ቀለል ባለ አማርኛ በወያኔና በጭፍራዎቹ አመለካከት የዘረኞችና የግብዞቹን የወያኔን መንግስት መቃወም ማልት
አምላክን እንደመስደብ አድርገው ይቆጥሩታል
ወያኔ ለኢትዮዽያና ለዜጎቿ ደንታ የሌለው ህዝቡን በመከፋፈል የጎጥና የሐይማኖት ጥላቻ በመስበክ ትውልዱን ራዕይ አልባ አድርጎ የሐገር ስሜት እንዳይኖረው በማድረግ እኔ ኦሮሞ እንጂ ኢትዮጵያዊነት አይገባኝም ጋንቤላዊ ካልሆነ ኢትዮጵያ ምንድን ነች አማራ ትግራይ ሀረሪ ጉራጌ እንጂ ኢትዮጵያ የምትሏት ምኔ ነች የሚል ትውልድ ማፍራት ና ውስጥ ለውስጥ በአገዛዙ እንደ
ፖሊሲ እየነደፈ ልዩነትን በማስፋፋት እርስ በርስ ከፍለው የነሱን ስርአት ለማራዘም ሲሞክሩ ማየት የተለመደ ሆኗል በተጨማሪም ካድሬዎቻቸው በደም የመጣ ስልጣን ነው አንዴት በምርጫ ብለው ይከራከራሉ ህዝቡ ነፃነቱን ተገፎ የሐገሪቱን
ሕዝብ በጎሣ በሐይማኖት እንዲጋጭ የተማረውንም ያልተማረውንም በጥቅማ ጥቅም ወይም በግዴታ የፓርቲው አባል በማድረግ
የተማረ ከሆነ ስራ ለማግኘት ወይም የስልጣን እርከን ለማሳደግ ያልተማረውን በኮንደሚኒየም ና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በማታለል ፍርድ ቤቶችና ሚድያዎችን መቶ በመቶ ለራሳቸው ጥቅም እንዲቆሙ ፓርላማውን እንደአሻንጉሊት በማድረግ
በሕዝቡ ላይ አንደፈለጉ የማንአለብኝነት ድርጊት መፈፀም ከጀመሩ አመታት ተቆጠሩ
እናም ነፃነት ከሌሎች የምንጠብቀው ወይም ማንንም ስጠን ብልን የማንጠይቀው ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለን ሐብታችን ነው ነፃነት የምንሻ ይቺን አገር እንደ ሐገር እንድትቀጥል የምንፈልግ አብዛኛው ለውጥ ፈላጊም የሚስማማበት ጉዳይ ቢኖር የችግሮቻችን መጠን ቢለያዩም ችግሩ ግን በዘር በጎሣ በፆታ በእድሜ ወዘተ ሳይል ችግሩ የእያንዳንዱን ቤት ማንኳኳቱ ነው በተልይም ደግሞ ፍትህ የተጠማው ነፃነቱን ተገፎ ተረግጦም ያለውን በየስርቤቱም የሚማቅቀውን ሐገሩን ጥሎም የሚስደደውንም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይህ ሁኔታ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው ብሎ ዘረኛውን የወያኔ መንግስት በአንድ ላይ ሆነን ልንታገለው ይገባል
እግዛብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ዳንኤል አምዶም
No comments:
Post a Comment