Saturday, March 30, 2013

ለጥቂቶች ኬክ ለብዙሃን እከክ -እድገት ወይስ ውድቀት Hey Woyane's ,what happened to all that "double-digit growth?" Is there really growth of whatsoever or is it just an illusion? Why are millions of Habeshas jobless, poor, and worse,rummaging through trash for scraps of food alongside dogs and wild animals

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሞ የውይይት መድረክ አዘጋጅነት በሚኒሶታ ሲካሄድ የነበረውን ተከታታይ ውይይት ተከትሎበአቶ ሌንጮ ለታ መሪነት እና በ አቶ ዲማ ነገዎ ሰርቦ ተከታይ ምክትልነት የሚመራ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባርየተሰኘ የብሄር ድርጅት መመስረቱ ይፋ ተደርጓል:: አብዛኛዎችን የቀድሞ የኦነግ አመራሮችን እና አባላትን ያቀፈው ይህ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ የድርጅቱን ደንብ በማጽደቅበይፋ ስራ ጀምሯል:; የድርጅቱን ደንብ ይመልከቱት ::

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲ በሌንጮ ለታ መሪነት ተመሰረተ።


ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሞ የውይይት መድረክ አዘጋጅነት በሚኒሶታ ሲካሄድ የነበረውን ተከታታይ ውይይት ተከትሎበአቶ ሌንጮ ለታ መሪነት እና  አቶ ዲማ ነገዎ ሰርቦ ተከታይ ምክትልነት የሚመራ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባርየተሰኘ የብሄር ድርጅት መመስረቱ ይፋ ተደርጓል::
አብዛኛዎችን የቀድሞ የኦነግ አመራሮችን እና አባላትን ያቀፈው ይህ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ የድርጅቱን ደንብ በማጽደቅበይፋ ስራ ጀምሯል:; የድርጅቱን ደንብ ይመልከቱት ::
DECLARATION OF THE OROMO DEMOCRATIC FRONT (ODF)
We, members of the Founding Congress of the Oromo Democratic Front (ODF), announce the launching of a new Oromo political movement that advocates justice for the Oromo and all other nations in Ethiopia. The founding of ODF ushers in a new phase in the Oromo nationalist struggle with the objective of working for the transformation of the Ethiopian state into a truly democratic multinational federation equitably owned by all the nations.
We are launching this new movement cognizant of the fact that Ethiopia has been, and remains, the prison of nations and nationalities, with the Oromo being one of the prisoners. Today in Ethiopia, domination, repression, discrimination, eviction, denial of religious freedom, humiliation and exploitation of the Oromo and other nations and nationalities have attained new heights. And this needs to come to an end. It is to contribute to this end that we are launching a movement that advocates freedom and justice for all individuals and nations.

Our advocacy of justice for all individuals and nationals is motivated by the universal principle that struggling for justice for oneself alone without advocating justice for all could ultimately prove futile because “injustice anywhere is a threat to justice everywhere.”
We also believe that the economic and security interests of the Oromo people are intertwined with that of other peoples in Ethiopia. In addition, thier geographic location, demography, democratic heritage and bond forged with all peoples over the years make it incumbent upon the Oromo to play a uniting and democratizing role.
By taking this proactive and inclusive stand we are heralding the re-articulation of the Oromo struggle for self-determination as the advocacy of justice for all Ethiopians. This measure does not imply the repudiation of the struggle waged to date by the Oromo Liberation Front (OLF) but rather to build on its achievements and to open a bold new forward looking chapter.

Thursday, March 28, 2013

የሙት ዜናዊን ሚስት ውሸታቸውም ለማሳማን እጃቸውን እያወናጨፉ የዜናዊ ድህነት ይሰመርበት እያሉ የወያኔ ፓርቲ ላይ ሲጮሁ ይመልከቱ ::ይቺ አዜብ የተባለች ግለሰብ ከንግግሯ ከ 20 አመት በኍላ ምን ያክል ያልተሻሻለች ተራ አሉባልተኛ የመንደር ሴት መሆኗን በዚህ ንግግር ላይ ከምታቀርበው ሀሳብና እጇን ማወናጨፍ ማስተዋል ይቻላል

