Saturday, April 13, 2013

የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! (በኢትዮ-ጀርመኒ ድረገጽ)


የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!!
(በኢትዮ-ጀርመኒ ድረገጽ)
እ.አ.አ በ1997 በጨረታ ወደ ግል ንብረትነት ተዛወረ የተባለው የኢትዮጵያውያን ሀብት የተሸጠው 172 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ሽያጩ
ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ሽያጩን ተከትሎ በርካቶች አርረዋል፤ ተቃጥለዋል። “ዋይ ዋይ ወርቃችን” ብለው አንብተዋል። ህዝብ የፈለገውን
ቢል ደንታ የሚሰጠው አካል ስለሌለ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኢትዮጵያ ህዝብ እጅ በአዋጅ ተነጠቀ።
ሽያጩን እውን ያደረገው የኢትዮጵያ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሀሰን
አሊ ሲሆኑ፣ የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ አሰፋ አብርሃ የኤጀንሲው ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ነበሩ። ሁለቱም ባለስልጣናት ዛሬ ሃላፊነት
ላይ የሉም። ስለ እውነትና ስለ አገር ሲሉ የሚያውቁትን ለመተንፈስ እስከዛሬ ቢጠበቁም ያሉት ነገር የለም። ሃሰን አሊ ሲኮበልሉ፣ አቶ
አሰፋ አብርሃ ከወንድማቸው ጋር በሙስና ተወንጅለው የወህኒ ቤት ጊዜያቸውን አጠናቀው እየኖሩ ነው።
ምዕራብ ሃረርጌ አሰበ ተፈሪ መምህር የነበሩትና ኢህአዴግን መንገድ ላይ የተቀላቀሉት ሀሰን አሊ ካገር መኮብለላቸውን ተከትሎ የተለያዩ
መረጃዎች ይወጡ ነበር፡፡ በርካቶች ጉዳዩን ከኦነግ ጋር ቢያያይዙትም “ካገር ውጡ ተብለው፣ ሀብትና ንብረት ተዘጋጅቶላቸው
ኮብልለዋል” የሚል መረጃ ለባለስልጣናትና ለባለሃብቱ ቅርብ ነን ከሚሉ ወገኖች እንሰማ ነበር። በወቅቱ ኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ
በነበረኝ ሃላፊነት ሳቢያ ከሰማኋቸው መረጃዎች ውስጥ ሃሰን አሊ “ውጡ” ተብለው እንደ ኮበለሉ የሰማሁት መረጃ ካለኝ ሃላፊነት ጋር
ተዳምሮ እንዳጣራው ወሰንኩና ጊዜ ሰጥቼ አነፈንፍ ገባሁ።
የሌሎችን ባላውቅም እንደ ኦሮሞነቴ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ውድ ንብረት ለሼኽ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ መሸጡ ሁሌም
ያንገበግበኛል። ሽያጩን አስመልክቶ የተለያዩ ጽሁፎች ቢወጡም እኔ ካሰባሰብኩት መረጃና እውነት ጋር የሚመጣጠን መስሎ ስላልታየኝ
በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለመተንፈስ ወሰንኩ።
ሼኽ መሐመድ አላሙዲና ሃሰን አሊ እንዴት ተዋወቁ?
ሼኽ መሀመድ አላሙዲና ሀሰን አሊን እንዳስተዋወቃቸው የነገረኝን ሰው ባንድ አጋጣሚ የማወቅ እድል አጋጥሞኝ ነበር። ተግባሩ ብዙም
ደስ ስለማያሰኝ ፊት እነሳው ነበር፡፡ ባለስልጣናትን በገንዘብ እየደለለ ሲሰርቅ ብዙ ጊዜ ስለማውቅ አልወደውም ነበር። የራሱን ትልቅነት
ለመግለጽ ድንገት ቢሮዬ በመጣበት ወቅት የነገረኝ ፍንጭ ትዝ ሲለኝ ላገኘው ወሰንኩ። ይህ ሰው ባለኝ ሃላፊነት እንደፈለገኝ ላገኘው
ስለምችል፣ እሱም ለሚሰራው ድለላና አየር ባየር ንግድ እኔ ከፈለኩት ቅር ስለማይለው ፊት ነስቼው ያቋረጥኩትን ግንኙነት እንደገና
መቀጠል ብቸኛ አማራጬ ሆነ፡፡ይህን ሰው ከተጠቀሙበት በኋላ ወርውረውት በነበረበት ወቅት ላይ ስላገኘሁት የፈለኩትን ለማግኘት
አጋጣሚው ተመቻቸልኝ፡፡
ቀደም ሲል ሃሰን አሊን ያውቃቸው እንደነበር፣ አብረው ሃድራ እንደሚያሞቁ፣ የፈለገውን ነገር ማድረግ ከፈለገ ሃድራው በሚሞቅበት
