሓት ታማኝ አገልጋይ ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸዉ። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለይስሙላ የተቀመጠና ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የመጡ ሰዎች የሚገኝበት አገዛዝ አለ፤ በዚህ አገዛዝ ዉስጥ ደግሞ አገሪቱን ወዳሰኘዉ አቅጣጫ በዘፈቀደ የሚዘዉረዉና ከትግርኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ሌሎች የማይገኙበት በአገዛዙ ዉስጥ ሌላ ቡድናዊ አገዛዝ አለ። ዛሬ እነ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ አባዱላ ገመዳና ደመቀ መኮንንን የመሳሰሉ ምስለኔዎች ስልጣን ላይ የተቀመጡ ነገር ግን የሕወሓት ጌቶቻቸዉ ከሚነግሯቸዉ ዉጭ በራሳቸዉ ምንም አይነት ትዕዛዝ መስጠት የማይችሉ አሻንጉሊቶች መሆናቸዉን እነሱ አራሳቸዉም የተገነዘቡት ይመስላል።
ግንቦት ሰባት- የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዛሬ አራት አመት (እ.ኤአ.በ2009) በዘር የተደራጀዉን የወያኔ መከላከያ ተቋም አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በመረጃ አስደግፎ ለአለም ህዝብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። ግንቦት ሰባት ይህ ይሻሻላል ወይም አደረጃጀቱ በሂደት ይለወጣል ተብሎ የተነገረለት የወያኔ መከላከያ ተቋም ጭራሽ ከድጡ ወደማጡ እያዘገመ መሆኑን በጥናታዊ መረጃዎች አስደግፎ እንደሚከተለዉ ያቀርባል። በዚህ ጥናት ዉስጥ የወያኔን መከላከያ ሠራዊት ይዘትና ቅርጽ በሚገባ የሚያዉቁ፤ ሠራዊቱን ለቅቀዉ የወጡና አሁንም በሠራዊቱ ዉስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ከፍተኛ መኮንኖች ተሳትፈዋል። ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበዉ ሠንጠረዥ የተለያዩ የመከላከያ ተቋም የስልጣን ቦታዎችን፣ በስልጣን ቦታዎችን እነ ማን እንደተቀመጡና  የተወለዱበትን ብሄረሰብም ጭምር ያሳያል።
Am1 (1)
Am2
Am3
Am4
Am5
Am6
-- Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.--


Thursday, October 9, 2014

ኢትዮጵያ በ21ኛው ክፍሇ ዘመን ያጋጠማት ፈተና



ባንድራ ጨርቅ ነው
ወዯብ ሸቀጥ ነው
ወዯብ ሇሃገር ጥቅም አይሰጥም የነፃ አውጪው ግብ
ሇወዯብ በቀን በትንሹ የሚወጣው ወጪ 3 ሚሉዩን ዶሊር
ኢትዮጵያ ወዯብ አሌባ በመሆኗ የምጣኔ ሃብቷ 11 በመቶ አዯገ የሚሌ ሚ/ር ያፈራች ሃገር
ትምህርት የኢትዮጵያን ግዛት ማጥበቡ
ምቀኝነት ሙያ መዯረጉ
የሃገሪቱ ሃብት በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር መሆኑ
ከዜጎች መሬት ነጥቆ ሇጠሊት መሰጠቱ
የኢትዮጵያ ድህነት መነሻ ነፃ አውጪው ቡድን
ሃገሪቱን ሇጠሊት አሳሌፎ የሰጠው ነፃ አውጪው ጎሰኛው
ወገን ሃገርን የማይወዯው ነፃ አውጪው ቡድን
የሃገሪቱን ምሁራን በማዯን ስራው የሆነው ነፃ አውጪው ቡድን
