Wednesday, April 10, 2013

ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ተወሰነ “ስህተት ተፈፅሟል” አቶ አህመድ ናስር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር


ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ተወሰነ “ስህተት ተፈፅሟል” አቶ አህመድ ናስር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር


 በዘሪሁን ሙሉጌታ
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው በጎጃም ፍኖተሰላምአካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረገው በስህተት መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የተፈናቀሉት በሙሉቀደም ሲል ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑንም አስታወቁ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰሞኑንከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራ ተወላጆች በሙሉ እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀዋል።
በክልሉ ከአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ከኦሮምያ ከመሬት ጥበት፣ ከአፈር ምርታማነት ማጣት ጋር በተያያዘ የተሻለመሬት ፍለጋ ሰዎች ወደ ክልሉ እንደሚገቡ የገለፁት አቶ አህመድ ነገር ግን ሰፈራው በሕገ-ወጥ መንገድ ሲፈፀም መቆየቱንአስታውሰዋል።
እኛ የምንቃወመው በሕገ-ወጥ መንገድ በደን ውስጥ እየገቡ ደን እየመነጠሩ ሰፈራ ማስፋፋቱን ነው። ይህ ደግሞለክልሉ ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገርም አደጋ አለው” ያሉት አቶ አህመድ “በሕገ-መንግስታችን መሠረት ማንኛውም ሰው ለስራቢዘዋወር ችግር የለውም” ብለዋል።

ነገር ግን አሁን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት ለምን እንደሆነ ርዕሰ መስተዳደሩ ተጠይቀው ከታች ያለውአስተዳደር ስህተት በመፈፀሙ ነው ሲሉ አምነዋል። አስተዳዳሪዎቹ ሕዝቡን ያፈናቀሉት ሕገ-ወጥ ሰፈራውን ከነባሩ የመለየትስራ ላይ ተናቦ የመስራት ችግር በማጋጠሙ ነው ብለዋል።
አስተዳደራችን አካባቢ ስህተት ተፈፅሟል። መፈፀም ግን አልነበረበትም። ነገር ግን እንደ ክልል መንግስትበሕገ-ወጥ መንገድ የሰፈሩትን መቆጣጠር አለብን። ኅብረተሰቡ በፈለገው ጊዜና ወቅት እየተነሳ ደን እየመነጠረ መስፈርአስቸጋሪ ስለሆነ ስርዓት መያዝ አለበት የሚል አቋም አለን” ያሉት አቶ አህመድ ስህተት የፈፀሙ የአስተደደር አካላት ላይምግምገማ በማካሄድ ማስተካከያ እናደርጋለን ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር ምክክር መደረጉንም ያስታወሱት አቶ አህመድ ችግሩ በድጋሚሊፈጠር የማይችልባቸውን ቀዳዳዎች ለመድፈን ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ወደ 1 ሺህ 346 አባወራዎች ሺህ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲፈናቀሉ መደረጉንየጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ችግሩ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ጋር የተያያዘ መሆኑንም አስረድተዋል።
በክልላችን አንዳንድ ቦታዎች ሰዎቹን ወደ አካባቢው ካስገቡአቸው በኋላ የሚታይ ችግር አለ። በተለይ ከመሬትአስተዳደር ጋር በተያያዘ ችግር አለብን። በየጊዜው እናጣራለን፤ እንጠርጋለን፣ እንገመግማለን ችግሩን ግን ሙሉ በሙሉማፅዳት አልተቻለም” ሲሉ ተናግረዋል።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ክልሉ መግባትና መውጣት የሚያስችል ሕገ-መንግስታዊ መብቱ የተከበረ መሆኑንያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይም ከአማራ ክልል ወደ ክልላችን ለስራ በሚገቡበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ላይመደረሱን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ የክልሉ ደን እንዳይወድምና ጥበቃ እንዲደረግ ከአማራ ክልል ጋር ከስምምነት ላይተደርሷል ብለዋል።
በትናንትናው ዕለት በፍኖተ ሰላም ከተማ ተፈናቃዮችን ወደመጡበት አካባቢ ለመመለስ 11 መኪኖችመዘጋጀታቸውንና ተፈናቃዮቹን የሚያጅቡ የፌዴራል ልዩ የፖሊስ ኃይል መታጀባቸውን የዓይን ምስክሮች ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment