በፌስ ቡክ “ስም አጉድፈሀል” የተባለው ተማሪ በ5 ሺ ብር ዋስ ተፈታ
መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ አመትተማሪ የሆነው ማንያዘዋል እሸቱ ለኢሳት እንደገለጠው ከአንድሳምንት እስር በሁዋላ፣ የአርባ ምንጭ ፍርድ ቤት “ስትፈለግትመጣለህ” በማለት በ5 ሺ ብር ዋስ ለቆታል። ወደ ፈተናለመግባት ሲዘጋጅ ሶስት ፖሊሶች መጥተው የፍርድ ቤት ማዘዣበማሳየት እንደወሰዱትና በአርባ ምንጭ እስር ቤት አንድ ሳምንትማሳለፉን ተማሪ ማንያዘዋል ገልጿል።
ተማሪ ማንያዘዋል፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በሙስና መዘፈቁንእንዲሁም በአገሪቱ ያለው የመብት አፈና መጨመሩን የሚገልጽጽሁፍ በድረገጽ አውጥተሀል ተብሎ መያዙን ገልጿል ።
አቃቢ ህግ በቂ ማስረጃ አላገኘሁም በማለቱ እንደተለቀቀ የገለጠውተማሪ ማንያዘዋል፣ ይሁን እንጅ 5 ሺ ብር በሁለት ሳምንት ውስጥእከፍላለሁ ብሎ ቃል በመግባት በመፈታቱ፣ ይህን ገንዘብ ካልከፈለወደ እስር ቤት እንደሚመለስ ተናግሯል። የደሀ ልጅ በመሆኑገንዘብ መክፈል እንደማይችል የገለጠው ተማሪ ማንያዘዋል፣ ፍርድቤቱ ቶሎ ውሳኔ ቢሰጠው ከጭንቀት እንደሚገላገልም ገልጿል።“አሁን ከአሁን መጥተው ይወስዱኝ ይሆን” በማለት ትምህርቱንተረጋግቶ መማር እንዳልቻለም ተናግሯል።
በጠባብ ክፍል ውስጥ 25 ሰዎች ታስረው እንደነበር፣ ከሙቀቱበተጨማሪ ቱሁዋን አስቸግሮት እንደነበር አልሸሸገም። ተማሪማንያዘዋል ፖሊሶች እና ፍርድ ቤቱ ላደረገለት ትብብርም ምስጋናአቅርቧል።
ተማሪ ማንያዘዋል 4 ነጥብ በማምጣት ዩኒቨርስቲ መግባቱምታውቋል። በሚማርበት ዩኒቨርስቲም እንዲሁ ከፍተኛ ውጤትእያስመዘገበ አለ የ21 አመት ወጣት ነው።
No comments:
Post a Comment