ነፃ አውጨው ነፃነት ገፋፊው
ኢትዮጵያን የማይወክሌ ሃገር አስገንጣይ ሕዝብን እንመራሇን
በግዳጅ ድህነትን የሚጭን የጎሳ ነፃ አውጪ ነጣቂው ቡድን
ነፃ የነበረች ሃገር በጎሰኞች ነፃቷን የተነጠቀች ኢትዮጵያ
የእምነት ቦታዎች/ገዳማት/ ማፍረስ ማጥፋት ማቃጠሌ
መዝርፍ ማዘረፍ
የስኳር ማምረቻ
ሃይማኖት ማመን እንዯ ወንጀሌ መቆጠሩ
የጎሳ በሽታ እንዯ ወረርሽ መስፋፋቱ
አረብ ሇእርሻ ወዯኢትዮጵያ እኛ ሇግርድና ወዯአረብ መፍሇስ
ኢትዮጵያ ቅርጾችን ከሃገር ማጥፋት ዘመቻ ወያኔና ተባባሪዎቹ ዋና ስራቸው
ቤተክርሲያቲያኖች አካባቢ የጭፈራ ሰፈር ማስፋፋት
መሲጊዶች ሙስሉም አሌባ መሆናቸው
ወንድም ወንድሙ ገድል ሃውሌት የሚሰራባት ሃገር
ሃገር ማስገንጠሌና ሃብታም መሆን
ከወያኔ ጋር መተባበር በየክሌለ ፎቅ መስራት
የጎሳ ግጭት መባባስ በዘመነ ወያኔ
529 ኪል ግራም ወርቅ ባላስትራ መሆኑ
46 ኪል ግራም ወርቅ የሰርቀው ላባ/ቦች/ ሶስት ወር ቅጣት የሚወሰንባት
አማራ የሚባሌ ዘር ከኢትዮጵያ ጨርሶ ማጥፋት
ጎሳችሁን እምንሰጣችሁ እኛ ወያኔዎች ነን
የምትሞቱበትን ቀን የሚነጋራችሁ ወያኔ ነው
ዩኒቨርሲቲዎች የሚያፈሩት የሰው ሃይሌ በጠባብ ቅኝት የተቃኙ
የሰሞኑ የተማሪዎችና የሰራቶች ስብሰብ ውጤት ኢትዮጵያ የተዋረዯችበት/ አሳፋሪ
የማይሰርቅና የማያሰርቅ ጎታች፣ካሃድ፣ኋሊቀር
ማንበብ ፣መጠየቅ፣መጻፍ፣መናገር፣መወያየት ስሇሃገር ማሰብ ወንጀሇኛ፣አሸባሪ፣የግንቦት ሰባት አባሌ፣ጠባብ
የበጎ አድራጊዎች መናሃሪያ የአሇማችን ድሃ ሃገር
ቀ.ኃ.ሥ እና ዯርግ ከሃገራቸው ጉዳይ ነበራቸው ወያኔ ግን ምንም ጉዳይ አሌነበረው/የሇውምየጎሳ ነጻ አውጭው ቡድን የሃገርን ሃብት ወዯውጭ ማሸሽ/መዝርፍ/ማዘረፍ
መፈናቀሌ በወያኔ ዘመን ተተገበረ
የሃገር ክህዯት በወያኔ ዘመን ተተከሇ
የሃገርን ሃብት በመዝረፍ ሃገርን ያንቀጠቀጠው ነፃ አውጪ
እምነት በጎሳ አስተዳዯር/በወያኔ/ እዳ፣ኩነኔ፣መከራ/ካመናችሁ በባዕዳን/እምነት የሇም
እምነት በቀ.ኃ.ሥ አስተዳዯር አንድ ሃይማኖት አንድ ሃገር
ነፃ አውጪው ዜጎችን በሰይጣናዊ ስራ ተሰማርቶ በክሌሌ መከሇሌ/መወስን፣ማጣሊት፣ማናከስ
እምነት በዯርግ/በመንጌ/ዘመን ሃገር የጋራ ሃይማኖት የግሌ
በኢትዮጵያ ነጭ ሽብር በኢሕአፓ
በኢትዮጵያ ቀይ ሽብር በዯርግ
በኢትዮጵያ ጥቁር ሽብር በጎሳ ዘመን/ወያኔ
ስሌካችን ሽቦ አሌባ
ማብሰያችን እሳት አሌባ/የሽ
መኪናችን ቁሌፍየሇሽ
ምግባችን ውፍረትየሇሽ
ጎማችን ቱቦየሇሽ
ሌብሳችን እጅጌየሇሽ
ወጣቶቻችን ስራየሇሽ
የጎሳ መሪዎቻችን ሃፍረትየሇሽ/የሇሾች/ ሃገር አይወክለ/ሃገር የሇሽ
ግንኙነታችን ዋጋቢስ/ትርጉም የሇሽ/
አመሇካከታችን/አስተሳሰባችን ግድየሇሽ
ሚስቶቻችን ሃፍረትየሇሽ/ዯፋሮች
ስሜታችን ግፈኛች
ህጻናቶቻችን አባትየሇሽ
ትምህርት ፍይዳቢስ/ዋጋየሇሽ
ሌጆቻችን ስርዓት የሇሽ
ተስፋችን መጨርሻየሇሽ
ንግግራችን ድምጽየሇሽ
ድንበራችን ወሰንየሇሽ
ሃገራችን ጠባቂየሇሽ
ሁለነገራችን/ው ያነሰ/ዝቃጫች
ምሁራኖቻችን የሰው ትንሾች/
ዘረኞች ጠባቦች፣ጡት ነካሾች ማሰቢያየሇሾች

ሳ.አ
ከአዲስ አበባ

ወያኔ ሲያስር አሜን….ሲገድልም (በኤፍሬም ማዴቦ)


ብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ”
ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ
ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት
ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ ለመሳ ለሁለት የተከፈለች ትመስላለች። እግዝአብሄር ይመሰገን እዉነቱ ግን ከዚህ እጅግ
በጣም የተለየ ነዉ። ርዕሴን የጀመርኩት አሜን ብዬ ነዉና እስኪ አንባቢዉ አንተም አሜን በል። ባንዳነትና ከሃዲነት ኃብታምና
በእድገት ወደፊት የገፉ አገሮችን እየዘለለ ደሃና ኋላ ቀር አገሮችን ብቻ የሚጠናወት ተራ በሽታ አይደለም። ብዙዎቻችን አምባገነን
መሪዎቻችንን ሸሽተን የተጠለልንባት አገር አሜሪካ እነ ሄንሪ ቤስትንና ጆን ብራዉንን የመሳሰሉ ከሃዲዎችን እንዳበቀለች ሁሉ
ኢትዮጵያችንም ትናንት እነ ኃ/ሥላሤ ጉግሳን ዛሬ ደግሞ የኃ/ሥላሤ ጉግሳ የልጅ ልጆች የሆኑትን እነ መለስ ዜናዊን፤ አባይ ፀሐዬንና
ሰብሃት ነጋን የመሳሰሉ የለየላቸዉ ከሀዲዎችን አፍርታለች። በነገራችን ላይ ሙስሊሙ በዱአዉ፤ ክርስቲያኑ በፀሎት፤ ጠቢብ በጥበቡ ፤
ፀሐፊ በምናቡ የባንዳዉንና የከሃዲዉን ብዛት ለመቀነስ ካልተባበሩ በቀር “ወላድ በድባብ ትሂድ” ብለን ባንመርቃቸዉም የባንዳ አባትና
አናት አስካሉ ድረስ ባንዳም መወለዱ አይቀርም።
ደጃዝማች ኃ/ሥላሤ ጉግሳ ማንም ሳያስገድደዉ ወድዶና ፈቅዶ ለወራሪዉ የጣሊያን ጦር ካደረ በኋላ ከጄኔራል ደቦኖ ጋር ሆኖ እናት
አገሩን ኢትዮጵያን ወግቷል። ጣሊያኖች ኃ/ሥላሤ ጉግሳ ከነተከታዮቹ ከጎናቸዉ ተሰልፎ አገሩን ሲወጋ ያደረጉት የመጀመሪያዉ ነገር
ይህ ከሃዲ ሰዉ ከጎናቸዉ መሰለፉን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለዓለም ህዝብ ማሰራጨት ነበር። ታሪክ እራሱን ይደግማል ሲባል አይኑ
አላይ እያለዉ በጆሮዉ ብቻ ለሰማ ሰዉ ዛሬ ማረጋገጫዉ እነሆ በግልጽ ቀርቦለታል። ትናንት ማክሰኞ መሰከረም 27 ቀን የወያኔ
ቴሌቭዥንና ሬድዮ ኢትዮጵያ ዉስጥ በጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀመዉን እስርና ስደት፤ ወያኔ በወገኖቻቸን ላይ የሚፈጽመዉን የዕለት
ከዕለት ሰቆቃና እንዲሁም በቅርቡ አምቦና ኦጋዴን ዉስጥ የተካሄዱትን የጅምላ ግድያዎች የሚደግፉ የዚህ ዘመን ኃ/ሥላሤ ጉግሳዎች
ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ያካሄዱትን የክህደት ሰለማዊ ሠልፍ በተደጋጋሚ ለህዝብ አቅርበዋል። እነዚህ ትናንት ክቡር ባንዲራችን
በአለባሌ ሰዉ አንደበት “ጨርቅ” ተብላ ስትሰደብ ከተሳዳቢዉ ሰዉ ጎን ቆመዉ የሳቁና የተሳለቁ ከሃዲ ሆድ አምላኪዎች ዛሬ
“ባንዲራችን ተደፈረ” ብለዉ የአዞ እምባ ያነቡብናል። የትኛዉ ባንዲራ? ለመሆኑ እነዚህ “እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነዉ” ባዮች ጀግናዉ
ዘርዐይ ደረስ ጣሊያኖችን በራሳቸዉ አደባባዮች አንገታቸዉን በጎራዴ የቀላዉ ለዬትኛዉ ባንዲራ እንደሆነ ያዉቃሉ? እነ አብዲሳ አጋ፤
በላይ ዘለቀ፤ ባልቻ አባ ነብሶና እልፍ አዕላፋት የኢትዮጵያ ልጆች ምትክ የሌላትን ህይወታቸዉን የሰጡት ለዬትኛዉ ባንዲራ አንደሆነ
ያዉቃሉ?