የሙት ዜናዊን ሚስት ውሸታቸውም ለማሳማን እጃቸውን እያወናጨፉ የዜናዊ ድህነት ይሰመርበት እያሉ የወያኔ ፓርቲ ላይ ሲጮሁ ይመልከቱ ::ይቺ አዜብ የተባለች ግለሰብ ከንግግሯ ከ 20 አመት በኍላ ምን ያክል ያልተሻሻለች ተራ አሉባልተኛ የመንደር ሴት መሆኗን በዚህ ንግግር ላይ ከምታቀርበው ሀሳብና እጇን ማወናጨፍ ማስተዋል ይቻላል

Meles was a poor man who had no bank account - Azeb Mesfin

Editor's Note - Azeb Mesfin, the widow of Meles Zenawi, said her husband's net salary was 4,000 Birr a month, too little money that he had no need for a bank account. Azeb was mad that such an important fact was missing from the minds of those who write flawless tributes in honor of her late husband. Eulogy writers should heed her advice before she gets hold of them: First, she is a member of the powerful TPLF politburo; second, if money is power, Azeb is uber-rich, perched like an eagle's nest atop the mountain of gold called "EFFORT."

Delegates of the ninth convention of the ruling EPRDF party have shown their dissatisfaction over a eulogy written for their late leader, Meles Zenawi, while some were critical of the quality of its writing and completeness of the content.
Translated from Tigrigna, the eulogy was first presented to the congress of the TPLF, held in Meqelle two weeks ago, before it was presented to over 1,000 delegates at the conclusion of the ruling coalition's convention on Tuesday, held in Bahir Dar.The first to voice such disappointment over the organisation of the eulogy and its content structure was Meles's widow. Elected to the political bureau of the TPLF for the second time and to the all too powerful Executive Committee of the EPRDF, Azeb Mesfin was displeased to see the eulogy incomplete.
Some of the points she argued as missed are Meles's place, role and the contributions he made as an Editor-in-Chief of the party's ideological organ, Addis Ra'ey. Azeb feels that the contributions Meles had made in originating the idea of forming a training facility for the rank and file, now directed by Addisu Legesse, and the manual he develop ought to be forcefully underlined.
Azeb defended her late husband's legacy in relations to how he had handled the conflict and the subsequent war with Eritrea. Despite condemnations from his political opponents due to his heritage, Azeb told delegates that Meles had never negotiated on the national interests of Ethiopia.
"Not even for a second," Azeb told delegates rather emphatically.
Azeb described Meles's conduct during the war with Eritrea in the late 1990s as "extraordinary" in not showing what he had felt of the accusations, but focused on defending his beliefs and political positions regardless.
She recalled her late husband as perhaps the only leader who had earned a little over 4,000 Br a month in net salary, but fought poverty with courage and resolve, while remaining selfless.
"Meles didn't have a bank account," Azeb said. "He had neither an ID card nor a driving licence."
These parts, Azeb argued, were not given their proper place in the eulogy, which was read by Hailemariam Desalegn, re-elected to chair the EPRDF twice since the death of Meles in August 2012.
Hailemariam's re-election was fait accompli, although he was made to pass the test of contest to the office. His deputy, Demeke Mekonnen of ANDM, and Alemayehu Atomsa of OPDO, were nominated by their respective parties for the chairmanship, while leaders of the TPLF have declined to nominate their leaders, Fortune learnt.
Hailemariam has won the chairmanship with a landslide, after bagging 176 votes of the 180 Council members of the ruling party, sources in the Council disclosed to Fortune.
Although the other two contenders have received two votes each against Hailemariam, Demeke too claimed the deputy chairmanship position with significant margin, claiming 146 votes against 25 given to his contender, Fortune learnt.
Emerging as uncontested non-combatant leader of the Revolutionary Democrats since the party's formation in the late 1980s, Hailemariam was seen endorsing the conciliatory proposition made by Addisu, who remains one of the 13 political bureau members of the ANDM but left out from the EPRDF's Executive Committee.
Addisu has argued that the eulogy is filled with repetition, is not well organised, and suffers from losses in translation, while its structure is weak. Addisu urged delegates to let the EPRDF's Executive Committee rewrite the eulogy before it gets adopted as the party's official document, a proposition Hailemariam had secured its adoption by the Congress unanimously.

