የማመሳቀል አቅምን ማሳየት የፖለቲካ አሸናፊነትን ማሳየት አይደለም!
አጼ ኃይለሥላሴ በሰጡት ንጉሳዊ ብይን ያልተደሰተ ኢትዮጵያዊ ንጉሱ ፊት ቀርቦተቃውሞውን የማሰማት እድል ነበረው። እናም በንጉሱ ፊት “ጃንሆይ የሰጡትፍርድ ፍርደ-ገምድል ነው። አቤት እላለሁ” በማለት ምሬቱን ይገልጻል። ንጉሱም“ከእኛ በላይ ማን አለና ነው…ለማን ነው አቤት የምትለው?” ብለው ይጠይቁታል።“ሁሉን ለሚችል አምላክ እንጂ ለሌላ ለማን ይነገራል” ብሎ መለሰላቸው። ንጉሱምበሚታወቁበት ርጋታቸው ከፈገግታ ጋር “እኛን ቀብቶ ያነገስን ማን ነው እና ነውለእግዚያብሄር ይግባኝ የምትለው” ብለው መለሱለት ይባላል። ከዓመታት በፊትኢትዮጵያ ውስጥ መጽሄት ሳነብ (ጦቢያ ላይ ይመስለኛል) ያገኘሁትን ነውያካፈልኩት። ተደርጎ ይሆናል። ውጭያዊ ምክንያቶችን እንደተጠበቁ ሆነው የለውጥሃሳብን ከኢትዮጵያዊነት እና ከኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ጋር ማዋኽድ ስለተሳነውበ1966 የፈነዳው ዓብዮት ዛሬም ድረስ ባይሳካም ፤ በወቅቱ የተወሰደው እሳትየለበስ እሳት የጎረሰ የፓለቲካ ርምጃ ጥሩ ነበር መጥፎ የሚለውን ብይን ለየራሳችንትተን ለውጡ በማያሻማ ሁኔታ ትቶት የሄደውን ትምህርት ግን ማስታወስያስፈልጋል።የህዝብ የቁጣ ሰይፍ ሲመዘዝ በነማን ላይ እንዳነጣጠረ የሚስተው ሰውያለ አይመስለኝም።