እነዚህ ወያኔ አዲስ አበባ ዉስጥ የገዛ ወገኖቻዉን ሲያስርና ሲገድል አሜን ብለዉ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ሠላማዊ ሠልፍ የሚወጡ
የለየላቸዉ ከሃዲዎች ባንዲራ አዲስ መንግስት በመጣ ቁጥር እንደ ፖሊሲና እንደ ካቢኔ ሚኒስቴር የማይቀያየር ቋሚ የአገር ማንነትና
የትዉልድ ትስስር መታወቂያ መሆኑን ሊገነዙ ይገባል። ባንዲራ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሊቀየር ይችላል ብለን ብናስብ እንኳን ምን
አይነት ሰዎች ብንሆን ነዉ ባንዲራን የመሰለ ህዝብና አገር ማስተሳሰሪያ ማተብ ኢትዮጵያንና ታሪኳን ከልቡ ለሚጠላዉ መለስ ዜናዊና
የትግራይ ሪፓብሊክ ካላቋቋምኩ ብሎ ይታገል ለነበረዉ ለከሃዲዉ ስብሀት ነጋ የምንተዉላቸዉ? ደግሞም እነዚህ ምናምንቴዎች
አንደሚሉት ባንዲራችን ላይ ባዕድ አካል ሆኖ የተለጠፈዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለምዶ “ባላ አምባሻዉ” እያለ የሚጠራዉ የወያኔ
ጨርቅ እዉነትም ኢትዮጵያ ዉስጥ የብሄር ብሄረሰቦችን እኩልነት አረጋግጦ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አገራችን በየቀኑ ብሄር ብሄረሰቦች
ዉጣልኝ አልወጣም እየተባባሉ የሚተላለቁባት አገር አትሆንም ነበር። አባቶቻችን የሞቱት ለአረንጓዴ፤ ብጫና ቀይ ባንዲራ ነዉ፤
እኛም ዛሬ በየተሰደድንበት አገር አገሬን እያሰኘ የሚያስጮኸን ይሄዉ አረንጓዴ፤ ብጫ ቀይ ባንዲራችን ነዉ። አገር ቤት ያለዉ
ኢትዮጵያዊም አንዱን “ባላአምባሻዉ” ሌላዉን ደግሞ ባንድራዬ እያለ የሚጠራዉ ይህንኑ አረንጓዴ፤ ብጫና ቀይ ባንዲራዉን ነዉ።
በአንዲት አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ እነሱም እኛም ለየቅላችን የኛ የምንለዉ ባንዲራ ሊኖር በፍጹም አይችልም። ይልቅ ወያኔዎች
ሲጠፉ እነሱ ይዘዉብን የመጡት ኮተቶ ሁሉ አብሯቸዉ መጥፋቱ አይቀርምና ዛሬ “ባንዲራችን ተደፈረ” ብላችሁ የምታቅራሩ እዉሮች
ነገ ከወያኔ በጸዳችዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ጭራሽ ባንዲራ ላይኖራችሁ ይችላልና መጀመሪያ ከራሳችሁ ጋር ቀጥሎም ከአገራችሁ
ከኢትዮጵያ ጋር እንድትታረቁ አጥብቄ እማጸናችኋለሁ።
የወያኔን ቂልነትና ባዶነት በሰብኩ ቁጥር ትዝ የምትለኝ አንዲት ቀልድ ብጤ አለችና እስኪ ለፈገግታ ትሆናለችና አዳምጡኝ። ሁለት
አመት የፈጀዉ የኤርትራና የኢትዮጵያ አላስፈላጊ ጦርነት እንዳለቀ በጦርነቱ ወቅት ስንቅና ትጥቅ በማመላለስ ትልቅ ዉለታ የዋለች
ኣንዲት አህያ ጦርነቱ አብቅቶ የድል በዐል ሲከበር መስቀል አደባባይ ተጋብዛ መለስ ዜናዊ ፊት ትቀርባለች፤ በቋንቋ ይግባቡ ነበርና
መለስ ጎንበስ ብሎ በጆሮዋ አንድ ነገር ሹክ ሲላት አህይት በደስታ እየፈነጠዘች አደባባዩን መዞር ጀመረች። በልማታዊ አህይት ዝላይናፍንጠዛ ግራ የተጋቡት የወያኔ ጋዜጠኞች ዜና ያገኙ መስሏቸዉ “ታላቁ መሪ” ምን አለሽ ብለዉ አህይትን ጠየቋት። የዕድሜ ልክ
የህወሓት አባል ሆነሻል ተብያለሁ ብላ አህይት ዝላይዋንና ፍንጠዛዋን ቀጠለች።
ትናንት እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ የወያኔን ጭፍጨፋ፤ እስርና በዘር መድሎ የተጨማለቀ ስርዐት አበጀህ ቀጥልበት ብለዉ አደባባይ
የወጡ ጥቂት ህሊና ቢሶችና እነሱን አመስግኖ የነጻነት አርበኞችን “ዱሪዬዎች” ብሎ የዘለፈዉ የአድር ባዮች ሁሉ አድርባይ የሆነዉ
ግርማ ብሩ ከዚያች ባድመ ላይ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ካመላለሰችዉ ጎበዝ አህያ የሚለዩበት መንገድ ቢኖር አህያዋ ማሰብ ስለማትችል
አለማሰቧ እነሱ ግን ማሰብ እየቻሉ አለማሰባቸዉ ብቻ ነዉ። በተረፈ እነሱም አህያዋም የወያኔ አባልነታቸዉ ያስደስታቸዋል፤
ምክንያቱም ሁለቱም አያስቡም። መቼም የገዛ ወንድሙና እህቱ ሲታሰሩ፤ ሲደበደቡና ሲገደሉ አሜን ብሎ ተቀብሎ ነብሰ ገዳዮችን
ደግፎ ሰላማዊ ሠልፍ የሚሰለፍ የሰዉ ዘር ያለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ መሆን አለበት። ለዚያዉም በወያኔ ዘመን ብቻ!