Wednesday, March 27, 2013

Over fifty die as lorry plunges into river in Ethiopia ESAT News March 26, 2013

Over fifty die as lorry plunges into river in Ethiopia
ESAT News March 26, 2013

Fifty nine people have reportedly died after a lorry that was transporting 60 people of an Amhara ethnic origin evicted from the BeniShangul Gumz Region crashed into Jedesa River in Tekesha District of Ethiopia on March 24, 2013. Women and children are among the dead. According to some of the evictee farmers, who wanted to remain anonymous, the deceased and the sole survivor received no proper care yet. ESAT’s repeated efforts to speak to the Regional authorities were unsuccessful.

In a related development, several of the famers ordered to leave the region, have today reported that they have been attacked by BeniShangul Region’s militia.

The Region’s officials recently told the Addis Abeba based weekly Newspaper, Addis Admas that the evictees were “illegal settlers”. Gizaw Legese, a legal expert, had stated that Article 32 of the Ethiopian Constitution respects “Freedom of Movement” and stipulates “Any Ethiopian or foreign national lawfully in Ethiopia has, within the national territory, the right to liberty of movement and freedom to choose his residence, as well as the freedom to leave the country at any time he wishes to.”

Benishangul Gumz Region had last month ordered thousands of Amhara farmers to leave the land that they have farmed and live on for decades. The Southern Region also had displaced thousands of Amhara farmers a year ago.
Over fifty die as lorry plunges into river in Ethiopia
ESAT News   March 26, 2013

 Fifty nine people have reportedly died after a lorry that was transporting 60 people of an Amhara ethnic origin evicted from the BeniShangul Gumz Region crashed into Jedesa River in Tekesha District of Ethiopia on March 24, 2013. Women and children are among the dead.  According to some of the evictee farmers, who wanted to remain anonymous, the deceased and the sole survivor received no proper care yet. ESAT’s repeated efforts to speak to the Regional authorities were unsuccessful.

In a related development, several of the famers ordered to leave the region, have today reported that they have been attacked by BeniShangul Region’s militia.

The Region’s officials recently told the Addis Abeba based weekly Newspaper, Addis Admas that the evictees were “illegal settlers”.  Gizaw Legese, a legal expert, had stated that Article 32 of the Ethiopian Constitution respects “Freedom of Movement” and stipulates “Any Ethiopian or foreign national lawfully in Ethiopia has, within the national territory, the right to liberty of movement and freedom to choose his residence, as well as the freedom to leave the country at any time he wishes to.”

Benishangul Gumz Region had last month ordered thousands of Amhara farmers to leave the land that they have farmed and live on for decades. The Southern Region also had displaced thousands of Amhara farmers a year ago.