ወቅት እዛው በሙቀት እንደሚያከናውኑ አውግቶኛል። ለዚህ ጽሁፍ ስለማይጠቅም እንጂ በርካታ ታላላቅ ጉዳዮች ቢሮ ውስጥ ሳይሆን
በተፈረሸ መደብ ላይ እንደሚከናወን በስፋት ስም እየጠቀሰ ነግሮኛል። እንግዲህ ይህ ሰው የ“ባለሃብቱ” ወዳጅ ነበር። ለዚያውም
የመጀመሪያ!
በዚሁ ሽርክናቸው ሰውየው ሃሰን አሊን መተዋወቅ እንደሚፈልጉ ባሳወቁት መሰረት ሃሰን አሊን በመያዝ ሳር ቤት አካባቢ አገናኛቸው።
ባለሃብቱ በወቅቱ ብዙም የሚያውቃቸው ባልነበረበት ወቅት ሃሰን አሊን አስቀድመው ተወዳጁ። በመኖሪያ ቤት ሃድራ ላይ የተመሰረተው
ወዳጅነት ጠበቀ። በኦሮሚያ በኩል አድርገው ዋናውን ሳሎን ወረሱ።
ሀሰን አሊ ከኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነታቸው ለቀው ስደትን ለምን መረጡ?
አሰበ ተፈሪ የሁለተኛ ደረጃ መምህር እያሉ ወያኔ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ በረዣዥም በአለም የምግብ ድርጅት ሽንጣም የጭነት
ተሽከርካሪዎች በሸራ ተሸፍነው ቀለሃ ሳያባክኑ ወደ ሃረርና ድሬዳዋ ሲተሙ ቆቦ የምትባል የመስመር ከተማ ላይ ሆኜ የመከታተሉ እድል
ነበረኝ፡፡ ወያኔ የሀረርንና የድሬዳዋን ከተማ ለመያዝ ስትሮጥ አሰበ ተፈሪ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከአቶ ሀሰን አሊ ጋር
ተገናኙ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ሀሰን አሊ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኑ፡፡ አስተማሪው ፕሬዚዳንት በስልጣን በቆዩባቸው ጊዜያት ከሚታሙባቸው
ከፍተኛ ሙስናዎች መካከል፣ ባሌ ውስጥ ተከስቶ በነበረው የዋና ከተማነት ጥያቄ ተከትሎ የተቀበሉት ብር ነው። የባሌ ሮቤ ነጋዴዎች ሮቤ
በዋና ከተማነት እንድትቀጥል ያሰባሰቡትን አንድ ሻንጣ ብር በስጦታ አቅርበውላቸው ነበር። ያረፉበት ቤት ድረስ የቀረበላቸው ስጦታ
ሮቤን በዋና ከተማነት ጸንታ እንድትቆይ ወሰነ። ገንዘብ ተናገረ። ከአገር የመኮብለላቸው ጉዳይ ከዚሁ ጋር ተያያዥ ነው ቢባልም
በፖለቲካው መስመር ደግሞ ኦነግ ናቸው የሚል ሰፊ ሃሜት ነበረባቸው። እኔ ባካሄድኩት ማጣራትና በሰበሰብኩት መረጃ መሰረት ቀደምሲል የጠቀስኩዋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው፣ አቶ ሀሰን አሊ በለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ በሙስና መጨመላለቃቸው ለመኮብለላቸው ዋናው
ምክንያት ስለመሆኑ ሚዛን የደፋ ምርመራ አካሂጃለሁ፡፡
የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን ለመሸጥ ወጥቶ በነበረው ጨረታ የተለያዩ ኩባንያዎች ቢሳተፉም ሼክ መሀመድ አላሙዲ ያሸነፉበት ድራማና
የሀሰን አሊ ወደ አሜሪካ መኮብለል በተመለከተ ያሰባሰብኩትን መረጃ ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ ለራሴና ለወዳጆቼ ደህንነት
ስል ስም ከመጥቀስ ግን እቆጠባለሁ፡፡
ሃሰን አሊ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የሚመሩት የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የለገደንቢን ወርቅ ሽያጭ ጨረታ ከማስፈጸሙ በፊት ለገደንቢን
አስመልክቶ ከፍተኛ የማባበል ስራ ተሰርቷል። በየጊዜው ሲደረጉ የነበሩ ማባበሎችን ይከታተል የነበረው የመረጃ መነሻ እንዳስረዳኝ
ለገደንቢ እንደ መስቀል ሰንጋ ጠልፎ የተበለተው አስቀድሞ ነው። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃቶች ከኢትዮጵያ ኪስ የሚወስዱትን ንብረት
ህጋዊ ለማስመሰል ያቋቋሙት ይህ ኤጀንሲ በቁንጮ አመራሩ መመሪያ ሰጪነት ባካሄደው ጨረታ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችም
ተሳትፈው ነበር።