እነዚህን ሆዳሞች ደግሜ ደጋግሜ እዉሮች እያልኩ የምጠራቸዉ አለምክንያት አይደለም። በእርግጥም ስለማያዩ ነዉ። ባለፈዉ ወር
አዚህ አሜሪካ ሚዙሪ ግዛት ፈርግሰን የሚባል ከተማ ዉስጥ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች መሳሪያቸዉን ሰላማዊ ሰልፈኛዉ ላይ
ስላዞሩ (ልብ በሉ ስላዞሩ ነዉ ያልኩት እንጂ ስለተኮሱ አላለኩም እነሱም አላደረጉትም) የአሜሪካ ህዝብ፤ መሪዎችና የህዝብ ተወካዮች
ምን ያህል እንደተንጫጩ ሁላችንም ተመልክተናል። እነዚያ እዉሮች ያልኳቸዉ ወንድሞቻችንም እኛ የተመለከትነዉን ተመልክተዉት
ይሆናል፤ ግን እነሱ የአዕምሮ እዉራን ናቸዉና ስዕሉን ብቻ ነዉ እንጂ ቁም ነገሩን አላዩትም። ስለዚህም ነዉ የነሱ ድፕሎማት ተብዬዉ
ድንጋይ ራስ (ርዕስ እምኒ) አዲስ አበባ ዉስጥ ያለ መስሎት ሠላማዊ ሠልፈኛ ለመግደል ደጋግሞ ሲተኩስ አበጀህ ብለዉ ሠላማዊ
ሠልፍ የወጡለት። እግዚአብሄር ከዚህ አይነቱ የአዕምሮ እዉርነት ያድነን! እባካችሁ አሁንም አሜን በሉ። እኔ እያረረ የሚስቅ ማሽላ
ብቻ ይመስለኝ ነበር . . . . ለካስ የገዛ ወገኖቹ ሲገደሉ ደስ ብሎት የሚስቅ ሰዉም አለ። አቤት እግዚኦ!!!!
ሌላዉ የገረመኝ ነገር ቢኖር እነዚህ የአዕምሮ እዉራን ትናንት ረፋዱ ላይ ለአሜሪካዉ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ በጻፉት ደብዳቤ
ግንቦት 7 ያ እንቅልፋም ፓርላማቸዉ “ሽብርተኛ” ብሎ የፈረጀዉ ድርጀት ነዉና ምነዉ ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ብለዉ ኬሪን
መወትወታቸዉ ነዉ። ኬሪ እንደነሱ ጨካኝና አምባገነን መሪዎች የማይወደዉንና የሚጠላዉን ሁሉ አይንህ አላማረኝም እያለ ማሰር
የሚችል መስሏቸዋል። እነዚህ ሆዳቸዉ ልባቸዉን የሸፈነ ከሃዲዎች አይገባቸዉም አንጂ የነሱን “ግንቦት ሰባቶችን” እሰሩልን ብሎ ጥያቄ
እንኳን ኬሪ የአለማችን ሀይለኛዉ መሪ አባማም ማስተናገድ አይችልም። እኛስ ብንሆን የምንታገላቸዉ ለዚሁ ነዉኮ - ኢትዮጵያን
የሚመራ ሁሉ ሀሳባችን ከሀሳቡ በተጋጨ ቁጥር አንዳያስረንና እንዳይደገድለን። እኔኮ ምን ይሻለኛል . . . . በአንድ በኩል
ኢትዮጵያዉያን የወገኖቻቸዉን መገደል ተቃዉመዉ ሠላማዊ ሠልፍ ሲወጡ የወያኔዉ ተላላኪ ግርማ ብሩ የኤርትራን መንግስት
ይከስሳል፤ የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ የግርማ ብሩ ተላላኪዎች ደግሞ (የተላላኪ ተላላኪ ማለት ነዉ) ግንቦት ሰባት የሚረዳዉ
በኤርትራ መንግስት ነዉና ስጋታችንን እዩልን እያሉ ኬሪን ይለማመጡታል። መቼም አዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም ነዉና የወያኔ
ደጋፊዎች አይገባቸዉም አንጂ ለሻዕቢያ ጎንበስ ቀና እያሉና የሻዕቢያን መሪዎች እንደ ታቦት እየተሳለሙ ለዚህ ዛሬ ላሉበት ደረጃ የበቁት
የወያኔ መሪዎች ናቸዉኮ። ዛሬ በባነኑ ቁጥር አንዴ ግንቦት ሰባት አንዴ ሻዕቢያ እያሉ ዛር እንደያዘዉ ሰዉ የሚያጓሩትም ተደምስሰዉ
ከታሪክ ምዕራፍ የሚፋቁት በዚሁ እንደ ህጻን ልጅ እጃቸዉን ይዞ ለታሪክ ባበቃቸዉ በሻዕቢያ በኩል መሆኑን በሚገባ ስለሚያዉቁት
ብቻ ነዉ። ምድረ የወያኔ አጎብጋቢዎች ዛሬ እቅጩን ልንገራችሁ፤ ወደዳችሁም ጠላችሁ ይህ “ልማታዊ” ብላችሁ የምትጠሩት ነብሰ
ገዳይ አገዛዝ ይደመሰሳል- ስጋታችሁ ትክክለኛ ስጋት ነዉ። ግን ከዚህ ስጋት የሚያድናችሁ ኬሪ ሳይሆን የራሳችሁ ሂሊና ብቻ ነዉና
ሳይዉል ሳያድር ዛሬዉኑ ኑና ከህዝብ ጎን ተሰለፉ፤ አለዚያ ዕድላችሁ ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ይሆናል። መቼም እንደኔዉ