ጩኸት እና ዋይታ እንደገና በጋምቤላ…በአማራ

ጩኸት እና ዋይታ እንደገና በጋምቤላ…በአማራ በበደኖ፣ በአርባጎጎ የተጀመረውና በሰው ልጅ ላይ ይፈፀማል ተብሎ በማይታሰበው ኢ- ሰባአዊ ድርጊት ግድያ ተባብሶ ዛሬ ጋምቤላ የጥቃቱ መንደር ባለተራ ሆናለች። ወደ ኋላ ባለፉት 9 አመታት በጋምቤላ ምድር በወያኔ ጥይት የተገደሉ፣ የተጨፈጨፉ ከ400 በላይ ንጹሃን አኙዋኮችን ማጣታችን ይታወሳል። ያ ሀዘንና ሰቆቃ፣ ጠባሳው ሳይጠፋ ዛሬ ደግሞ ሌላ ዋይታ፣ ግድያ፣ እንግልት፣ ጮኸት በዛው ቦታ በጋምቤላ እንደና እየተሰማ ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው የዘረኝነት ፖሊሲ አስተዳደር ስልጣኑን እስከጠበቀለት ድረስ ማናቸውንም ዜጋ መግደል፣ማሰር፣ ማባረር እንደሚችል የጋምቤላው ክልል አስተዳደር ደረታቸውን ሞልተው ነግረውናል። ይህ ዘር ላይ ያነጣጠረው ጭፍጨፋ የጋምቤላን ህዝብ መሬቱንና ቀን ከሌት ደከመኝ ሳይል ያፈራውን ንብረቱን በመንጠቅ፤ የተማረውን የክልሉን ተወላጅ በትውልድ – መንደሩ ስደተኛ፣ የበይ ተመልካች እንዲሆንና እንዲቆጭ እያደረጉት ነው። በተለይም በሀገሩ ምድር በመኖሩ ወንጀለኛ፣ ሽብርተኛ በማድረግ ዜጎች ስለመብታቸው እንዳይጠይቁ የማስፈራራት፣ የወዮላችሁ ዘመቻ ላይ ናቸው ወያኔዎች። ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚገርመው: መንግስት የሆነ አካል ቻይና የተበደለን አዳማጭ፣ ፍትህ ሰጭ መሆን ሲገባው ፣ ገዳዩም አሳሪውም ፈራጁም መንግስት መሆኑ እንቆቅልሽ ይሆንበታል። ይሄው አካል ቅንጣት ያህል ርህራሄ በሌለው የንጹሃን የሰው ልጅን ክቡር ሂዎት በማጥፋት ይህንንም እንደሚቀጥልበት በራሱ ልሳን የቲቪ መስኮት የተገደሉ ወጣት አኙዋኮችን ሬሳቸውን ከመሳሪያ ጋር በማሳየት እኛ ደም የጠማን ርካሽ አውሬዎች ነን ይሉናል። ከአውሬም አውሬ ሽብርተኞች ናቸው። በርግጥም ነው ከወደ ባህርዳር ከተማ የክልሉ ተወላጆች በአማራነታችን ምክንያት ከቤንሻንጉል ክልል ተባረርን ለስደት፣ ለእንግልት፣ ለርሃብ ተዳረግን፣ የወላጅ መካን ተበራከተ፣ እኛስ ይሁን ለጋ ህጻናት በምን በደላቸው፣ ሀጺያታቸው ይንገላቱ? እባካችሁ ለወገናችን አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አቤት ልንል በደላችንን ልናሰማ በሄድን ቤንሻንጉል ሄዳችሁ እንደገና ጠይቁ፣ አይመለከተንም፤ አሁን ግቢውን ለቃችሁ ውጡ ተብለን በፌድራል ተዋከብን፣ ተደበደብን፣ የት እንሂድ? ተቃጠልን የሚል ስቃይም ሰምተናል። እንግዲህ ወገን የትኛውን ጩኸት፣ የትኛውን ስቃይ ትመርጣላችሁ? በክብር ነክ ስድብ ውርደት መኖር? በአሰቃቂ ጭፍጨፋ ግድያ እጃቸው በደም የተላወሰውን የወያኔን ጎራ ፉከራ ማየትና ከንፈርን መምጠት? ወይስ ለነጻነት ጮራ ፍንጠቃ፣ ለድምጽ አልባዎቹ ዜጎች ድምጽ ለመሆን ከሚታገለው የህዝባዊ ሃይሎች ጎራ መቀላቀል? መልሱን መልሱት። ግንቦት 7 ንቅናቄ ሀገርን የማዳን ተስፋን አርግዞ ረጅሙን ጉዞ በአንድ ርምጃ ጀምሮታል። የህዝባችን