አንድ ቀን እዛው ቤት ውስጥ እንደተለመደው ሃድራው እየሞቀ በጨረታው የተሳተፈ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ የተሻለ ገንዘብ ማስገባቱ
ባለሃብቱ ጆሮ ይደርሳል፡፡ ኩባንያው ያስገባው ገንዘብ መጠን ይገለጽላቸዋል፡፡ መጀመሪያ ያስገቡት ሰነድ ተቀይሮ ሌላ ሰነድ እንዲያስገቡ
በተነገራቸው መሰረት አዲስ ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ድራማ ለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኢትዮጵያ ህዝብ ሀብትነት ወደ ሼክ
መሀመድ አላሙዲ ንብረትነት በ1997 ለስምንት ዓመት ተዛወረ፡፡
በጉጂ ዞን ሻኪሶ ወረዳ ሳካሮ በተባለው ቦታ የተሰራው ይህ አዲስ 4ኪሜ የዋሻ መንገድ ቀጭን ረጅም ጥቅልል ብረት ከምድር በታች እስከ
70ሜትር ይዘልቃል፡፡ (ፎቶ፡ ስቬን ዱሜሌ)
በዓመት 3.5 ቶን ወርቅ በአማካይ ሲያመርት ቆይቶ ምርቱን በማሳደግ በአሁኑ ሰዓት ከ4.0 ቶን በላይ ማሳደጉን ይፋ ያደረገው ሚድሮክ
ጎልድ በዚህ ዓይነት አሳፋሪ ድራማ ወደ ግል ይዞታነት ከተዛወረ በኋላ ሀሰን አሊ አገር ጥለው እንዲወጡ ተወሰነባቸው፡፡ የሽያጩ ድራማ
ደብዛ መጥፋት ስላለበት ሀሰን አሊ በኦነግ ስም ካገር እንዲኮበልሉ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ ከተጠናቀቀ በኋላ አሜሪካ ለስራ በሚል ሰበብ
እንዲሄዱ ተደርጎ በዛው ቀሩ፡፡ አሜሪካን አገር ሱፐር ማርኬትና ነዳጅ ማደያ ተገዝቶላቸው ስለነበር ከነቤተሰቦቻቸው ወደ ንግድ ዓለም
መግባታቸው ተሰማ። አሜሪካ ተገኝቼ ማጣራት ባልችልም አደራውን እዚያው ለምትኖሩ ታጣሩትና ትጎለጉሉት ዘንድ አሳስባለሁ። ምንም
በሉ ምን የኢትዮጵያው “ለገደንቢ” የግለሰብ “ሚድሮክ” የሆነው በተፈረሸ ፍራሽ ላይ ነው – በምርቃና!!
ከ2005 በኋላ ለገደንቢ ወርቅ የማን ይሆናል?
ሚድሮክ ጎልድ ይፋ እንዳደረገው ሃያ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ዘመናዊ መሳሪያ ተገዝቶ ወርቅ የማምረቱ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
በማስፋፊያ በተከለሉ ቦታዎች ላይ ከ4.7 እስከ 6.52 ቶን የሚደርስ ወርቅ በዓመት ለማምረት የተጀመረው ስራ ውጤት ማሳየት ጀምሯል፡
፡ ስለማስፋፊያ ስራው አዲስ ስምምነት መንግስትም ሆነ ማዕድን ሚኒስቴር ያሉት ነገር የለም፡፡ ሚድሮክ ከኮንትራት ዘመኑ (2005)
በማለፍ እስከ 2020 በያዘው ዕቅድ ከ70 ቶን በላይ ወርቅ ለገበያ በማቅረብ ለመሸጥ ማቀዱን በመንግስት ሚዲያ ይፋ አድርጓል፡፡ 1.6
ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ እንደሚያገኝም አፉን ሞልቶ ተናግሯል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አገር ምን ታገኛለች በሚለው ጉዳይ ላይ ጥያቄ
ማንሳት ሃጢያት ነው፡፡ያስገድላል፣ ያሳስራል፣ ያስደበድባል …
ለመሆኑ ከ1997 ለስምንት ዓመት ኮንትራት የተሰጠው ለገደንቢ ወርቅ እስካሁን በአላሙዲ እጅ እንዲቆይ የተደረገበት ውልና የውሉ
ዝርዝር ለምን ምስጢር ሆነ? በምን ዓይነት አዲስ ውልና ክፍያ ተጨማሪ ቦታ ተከለለ? በምን ያህል ዶላር የሽያጭ ውልና መግባቢያ
ባለሃብቱ ወርቁን እንዲዝቁ ተወሰነ? ማዕድን ሚኒስቴር አለሁ ቢል ወይም ራሱ ሚድሮክ በግልጽ በድረ ገጹ ቢያሰፍረው ቢያንስ ቂማችን
ይቀንስ ነበር።
ለወትሮውም በብድር እንደተሸጠ የሚነገርለት ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ብድሩ ሙሉ በሙሉ መከፈሉ በይፋ ባይገለጽም ሀብቷን በድራማ
ጨረታ በብድር የሸጠችው ኢትዮጵያና ህዝቧ ከሃብታቸው ድርሻቸው 2% ብቻ ነው፡፡ ከሮያሊቲ ክፍያ ማግኘት የሚገባትን ሚጢጢ