የዚያች ምስኪን አገር ልጆች ናችሁና በተረት ብነግራችሁ ይገባችኋል ብዬ ነዉ እንጂ በእናንተና መወቀጥ በሚገባዉ ኑግ መካከል ምንም
ልዩነት የለም።
የዘረኞቹ የወያኔ መሪዎችና እንደ ችግኝ ኮትኩተዉ ያሳደጓቸዉ ቡችሎቻቸዉ አስቂኝ ታሪክ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ እነዚህ ጣምራ
ጉደኞች ብዙ ተነግሮ የማያልቅ ጉድ አላቸዉ። ወያኔዎች ጋዜጠኛ እያሰሩና ከአገር እንዲሰደድ እያደረጉ ተዉ ያላቸዉን ፀረ አገርና ፀረ
ልማት ይሉታል፤ በየሰላማዊ ሠልፉ ላይ ንጹህ ዜጎችን በጅምላ ሲጨፈጭፉ ምነዉ ያላቸዉን ደግሞ ሽብርተኛ ብለዉ ያስሩታል።
እነዚህ አረመኔዎች ይህንን የመሰለ ለጆሮ የሚቀፍ ወንጀል በህዝብና በአገር ላይ ፈጽመዉ ሰዎች በነጻነት ወደሚኖሩበት አገር ሰዉ
መስለዉ ሲመጡና ስንቃወማቸዉ ደግሞ እዚህ ዉጭ አገር ያስቀመጧቸዉ ተናካሽ ዉሾቻቸዉ “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የጎደላቸዉ
ብለዉ ይዘልፉናል። ለመሆኑ ለእነዚህ እንደ ዉሻ ቁራሽ ስጋ በተወረወረላቸዉ ቁጥር ለሚያላዝኑ ምናምንቴዎች ማነዉ ኢትዮጵያዊ
ጨዋነት እንደነሱ ነዉርን አሜን ብሎ መቀበል ብሎ የነገራቸዉ? ዜጎችን አንደ እንስሳ አየጎተቱ ገድለዉ አስከሬኑን በሟቹ ወንድም
እያስጎቱና ይህንን ነዉር በቪድዮ እየቀረጹ መሳቅና መሳለቅ ነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወይስ ይህንን ኔሮና ሂትለር ምን አደረጉ
የሚያሰኝ ጭካኔና አረመኔነት መቃወም ነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት? አዲስ አበባ ዉስጥና እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ተቃዋሚ
ኃይሎችን “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የጎደላቸዉ ብለዉ የዘለፉት ሬድዋን ሁሴንና ግርማ ብሩ የዉኃ ጠብታን ያክል ኢትዮጵያዊ ጨዋነት
በደማቸዉ ዉስጥ ቢኖር ኖሮ “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የኢትዮጵያዉያንን ህይወት በየአደባባዩ መቀማት አይደለምና እናከብራቸዉ ነበር
እንጂ በወጡና በገቡ ቁጥር ስማቸዉን እየጠራን ሌባና ከሃዲ እያልን አናሸማቅቃቸዉም ነበር። ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ስንታሰርና
ስንዋረድ እልል፤ ስንገደል ደግሞ አሜን ብለን እንደ በሬ አንገታችንን ለቢለዋ መስጠት ማለት አይደለም። ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ለወገንማዘን ነዉ፤ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወገን ሲጎዳና ሲጠቃ ከለላ መሆን ነዉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ዜጎች ሰቆቃ
ሲፈጸምባቸዉና ሲገደሉ ቆሞ ከመመልከት ይልቅ ወይም የገዳዮች ጠበቃ ከመሆን ባጭር ታጥቆ ነብሰ ገዳዮችንና የጭካኔ ምልክቶችን
ከአገር አናትና ከህዝብ ጀርባ ላይ ማስወገድ ነዉ - ወላድ በድባብ ትሂድ - ይህንን የሚያደርጉ የቁርጥ ቀን ልጆች እናት ኢትዮጵያ
ትናንንት ነበሯት፤ ዛሬ አሏት ነገም ይኖሯታል።
ebini23@yahoo.com
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
October 7, 2014

የጎዛምን ወረዳ የሰማያዊ አመራሮች በገዥው ፓርቲ አፈና እየተደረገባቸው መሆኑን አስታወቁ


  • 36
     
    Share
• ‹‹ወጣትና አርሶ አደሩ ‹‹ለምን ከሰማያዊ አባላት ጋር ታወራላችሁ እየተባለ ይታሰራል››