ሰቆቃ በየደቂቃዎች፣ በየሰእታቱ፣ በየቀናቱና ሳምንታቱ የምንሰማው የወገናችን የስቃይ ጣእር የድረሱልን ጥሪ ደወል ለሁሉም የሀገራችን ህዝብና ለነጻነት ታጋዮች ነውና እጅ ለእጅ ተያይዘን ለጥሪው እንድረስ። ከዚህ በላይ ውርደት፣ ስቃይ፣ እንግልት፣ ስደት፣ ሰቆቃ የምናስተናግድበት፣ የምንችልበት አንጀት የለንም። የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ በእኛ ይብቃ ብለህ ትግሉን ተቀላቀል። ዜጎች ፍትህን በሰውነታቸውና በዜግነታቸው ሳይሆን በመደብ ጀርባቸው፣ በዘርና በጎጥ ማንነታቸው በችሮታ የሚሰጥበት የወያኔ ዘመን ላይ ነን። የጋምቤላና የተቀረው ህዝባችን በወያኔ ጥይቶች እየተገደሉ ሲሰደዱ፣ ንብረት አልባ ሲሆኑ፣ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ሲሆንባቸው፤ በአንጻሩ የወያኔ ጀሌ አጫፋሪ የሆኑ የስርአቱ አገልጋዮች የህወሃት ሰዎች 90 ፐርሰንት በግል ኢንቨስተርነት ታዋቂ ናቸው። ይህ የሚያሳየው የአንድ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭነት አይሎ መንግስት የህዝብ ንብረት ቀማኛ ዘራፊ መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ የዜጎች ሂዎት በእብሪተኞች መቀጠፉ እንዲበቃ፣ እንዲያቆም ወያኔን እንታገለው ዘንድ የወጣቱን ህዝባዊ ሃይል የመቀላቀል ጊዜ አሁን ነው። ሀገራችን መንግስት አልባ ሆናለች፣ ሀገራችን በወንበዴዎች እየተመራች ነው። በሀሰት ወንጃዮች፣ በሀሰት አሳሳሪዎች፣ አዘራፊዎችና ዘራፊዎች፣ አሰቃዮች የነገሱበት ሰአት ላይ ነች ኢትዮጵያ! ስለዚህ ፍትህን ከተቀበረችበት የማውጣት ጥሪ በድጋሜ ይድረሳችሁ። ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ቀድሞውንም የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህ የማግኘት ተስፋው በወያኔ ተቀብሯል ብሏል። ዛሬ ወያኔ በሀገራችን ፍትህን በመግደል እየዘራ ያለውን አደገኛ መርዝ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ አስቸጋሪ በመሆኑ፤ ላንመለስ ወደኋላ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል፣ የፍትህ ቡራኬን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማቃበል፣ ዲሞክራሲን ለማስፈን ወያኔን አስገድዶ ለማስወገድ ትግሉን ጀምረናል። ወንጀለኞችን ወደፍርድ አደባባይ ለማቅረብ፣ ለድምጽ አልባዎቹ ድምጽ ለመሆን የጥሪ ድምጻችንን ሰምታችሁ ኢትዮጵያዊ የሞራል ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ በራችን ክፍት ነው።ኑ እንታገለው፡፡ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Fifty-nine uprooted people killed in car accident Ethiomedia; March 27, 2013