ገንዘብ እንኳን ባግባቡና በወቅቱ አታገኝም፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር አቶ ሱፍያን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሃላፊዎችን
ሰብስበው ሲያነጋግሩ ‘’ለመሆኑ ሚድሮክ ጎልድ ላይ ያለን ድርሻ ስንት ነው? ማስገባት ያለባቸውን ገንዘብስ ይከፍላሉ?” በማለት
መጠየቃቸው በወርቅ ማዕድኑ ዙሪያ ያለውን እንቆቅልሽ ወለል አድርጎ እንደሚያሳይ ስብሰባው ላይ የተሳተፉ በወቅቱ የተናገሩት ነው።
በቀኝ በኩል የሚታየው አርቲፊሻልና በኬሚካል የተፈጠረ ሐይቅ ሲሆን በግራ ደግሞ ያለው የተፈጥሮ ሐይቅ ነው፡፡ አርቴፊሻሉ ሐይቅ
ቀለም የተከሰተው በቁፋሮ የሚወጣውን ወርቅ ለማጣራት ጥቅም ላይ በሚውለው ኬሚካል አማካኝነት ነው፡፡ (ፎቶ ስቬን ዱሜሌ)
ይህ ብቻ አይደለም ከለገደንቢ ከርስ የሚጣራው የኢትዮጵያ ደም /ወርቅ/ ወደገበያ ሲሄድ ቁጥጥር አለመደረጉ ሌላው አስገራሚ ድራማ
ነው፡፡ አገርና ህዝብ እመራለሁ የሚለው ኢህአዴግ ሚድሮክ በቀጠራቸው ባንዳዎች አማካይነት ወርቁን በሉፍትሐንሳ አውሮፕላን ብቻየሚያመላልሱት ለምንድነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ የለውም፡፡ በሌላ አነጋገር አገር የሚገባትን የሽያጥ ታክስም ወደ ውጪ በሚላከው
መጠን መሰረት እየተሰላ አይከፈልም። በእንዲህ ዓይነት መልኩ በአገራችን ኢኮኖሚና ህልውና ላይ ይጋለብበታል፡፡ ሚድሮክ ወርቅ አንዱ
ማሳያ እንጂ ማጠቃለያ ግን አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወርቁን ወደሚላክበት ስፍራ በማመላለስ የትራንስፖርት ንግድ ለመነገድ ጠይቆ “አይሆንም” ነው የተባለው
ለምን? ኢህአዴግና ባለስልጣናቱ ለዚህም መልስ የላቸውም፡፡ አገር ወዳዶች ግን መልሱን ያውቁታል፡፡ ልባቸው እየደማ፣ ኅሊናቸው
እየቆሰለ፣አገራቸው ስትታረድ የሚመለከቱ ወገኖች ለምንና እንዴት ብለው ሲጠይቁ አሁንም ይገደላሉ፣ይታሰራሉ፣ ይገረፋሉ፣ ህዝብን
በማነሳሳትና በሽብርተኛነት ወንጀል ይከሳሳሉ፡፡ እስከ ህልፈታቸው ወህኒ እንዲጣሉ የተሸጡ ወንድሞቻቸው ይፈርዱባቸዋል፡፡ በሃገረ
ማሪያምና በቡሌ ሆራ ወረዳ የሆነው ይኸው ነው!
ሚድሮክ ወርቅ እያግበሰበሰ ያለው ሃብት ስለጣፈጠው በግልጽ ባልተቀመጠ ውል ግዛቱን እያስፋፋ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ሲያፈናቅል
የቡሌ ሆራና የሀገረ ማሪያም ነዋሪዎች ከልማቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና ባካባቢው ላይ እየደረሰ ያለው ብክለት ጉዳት እያደረሰባቸው
መሆኑን ገልጸው በመቃወማቸው በሽብርተኛነት ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ጥር 5 ቀን 2002 በሻሸመኔ ምድብ ችሎት በሽብርተኛነት ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው የአካባቢው ተወላጆች ላይ የደረሰውን መከራ
የሰብአዊ መብት ጉባኤ 34ኛ መደበኛ ጉባኤ ህዳር 8 ቀን 2003 ዓም ስም በመዘርዘር ይፋ አድረጓል፡፡ ከሳምንት በላይ ትምህርት ተቋርጦ
በርካታ ተማሪዎችና ነዋሪዎችም ታስረው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
የፌዴራሉን እንተወውና ኦሮሚያና ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በምን ምክንያት ተጣሉ? በወቅቱ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና ኦህዴድ፣ ወደፊት
የባለሃብቱና የኦሮሚያ እጣ ፈንታ ምን ይመስላል? በሚሉት ርዕሶች ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባ ይዤ እመለሳለሁ። በመግቢያዬ እንዳልኩት ዋይ
ዋይ ወርቃችን!!
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
April 11, 2013

በህዝብና በሀገር ላይ ቀልድ የለም (በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ) በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ የተሰጠ የተቃዉሞ መግለጫ


በህዝብና በሀገር ላይ ቀልድ የለም (በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ)


በህዝብና በሀገር ላይ ቀልድ የለም (በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ)

በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ የተሰጠ የተቃዉሞ መግለጫ
ህዝባችን መስዋእትነት ከፍሎና ተንከባክቦ ባቆያትና እትብቱ በተቀበረባት ምድር የመኖር ነፃነቱን ከተነፈገ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን በዘርና በቋንቋ እየተመነዘረ በገዛ ሀገሩ እንደ ባይታዋር ተቆጥሮ ከተባረረና ሜዳ ላይ ከተጣለ፡- ሀገር አለኝ ማለቱ ትርጉሙ ምንድን ነው?። የውጭ ባለሃብቶች ለም መሬታችንን ይዘው ኰርተውና ተንደላቅቀው ሲያርሱና ሲያለሙ በአንፃሩ የሀገሩን ባለቤት የሆነውን ህዝብ የበይ ተመልካችና ተመፅዋች ሆኖ እየተንከራተተ የሚኖረው እስከ መቼ ይሆን?። ይህ ዓይነቱ አሳፋሪ እርምጃ እየተደጋገመ ከሄደስ የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ምን ሊሆን ይችላል? ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ስርዓተ አልበኝነት ነግሶ ህዝቡ አቤት የሚልበት የፍትሕ ቦታ አጥቶ ሲተራመስ ስናይ ለመሆኑ በሀሪቱ ላይ መንግስት አለ ወይ? የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ አድርጎናል።
ሰሞኑን በቤንሻንጉል አካባቢ በሽዎች በሚቆጠሩት የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት በተለያዩ ሚዲያችና እንዲሁም ሜዳ ላይ ከወደቁት ተፈናቃዮች ከራሳቸው አንደበት ስንሰማ እጅጉን አሳዝኖናል። ይህ አረሜናዊ ድርጊት ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል መንግስት ቀርቶ በባዕዳን ወረራ ጊዜም ቢሆን ያልተፈፀመና በኢትዮጵያ የመንግስታት ታሪክም ታይቶ የማይታወቅ አስነዋሪ ተግባር መሆኑን አሳይቶናል። ከዚህም አልፎ የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ደግሞ ድርጊቱን መፈፀሙ ብቻ ሳይሆን የህወሓት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት እንደ ለመዱት ሁሉ ወንጀሉን ለመሸፋፈን ሲሉ የሰጡትን መግለጫ በህዝቡ ህይወት ላይ መቀለድና ማፌዝ መሆኑን በይፋ አሳይቶናል። ሰለሆነም ፡-
1. የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው አረሜናዊ ድርጊት ኢትዮጵያዊነት ስነ ምግባር ያልተከተለ፣ የህዝባችን ሕገ መንግስታዊና ዜግነታዊ መብት የሚጥስ፣ ዓለም አቀፋዊ የሰብኣዊ ፍጡር አያያዝ የሚፃረር የወንጀል ድርጊት በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። በዚሁ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሳተፉ ሰዎችም በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።
2. “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ነውና የዜጎች ህይወት የዶሮን ያህል ክብር ሳትሰጡ ሀገርንና ህዝብን በፍርፋሪ፣ በስልጣንና በጊዚያዊ ጥቅም በመለወጥና እንዲሁም የህዝቡን ትዕግስት፣ ጨዋነትና ዝምታ እንደ ሞኝነት በመቁጠር በየዋሁ ህዝባችን ላይ ወንጀል እየፈፀማችሁ የምትገኙ የስርዓቱን ካድሬዎችና ደጋፊዎች ሁሉ ትዕግስት ገደብ አለውና የዛሬ ዝምታ የነገ እሳተ ጎሞራ እንደሚሆን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ድርጊት እጃችሁን እንድታነሱ እንጠይቃለን።
3. በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የወንጀል ድርጊት እንደ ተለመደው “የባሰ አታምጣ” ተብሎ በማድበስበስ፣ በዝምታና በማዳፈን የሚታለፍ ሳይሆን ጉዳዩን ገለልተኛ አካል እቦታው ድረስ ሂዶ እንዲያጠራ ዓለም አቀፍ ሰብኣዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
4. በሀገር ውስጥም ሆነ በዲያስፓራ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሁሉ በመካከላችን ሊኖር የሚችለው የአመለካከት ልዩነት እንደ ባላንጣነት ሳይሆን እንደ ውበት ተቀብለን ለጋራ ችግር በጋራ መቆም ጊዜው የግድ ይለናል። ካልሆነ ግን በተናጠል ተበታትነን በየተራ እየተደቆስን መኖር የማይቀር ነው። ስለዚህ “ጎርፍ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንዲሉ የህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች ቀለማቸውን እየቀያየሩ በልማት ስም የህልም እንጀራ ለማብላትና መርዝ በማር ጠቅልለው ለማጉረስ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተው ሲንቀሳቀሱ እኛ ደግሞ የህልውናችን ሞሶሶና ዋስትና በፍቅር፣ በመከባበር፣ በመደማመጥና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ አንድነት በተግባር ማሳየት ለነገ የማይባል የያንዳንዳችን አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን በፅኑ እናምናለን።
5. ኢሕአዴግ በተለይም ዕድሜ ልኩን ያንተ ነፃ አውጪ ነኝ እያለ በትግራይ ህዝብ ስምና ደም ሲነግድ የኖረው ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) በተለመደው ባህሪው በወንድሞቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ጭካኔ የተሞላበት አረሜናዊ ድርጊት ሆን ተብሎ ወገን ከወገኑ ጋር ለማጋጨትና ጥርጣሬ ለመፍጠር የተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ውሎ አድረዋል። ስለዚህ ህወሓት በኢትዮጵያውያን መካከል እየተከለ ያለው ልማት ሳይሆን ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ የጥፋት ፈንጅ መሆኑን በመገንዘብ የአንድነትና የሰላም ባላንጣ የሆነውን ድርጅት የሚፈፀመው ግፍ ከካድሬዎቹ በስተቀር ብዙሃኑን የማይወክል መሆኑን እየገለፅን ቡድናዊ አምባ ገነኖችን ከህዝብ ነጥሎ መታገል የፓለቲካ ብልህነት ብቻ ሳይሆን አማራጭ የሌለው የለውጥ መንገድም እሱ ብቻ መሆኑን እናምናለን።
6. እኛም ከማንም ከምንም በላይ ዘር፣ ቦታ፣ ሀይማኖት፣ ቋንቋ፣ የፓለቲካ እምነትና ስደት ሳይገድበን ከ80 ሚሊዮን በላይ የሆነውን ህዝብ እንደ ዓይን ብሌናችን በማየት ችግሩ ችግራችን፣ ደስታው ደስታችን፣ ሀዘኑም ሀዘናችን መሆኑን በማመን የጋራ ችግራችንን በጋራ ለመፍታት በሚደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ ከጎኑ የምንቆም መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

CPJ expresses grave concern over the deteriorating health conditions of Reeyot Alemu


CPJ expresses grave concern over the deteriorating health conditions of Reeyot Alemu


The New York-based Committee to Protect Journalists (CPJ) has expressed concern about the safety of Reeyot Alemu, a jailed Ethiopian journalist and teacher.
Reeyot Alemu
In a protest letter to Birhan Hailu, Ethiopia’s justice minister, Joel Simon, CPJ’s Executive Director asked that Alemu, whose health has reportedly deteriorated since being held on terrorism charges, to withdraw the threat of placing her in solitary confinement.
Human rights and press freedom groups have long accused Addis Ababa of using its controversial terrorism legislation to curb opposition and stifle the media in the East African nation.
“Prison authorities have threatened Reeyot with solitary confinement for two months as punishment for alleged bad behavior toward them and threatening to publicize human rights violations by prison guards” said CPJ’s letter, which was published on its website.
Despite pledges to the contrary Ethiopia’s Ministry of Justice has failed to ensure that Reeyot’s full human rights have not been violated during her detention, which began in June 2011.
“We urge you to fulfill Ethiopia’s promise to build a humane and democratic state by withdrawing the threat of solitary confinement against Reeyot and ensuring her access to adequate medical care” CPJ said.
“No journalists should face detention or imprisonment in the exercise of their duty”
Reeyot, a columnist for the now-defunct independent weekly Feteh, is being held of the basis of accusation that she was involved in a vague terrorism plot.
In January 2012 she was sentenced her to 14 years in prison under the country’s anti-terrorism law however an appeals court later in August, reduced the initial sentence to five years after the court dropped most of the terrorism charges pressed against the journalist, who is known for writing columns critical of the government.
CPJ has also expressed grave concern over the deteriorating health conditions of Reeyot saying she has been denied of access to adequate medical treatment after she was diagnosed with a tumor in her breast.
Reeyot is a 2012 winner of the International Women’s Media Foundation Courage Award.
International human right groups accuse Ethiopia of using the country’s broadly defined anti-terrorism law to punish critical journalists and opposition members, an allegation Addis Ababa denies.
In 2011 the United Nations special rapporteur on torture, Juan E. Méndez, urged the prohibition of “the imposition of solitary confinement as punishment – either as part of a judicially imposed sentence or a disciplinary measure.”
In the report the special rapporteur urged Ethiopia to fulfill its obligation as signatory to the United Nations Convention against torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment.
Source: Sudan Tribune

Thursday, April 11, 2013

በአዲስ አበባ የወያኔ/ኢህአዴግ ደጋፊ ሴቶች ቃለ ማህላ ፈጸሙ


በአዲስ አበባ የወያኔ/ኢህአዴግ ደጋፊ ሴቶች ቃለ ማህላ ፈጸሙ


በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሴቶች ሚያዚያ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባስታዲየም በመገኘት ኢህአዴግን እንደሚመርጡ አስታውቀዋል
ኢህአዴግ ያለጠንካራ ተቃዋሚ በሚሮጥበት የአዲስ አበባ እና የክልልምርጫ በአዲስ አበባ ሴቶች ሊግ አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ እናማስፈራሪያ ሲደረግ ቆይቷል።
ሴቶቹ በነፍስ ወከፍ ኮፍያ እና ቲሸርት የታደላቸው ሲሆን አንዳንዶ አበልእንደተከፈላቸውም ሲናገሩም ደምጠዋል። በተለያዩ መኪኖች ላይ ቅስቀሳያደርጉ የነበሩ ሴቶች የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ የያዙ ቲሽርቶችን በመልበስእንዲሁም ፎቶግራፋቸውን በመያዝ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

ሴቶቹ እጅ ለእጅ በመያያዝ አቶ መለስን ራእይ እናሳካለን በማለት ቃልመግባታቸው ታውቋል።
አንድ አስተያየት ሰጪ የምርጫ ቅስቀሳው አቶ መለስ ዜናዊ ከሞት ተነስተውለምርጫ እየተወዳደሩ ነው እንዴ ያስብላል ብሎአል። የምርጫ ቅስቀሳውኢህአዴግን ምረጡ ሳይሆን መለስን ምረጡ ሆኗል ብሎአል።
ኢህአዴግ 2002 የተደረገውን አገራዊ ምርጫ 99 ነጥብ 6 በመቶድምጽ ማሸነፉ ይታወሳል። የሚቀጥለውን ሳምንት ምርጫም አሀዙን በነጥብሶስት በማሳደግ፣ 99 ነጥብ 9 ያሸንፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይነገራል

መንግስት በመለስ ፋውንዴሽን ውስጥ ጣልቃ መግባቱን የአቶ መለስ ልጅ ተቃወመች የአቶ መለስ ዜናዊን ምስል ያለፈቃድ መጠቀም ሊከለከል ነው


