በአዲስ አበባ የወያኔ/ኢህአዴግ ደጋፊ ሴቶች ቃለ ማህላ ፈጸሙ
በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሴቶች ሚያዚያ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባስታዲየም በመገኘት ኢህአዴግን እንደሚመርጡ አስታውቀዋል
ኢህአዴግ ያለጠንካራ ተቃዋሚ በሚሮጥበት የአዲስ አበባ እና የክልልምርጫ በአዲስ አበባ ሴቶች ሊግ አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ እናማስፈራሪያ ሲደረግ ቆይቷል።
ሴቶቹ በነፍስ ወከፍ ኮፍያ እና ቲሸርት የታደላቸው ሲሆን አንዳንዶቹ አበልእንደተከፈላቸውም ሲናገሩም ተደምጠዋል። በተለያዩ መኪኖች ላይ ቅስቀሳያደርጉ የነበሩ ሴቶች የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ የያዙ ቲሽርቶችን በመልበስእንዲሁም ፎቶግራፋቸውን በመያዝ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ሴቶቹ እጅ ለእጅ በመያያዝ አቶ መለስን ራእይ እናሳካለን በማለት ቃልመግባታቸው ታውቋል።
አንድ አስተያየት ሰጪ የምርጫ ቅስቀሳው አቶ መለስ ዜናዊ ከሞት ተነስተውለምርጫ እየተወዳደሩ ነው እንዴ ያስብላል ብሎአል። የምርጫ ቅስቀሳውኢህአዴግን ምረጡ ሳይሆን መለስን ምረጡ ሆኗል ብሎአል።
ኢህአዴግ በ2002 የተደረገውን አገራዊ ምርጫ በ99 ነጥብ 6 በመቶድምጽ ማሸነፉ ይታወሳል። የሚቀጥለውን ሳምንት ምርጫም አሀዙን በነጥብሶስት በማሳደግ፣ በ99 ነጥብ 9 ያሸንፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይነገራል።
No comments:
Post a Comment