BENISHANGUL GUMUZ - Fifty-nine people were killed on Monday when their Isuzu truck overturned, Ethiopian Satellite TV (ESAT) reported on Tuesday. Children and women were among the victims who perished when they were evicted from the Benishangul-Gumuz Region because they were ethnic Amhara, and couldn't live in the Benishangul-Gumuz region. Ethiopia has been a victim of a deliberate government policy that has fragmented the country - and hence the unity of the people - along ethnic lines. ESAT said 25,000 ethnic Amharas are on schedule to be uprooted from the Benishangul Areas into the Amhara region. Many rights groups consider the government actions as crimes against humanity. No medical help was rushed to the victims whose fate would have remained a mystery had it not been reported by a lone survivor. One of the poorest countries in the world, Ethiopia has the highest per capita rate of car fatalities in the world, with 190 deaths per 10,000 vehicles, according to a Newsweek report. Related Story

ወያኔዎች ተደናግጠዋል!! የአቶ ሃይለማርያም ማስጠንቀቂያ ለአክራሪ ህወሃቶች!!!

WEDNESDAY, MARCH 27, 2013 ወያኔዎች ተደናግጠዋል!! የአቶ ሃይለማርያም ማስጠንቀቂያ ለአክራሪ ህወሃቶች!!! ማስጠንቀቂያ ለአክራሪ ህወሃቶች!!! አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተከፈተው በር ሰተት ብለው መግባት አለባቸው:: በወያኔ ውስጥ የተደረገውን የስልጣን ሽግሽግ ተከትሎ አዳዲስ ለውጦች እየታዩ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የበላይነት ጎልቶ ለመውጣት እያቆበቆበ መሆኑን ከ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ ከአከባቢው የህወሃት አክራሪዎች መወገድ እና የአቶ ደብረጺሆን የግለኝነት አትኩሮት ለአቶ ሃይለማርያም እድሉን ገርበብ አድርጎ የከፈተላቸው ሲሆን የአቶ ደብረጺሆን ግለኝነት በሙስና ስም ሊደፈቅ እንደሚችል ያከባቢው ገማቾች ሲናገሩ ወታደራዊው አካል ራሱን ለማዳን ሲል በተጠንቀቅ ከሃይለማሪያም አዲስ ካበበው ቡድን ጋር እንደሚሰለፍ አንዳንድ ፍንጮች ታይተዋል:: አቶ ሃይለማርያም በሙሉ መንፈስ ባይሆኑም ድፍረት እንዳገኙ ከደቡብ ጉባዬ በሁዋላ እየታየ ሲሆን የደቡብ ባለስልጣናት አንድነት ወያኔን አስደንግጦታል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) የሕወሓት የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ባለስልጣናት በአቶ ሃይለማርያም ዙሪያ ጥያቄ በማንሳት ላይ ቢሆኑን በባህር ዳር በተደረገው ጉባዬ ላይ ያላቸውን የበላይነት እንዲያሳዩ ከፓርቲያቸው ግፊት እንደተደረገባቸው ምንጮች ጠቁመዋል::የደቡብ ባለስልጣናት አብዛኛዎቹ በግል አቶ ሃይለማርያምን በደቡቡ ጉባዬ ወቅን አግኝተው ያናገሯቸው ሲሆን በአንድነት ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እና ከሕወሓት የበላይነት እንዲላቀቁ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው መክረዋል::ለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚረዳቸው ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር አስታከው ተወያይተውል:: በህወሓት ውስጥ ያለው ፍትጊያ በአባይ ወልዱ የበላይነት ያበቃ ነው ብለን መደምደም እንደማንችል እና መሃል ሰፋሪ ሆነው ወዳሸናፊው ለማዘንበል የግለኝነት ሚና እየተጫወቱ ያሉት ደብረጺሆን ደቡቦችን አመቻችቶ መያዝ አስፈላጊ እንደሆን ስለተረዱት በሃይለማርያም ድፍረት ጀርባ ሆነው ጨዋታውን ማጋጋል ተይይዘውታል:: ምንጮቹ በአከባቢያቸው ያለውን ሁኔታ በማየት እንዳሉት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃይለቃል ጭምር የሚደፋፈራቸው የደህንነት አማካሪው አለቃ ጸጋይ ከፓርቲው መነሳቱን ተከትሎ በደብረጺሆን ተዘዋዋሪ ቁጥጥር ስር መሆኑን ከጠ/ሚ ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ እንደት ከስልጣን እንደሚባረር ታቅዶለታል::