መንግስት በመለስ ፋውንዴሽን ውስጥ ጣልቃ መግባቱን የአቶ መለስ ልጅ ተቃወመች የአቶ መለስ ዜናዊን ምስል ያለፈቃድ መጠቀም ሊከለከል ነው


በዘሪሁን ሙሉጌታ

የቀድሞ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የበኩር ልጅ ወጣት ሰምሀል መለስ ባለፈው ቅዳሜ በተቋቋመው “የመለስ ፋውንዴሽን” ውስጥ መንግስት ጣልቃ መግባቱን ተቃወመች።
ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው የፋውንዴሽኑ የማቋቋሚያ መስራች ጉባኤ ላይ ወጣት ሰምሀል ፋውንዴሽኑ የመለስ አስተሳሰብ ምንጭ መሆን ሲገባው መንግስት በፋውንዴሽኑ ላይ ሚናው መጉላቱ ተገቢ አለመሆኑን ተናግራለች።
ወጣት ሰምሀል በፋውንዴሽኑ ምስረታ ወቅት “አሰራሩ እኔ አልገባኝም። ከዚህ በፊትም ቤተሰብ አንስቶ ነበር። በአዋጁ ላይ የመንግስት ሚና መጉላቱ ስህተት ነው ብለናል” ስትል ተቃውሞዋን አሰምታለች።
ሰምሀል የመንግስትን በፋውንዴሽኑ ጣልቃ መግባትን ብትቃወም ከፋውንዴሽኑ 13 የቦርድ አባላት አራቱ ከቤተሰባቸው ዘጠኝ ደግሞ የመንግስት አካላት ሆነው የተመረጡ ሲሆን ወደፊት አዋጁን በማሻሻል ሌሎች አካላትን ለማሳተፍ ከመታሰቡ ባለፈ በዕለቱ የሰማህል ሃሳብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
በተያያዘ ዜና የቀድሞ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ምስል ያለቤተሰቦቻቸውም ወይም በስማቸው ከተቋቋመው ፋውንዴሽን ፈቃድ ውጪ በማንኛውም ቦታ መለጠፍም ሆነ ምስላቸውን ቀርፆ መጠቀም ሊከለከል ነው።
የአቶ መለስን ምስል ያለፈቃድ መጠቀምን የሚከለክለው ረቂቅ መመሪያ የተዘጋጀው በአዋጅ ቁጥር 781/2005 አንቀፅ ዘጠኝ ንዑስ አንቀፅ 2(ሰ) መሰረት ነው።
ረቂቅ መመሪያው ባለፈው ቅዳሜ የመለስ ፋውንዴሽን ይፋ በተደረገበት ወቅት ለውይይት ተበትኗል። በረቂቅ መመሪያው ስለ ምስላቸው አጠቃቀም በሚያወሳው አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ (1) ላይ ማንኛውም ሰው ለክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ያለውን ፍቅርና ክብር ለመግለፅ ምስሉን በመኖሪያ ቤቱ ግድግዳ ላይ ሊሰቅል፣ በአልበም ውስጥ፣ በቦርሳው፣ በኪሱ፣ በተሽከርካሪው ወይም በሌላ የግል መጠቀሚያው ሊይዘው ከሚችለው በስተቀር ምስላቸውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ፣ ለሽያጭ፣ ለባዛር፣ ለጨረታ ወይም ለማንኛውም የንግድ ድርጅት ወይም ሌላ ተቋም ማስታወቂያ፣ የንግድ ምልክት፣ ለመታሰቢያነት ወይም ለማንኛውም ጥቅም ማስገኛነት ሊሰቅል ወይም ሊቀርፅ ወይም በማንኛውም ሁኔታ ሊያስቀምጥ እንደማይችል አስቀምጧል።
ከዚህ በተጨማሪ የአቶ መለስን ምስል በተለየ ሁኔታ ለህዝባዊ አላማና ጥቅም ለመጠቀም የፈለገ አካል ከቤተሰባቸው ወይም ከፋውንዴሽኑ ቦርድ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት መመሪያው ያስገድዳል።
በተያያዘም ከፋውንዴሽኑ ፈቃድ ውጪ በአቶ መለስ ዜናዊ ስም ማንኛውንም አይነት ግንባታ ለመገንባት በማሰብ የእሳቸውን ስም፣ ምስል ወይም ስራዎች በመጠቀም ገንዘብ ወይም ቁሳቁስ መሰብሰብን ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል።¾

Wednesday, April 10, 2013

ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ለግራዚያኒ የሚሰራውን ሀውልት አለም እንዲያወግዘው ጠየቁ


ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ለግራዚያኒ የሚሰራውን ሀውልት አለም እንዲያወግዘው ጠየቁ