በምስራቅ ጎጃም ጎዛምን ወረዳ በአባሊባኖስ ቀበሌ የሰማያዊ ፓርቲ ቅርንጫፍ አመራሮችና አባላት፣ ‹‹ለምን የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆናችሁ?›› በሚል ከፍተኛ አፈና እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
የወረዳው የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ አክሊሉ ውቤ፣ ወጣት ምህረት እንየውና አቶ አንመው ይዘንጋው ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጹት የወረዳና የቀበሌ ባለስልጣናት የሰማያዊ አመራሮችን ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲወጡ እንደሚያስገድዷቸው ገልጸዋል፡፡
blue party
አቶ አንመው ይዘዘው የተባለውን የፓርቲው አባል መስከረም 14/2007 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ሚሊሻ ጥሩነህ መኮንን፣ ሚልሻ ሽታሁን ዘውዴ፣ ሚሊሻ አበባየሁ አባተ አስገድደው ወደ ቀበሌው ቢሮ በመውሰድ የቀበሌው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በልስቲ ትዛዜ ከሰማያዊ ፓርቲ ካልወጣ እንደሚገረፍ፣ ካልሆነ አገር ጥሎ መሰደድ እንዳለበት እንደዛቱበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
የቀበሌው ሊቀመንበር ‹‹ኢህአዴግ በ1997 ምርጫ ቢሸነፍም ሰራዊቱም፣ ወታደሩም፣ ፖሊሱም፣ የኛ ነው፣ እናንተ ወረቀትና እስክርቢቶ ይዛችሁ ልታሸንፉ አትችሉም፤ አሁንም እርምጃ እንወስድባችኋለን›› በሚል እንደዛቱበትና ከፓርቲው እንዲወጣ እንዳስጠነቀቁት ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ አቶ አክሊሉ ውቤ የተባሉትን ግለሰብ ‹‹ቢያርፍ ይረፍ ከፖለቲካ ድርጅት መውጣት አለበት፣ ካላረፈ ለህይወቱ ያሰጋዋል›› በሚል የቀበሌው ሹም የሆኑት አቶ ገነነ እና አቶ በልስቲ ትዕዛዜ እንደዛቱባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ምህረቱ ይታየው የተባለው ወጣትም ተመሳሳይ ማስፈራሪያ እንደደረሰበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል አቶ በልስቲ ትዕዛዜ፣ ኮማንደር አንተነህ ፈንታሁን፣ አቶ ተሻገር አዲሱ የተባሉት የቀበሌው ባለስልጣናት ‹‹ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለምን ታወራላችሁ፣ ለምን ከእነሱ ጋር ትቆማላችሁ›› በሚል በየዕለቱ ወጣቱንና አርሶ አደሩን እንደሚያስሩ የወረዳው የፓርቲው ቅርንጫፍ አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ አክለው ገልጸዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ገዥው ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በከፈተባቸው ቦታዎች ቢሮዎችን ለመዝጋት፣ ቢሮ ለመክፈት እየጣረ በሚገኝባቸው ቦታዎች ደግሞ አባላቱንና አመራሮቹ ከፓርቲው እንዲወጡ ጫና እያደረገ እንደሚገኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ጋጠ ወጡ ማን ነው?


የህወሃት ጉጅሌና ሎሌዎቹ መቼም ራሳቸውን የሚያይ አይንም መስታዎትም ያላቸው አይመስሉም። ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ነገሮች በአጠገባቸው የዘሩ የማይመስሉት ለዚህ ሳይሆን ይቀራል። ምናልባትም ብልግና፣ ጭካኔ፣ ግፍ፣ አውሪያዊ ስብእና፣ ወገን ካለህግ መግደልና ማዋረድ፣ የህዝብ ሃብት በጠራራ ጸሃይ መዝረፍ ለእነሱ የተፈቀደና የተሰጠ ጸጋ አድርገው ሳይቆጥሩት ይቀራሉ?
ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰለጠነና የዳበረ ስርዓት አከባበር በሰፈነበት ከተማ ውስጥ ባልታጠቁ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩሱና ሲያስተኩሱ በመዋላቸው ለደረሰባቸው ትዝብት የነውረኝነት ሀፍረት እንደማፈር ሰላማዊዎቹንና በሰላማዊ መንገድ እስከ ሲቪላዊ አልታዘዝም ባይነት መብት ያላቸውን ጠንቅቀው አወቀው የተንቀሳቀሱትን ዜጎች ጋጠ ወጥና ባለጌዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ትንሽ ሲቀዠብርባቸው ደግሞ ኦባማ ስላነጋገረን የቀኑ ተቃዋሚዎች፣ ይህ አልበቃ ሲል ደግሞ የሻእቢያ ተላላኪዎች ሲሉም ተደምጠዋል። ከአውሬነት ብዙ ያልተለዩት ደጋፊዎቻቸው ተኩሱን ሲያንጣጣ የነበረው የቀድሞ የስዩም መስፍን የግል አሽከርና ሹፌር የነበረው ወዲ ወይኒ ግደይ ስለተባረረ ንዴታቸውን ከአደባባይ እንኳን መደበቅ አልቻሉም። እናስ እዚህ ውስጥ ጋጠወጡ ማነው? ሀገሩን የሚያስተዳድርበትን አራዊታዊና ህግ አልባ ስርአት በሰለጠነ ህዝብ ሀገር በአደባባይ ለኤግዚብሽን የሚያቀርብ መደዴ ወይስ እስከ ሲቪል እምቢተኝነት ድረስ ሊደርስ የሚችል መብታቸውን ጥንቅቀው የሚያውቁና በግፍ ስርአት ለሚኖረው ወገናቸው ድምጽ ያሰሙ የህዝብ ልጆች?
በዘሩ ታማኝነት ተመርጦ ከስዩም መስፍን ሾፌርነት ውጪ ቅንጣት የዲፕሎማሲ እውቀት የሌለውን ደንቆሮ የዲፕሎማት ማእረግና ሽጉጥ አስታጥቆ ዋሽንግተን ከሚልክ መንግስት በላይ ጋጠወጥና አጉራ ዘለል ከየት ይገኛል።
እውነቱ ግን ወዲህ ነው ያለው። ቢያንስ በነጻው አለምየሚኖሩ የኢትዮጵያ ልጆች በሀገራቸውና በወገናቸው ላይ በሚደርሰው ስቃይ ውርደትና ግፍ ተንገፍግፈዋል። የወያኔ ሹማምንት ግፋቸውን እንዲያቆሙ ያሰሩዋቸውን እንዲፈቱና ሀገር ዝርፊያ እስኪያቆሙ ድረስ በገቡበት እየገባ ቁም ስቅላቸውን ማሳየትና ጋጠወጥና የነውረኛ ስርአት አገልጋዮች መሆናቸውን ማጋለጡን ይገፉበታል። በሰሩት ወንጀል አለምአቀፍ ፍርድቤቶች መድረክ ላይ እየጎተተ የሚያቀርብበት ጊዜም ሩቅ አይደለም።
የወጋ ይርሳ እንደሆነ እንጂ የተወጋ አይረሳም። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሰላማዊ ተቃዋሚውን ድርጅት አባል በብረት ሶዶማዊ ምግባር የፈጸሙትን ጋጠ ወጥ የወያኔ ተላላኪዎች ማን ይረሳል። በየቤቱና በየጎዳናው በዱላ የሚቀጠቀጡትና ደማቸውን ሲጎርፍ ያየናቸው አዛውንት ሙስሊም ወገኖቻችን ደም እንዴት እንረሳለን። ሬሳቸው እንኳን ክብር አጥቶ የጋጠወጥ ወያኔ መጫወቻ የሆኑትን የኦጋዴን ወገኖቻችንን ማን ይረሳል። ጋምቤላ ጫካ ውስጥ እንደደኑ ተጨፍጭፈው የተቆለሉትን አኙዋኮች ማን ይረሳል። ከየኖሩበት ቦታ በግፍ እየተፈናቀሉ የሚንከራተቱትን እና የሚሞቱትን አማሮች ማን ይረሳል። በቆራጥነት ብቻ በሰላም መንገድ እንታገላለን ብለው በተነሱ ወህኒ የተወረወሩትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የታሰሩትንና የተሰደዱትን ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች የምንረሳቸው ስንሞት ብቻ ነው። ከየጎረቤት ሀገሩ እየታፈኑ የሚሰቃዩትን እነ አንዳርጋቸውን እና ሌሎች የሞቱትን ማን ይረሳል።
ህዝባችንን ወደ ሰላማዊ አመጽም ሆነ ወታደራዊ አመጽ እየገፋው ያለው ይህ የወያኔ ባህሪ ነው።
ግንቦት 7 ከዚህ አራዊታዊ ስርአት ጋር ሆናችሁ በተለያየ ምክንያት በህዝባችሁ ስቃይ ላይ የምትተባበሩ ወገኖች ሁሉ በአገኛችሁት አጋጣሚ ከእዚህ እኩይ ስርአት ተግባራት ራሳችሁን እንድታወጡ፣ ከቻላችሁ በውስጥም ሆናችሁ ወገናችሁን ሳትበድሉ ትግሉን እንድትቀላቀሉ ይመክራል።
መላው ህዝባችን በያለህበት ራስህን በራስህ እያደራጀህ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎችን ጀምር። በመላው አለም ዙሪያ ተሰደህ የምትኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለወገንህ ለራስህም ትንሳኤ ተነስ!!
ትግላችን የመጨረሻውን መጀመሪያ እየተያያዘ ነው። የትልቅ ሀገርና ትልቅ ህዝብ ባለቤቶች ስለሆንን ከወያኔ ወሮበላ ጉጅሌ በበለጠ የሚገባን ህዝብ ነን!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!