አወዛጋቢ ንግግር በመናገር የሚታወቁት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሚያዚያ 1 ቀን ሚኒስተሩ በሰጡት አስተያየት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የአለማቀፉ ማህበረሰብና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እና በሊቢያ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ላደረሰው ግራዚያኒ ሀውልት ለማቆም የሚደረገውን ጥረት እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።ሚ/ሩ ይህን የተናገሩት በሩዋንዳ የደረሰውን ዘር ማጥፋት 19ኛ አመት ለማስታወስ በተጠራ ዝግጅት ላይ ነው።
የኢትዮጵያን እና የሊቢያን ዜጎች በግፍ የጨፈጨፈው ግራዚያኒ ሀውልት አይገባውም ብለዋል ሚኒስትሩ።የሚኒሰትሩ ንግግር መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም አ/አ ስድስት ኪሎ የካቲት 12 መታሰቢያ ሐውልት እስከ ጣሊያንኤምባሲ ሰልፍ በማድረግ በጣሊያን ለፋሽስቱ ግራዚያኒ መናፈሻና ሙዚየም መሰራቱን በመቃወማቸው አለማቀፍ የህግ ባለሙያውን ዶ/ር ያእቆብ ሀይለማርያምን ጨምሮ 38 ያህል ሰዎች በፖሊስ ታስረው ከተፈቱበት ድርጊት ጋር የሚቃረን ሆኖ ተገኝቷል።የኢትዮጵያ መንግስት በወቅቱ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ትችት ሲደርስበት እንደነበር ይታወሳል።

ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ተወሰነ “ስህተት ተፈፅሟል” አቶ አህመድ ናስር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር


ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ተወሰነ “ስህተት ተፈፅሟል” አቶ አህመድ ናስር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር


 በዘሪሁን ሙሉጌታ
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው በጎጃም ፍኖተሰላምአካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረገው በስህተት መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የተፈናቀሉት በሙሉቀደም ሲል ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑንም አስታወቁ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰሞኑንከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራ ተወላጆች በሙሉ እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀዋል።
በክልሉ ከአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ከኦሮምያ ከመሬት ጥበት፣ ከአፈር ምርታማነት ማጣት ጋር በተያያዘ የተሻለመሬት ፍለጋ ሰዎች ወደ ክልሉ እንደሚገቡ የገለፁት አቶ አህመድ ነገር ግን ሰፈራው በሕገ-ወጥ መንገድ ሲፈፀም መቆየቱንአስታውሰዋል።
እኛ የምንቃወመው በሕገ-ወጥ መንገድ በደን ውስጥ እየገቡ ደን እየመነጠሩ ሰፈራ ማስፋፋቱን ነው። ይህ ደግሞለክልሉ ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገርም አደጋ አለው” ያሉት አቶ አህመድ “በሕገ-መንግስታችን መሠረት ማንኛውም ሰው ለስራቢዘዋወር ችግር የለውም” ብለዋል።

ነገር ግን አሁን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት ለምን እንደሆነ ርዕሰ መስተዳደሩ ተጠይቀው ከታች ያለውአስተዳደር ስህተት በመፈፀሙ ነው ሲሉ አምነዋል። አስተዳዳሪዎቹ ሕዝቡን ያፈናቀሉት ሕገ-ወጥ ሰፈራውን ከነባሩ የመለየትስራ ላይ ተናቦ የመስራት ችግር በማጋጠሙ ነው ብለዋል።
አስተዳደራችን አካባቢ ስህተት ተፈፅሟል። መፈፀም ግን አልነበረበትም። ነገር ግን እንደ ክልል መንግስትበሕገ-ወጥ መንገድ የሰፈሩትን መቆጣጠር አለብን። ኅብረተሰቡ በፈለገው ጊዜና ወቅት እየተነሳ ደን እየመነጠረ መስፈርአስቸጋሪ ስለሆነ ስርዓት መያዝ አለበት የሚል አቋም አለን” ያሉት አቶ አህመድ ስህተት የፈፀሙ የአስተደደር አካላት ላይምግምገማ በማካሄድ ማስተካከያ እናደርጋለን ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር ምክክር መደረጉንም ያስታወሱት አቶ አህመድ ችግሩ በድጋሚሊፈጠር የማይችልባቸውን ቀዳዳዎች ለመድፈን ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ወደ 1 ሺህ 346 አባወራዎች ሺህ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲፈናቀሉ መደረጉንየጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ችግሩ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ጋር የተያያዘ መሆኑንም አስረድተዋል።
በክልላችን አንዳንድ ቦታዎች ሰዎቹን ወደ አካባቢው ካስገቡአቸው በኋላ የሚታይ ችግር አለ። በተለይ ከመሬትአስተዳደር ጋር በተያያዘ ችግር አለብን። በየጊዜው እናጣራለን፤ እንጠርጋለን፣ እንገመግማለን ችግሩን ግን ሙሉ በሙሉማፅዳት አልተቻለም” ሲሉ ተናግረዋል።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ክልሉ መግባትና መውጣት የሚያስችል ሕገ-መንግስታዊ መብቱ የተከበረ መሆኑንያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይም ከአማራ ክልል ወደ ክልላችን ለስራ በሚገቡበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ላይመደረሱን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ የክልሉ ደን እንዳይወድምና ጥበቃ እንዲደረግ ከአማራ ክልል ጋር ከስምምነት ላይተደርሷል ብለዋል።
በትናንትናው ዕለት በፍኖተ ሰላም ከተማ ተፈናቃዮችን ወደመጡበት አካባቢ ለመመለስ 11 መኪኖችመዘጋጀታቸውንና ተፈናቃዮቹን የሚያጅቡ የፌዴራል ልዩ የፖሊስ ኃይል መታጀባቸውን የዓይን ምስክሮች ገልፀዋል።