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተከፈተው በር ሰተት ብለው መግባት አለባቸው

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተከፈተው በር ሰተት ብለው መግባት አለባቸው:: በወያኔ ውስጥ የተደረገውን የስልጣን ሽግሽግ ተከትሎ አዳዲስ ለውጦች እየታዩ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የበላይነት ጎልቶ ለመውጣት እያቆበቆበ መሆኑን ከ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ ከአከባቢው የህወሃት አክራሪዎች መወገድ እና የአቶ ደብረጺሆን የግለኝነት አትኩሮት ለአቶ ሃይለማርያም እድሉን ገርበብ አድርጎ የከፈተላቸው ሲሆን የአቶ ደብረጺሆን ግለኝነት በሙስና ስም ሊደፈቅ እንደሚችል ያከባቢው ገማቾች ሲናገሩ ወታደራዊው አካል ራሱን ለማዳን ሲል በተጠንቀቅ ከሃይለማሪያም አዲስ ካበበው ቡድን ጋር እንደሚሰለፍ አንዳንድ ፍንጮች ታይተዋል:: አቶ ሃይለማርያም በሙሉ መንፈስ ባይሆኑም ድፍረት እንዳገኙ ከደቡብ ጉባዬ በሁዋላ እየታየ ሲሆን የደቡብ ባለስልጣናት አንድነት ወያኔን አስደንግጦታል:: የሕወሓት የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ባለስልጣናት በአቶ ሃይለማርያም ዙሪያ ጥያቄ በማንሳት ላይ ቢሆኑን በባህር ዳር በተደረገው ጉባዬ ላይ ያላቸውን የበላይነት እንዲያሳዩ ከፓርቲያቸው ግፊት እንደተደረገባቸው ምንጮች ጠቁመዋል::የደቡብ ባለስልጣናት አብዛኛዎቹ በግል አቶ ሃይለማርያምን በደቡቡ ጉባዬ ወቅን አግኝተው ያናገሯቸው ሲሆን በአንድነት ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እና ከሕወሓት የበላይነት እንዲላቀቁ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው መክረዋል::ለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚረዳቸው ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር አስታከው ተወያይተውል:: በህወሓት ውስጥ ያለው ፍትጊያ በአባይ ወልዱ የበላይነት ያበቃ ነው ብለን መደምደም እንደማንችል እና መሃል ሰፋሪ ሆነው ወዳሸናፊው ለማዘንበል የግለኝነት ሚና እየተጫወቱ ያሉት ደብረጺሆን ደቡቦችን አመቻችቶ መያዝ አስፈላጊ እንደሆን ስለተረዱት በሃይለማርያም ድፍረት ጀርባ ሆነው ጨዋታውን ማጋጋል ተይይዘውታል:: ምንጮቹ በአከባቢያቸው ያለውን ሁኔታ በማየት እንዳሉት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃይለቃል ጭምር የሚደፋፈራቸው የደህንነት አማካሪው አለቃ ጸጋይ ከፓርቲው መነሳቱን ተከትሎ በደብረጺሆን ተዘዋዋሪ ቁጥጥር ስር መሆኑን ከጠ/ሚ ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ እንደት ከስልጣን እንደሚባረር ታቅዶለታል:: በስበሃት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋይ የነበሩት እና በአሁን ሰአት በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በማሰባሰብ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ እና ከሕወሓት ሰው ጠፍቶ ነው ወይ ከደቡብ ለትግሉ አስታውጾ ያላበረከቱ ሰዎች የሚመሩን ነገ ስጋት ሆኖብናል የሚሉ ታጋዮች ይህን ፕሮፓጋንዳ ይዘው በአቶ ስበሃት በኩል መሰለፋቸው በዚህ ሰሞን እንደገና ተረጋግቷል የተባለውን የወያኔ ክፍፍል እንደ አዲስ አግሎታል:: የሃይለማርያም ስልጣን መያዝ ያልጣማቸው አክራሪ ሕወሓቶች ከባህር ዳር መልስ አዲስ አበባ ውስጥ በስበሃት ነጋ ሰብሳቢነት አርከበ እቁባይ ;ብርሃነ ገብረክርስቶስ ;አዲሳለም ባሌማ;አባዲ ዘሙ ;አለቃ ጸጋይ በርሄ; ቅዱሳን ነጋ; ሃይለኪሮስ እና ሌሎችም ተሰባሰበው በህወሃት ውስጥ ስለለው ሁኔታ እና ራሳችን በፈጠርናቸው ደቡቦች ልንዋጥ ነው የሚል እደምታ ያለው ውይይት አካሂደው ነበር:; በአንድ ወገን ሆነው በአባይ ወልዱ መሪነት ብኣዴንን አስከትለው የስብሃትን ቡድን እየተዋጉ የሚገኙት አዜብ መስፍን እና ሌሎች..ሳሞራ የኑስን እንደመከታ አድርገው ቢተሙም ሳሞራ ሁኔታዎችን ከመከታተል ዉች ተሳትፎው የተልፈሰፈሰ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል:: የደቡብ ባለስልጣናት ወይም በስበሃት አጠራር የከተማ ጮሌዎች ወደ ከፍተኛ የስልጣን እርከን መምጣታቸው እያንገበገባቸው ሲሆን መለስ ዜናዊ ላልሰለጠኑ አናሳ ብሄሮች ሸጠን በማለት በሟቹ ላይ ከንፈር ነክሰው እየሞገቱ ሲሆን ይህም አልበቃ ብሎ ከድርጅታችንን መመሪያ እና ደንብ ዉጭ በተለያየ ቦታ የመለስን ምስል ማየት ሰለቸን በሚል ምስሉ እንዲነሳ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል ምናልባት ሁኔታዎችን ያረግብ ይሆናል በሚል አቶ አዲሱ ምስሉ እንዲነሳ ቢናገሩም አቶ በረከት ጠላት እና ወዳጅን አጥርቶ ለመለየት በሚል እንዲቆይ አድርገዋል.. የስበሃት ቡድን ዉስጥ ውስጡን በትግራይ ለሚገኙ የሕወሓት የበታች አመራሮች እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ ለሚገኙ የህወሓት መኮንኖች በሚያሰራጩት ፕሮፓጋንዳ በበረሃ ወንድም እና እህት ታጋዮችን ሰውተን ደማችንን አፍሠን የልጅነት ወዛችንን ጨርሰን ለዚህ የደረስነው ለደቡብ ሰዎች እና ለከተማ ጮሌዎች ስልጣን ለመስጠት አይደለም አብረውን የታገሉ ኦሆዴዶች እንኳን ያላገኙትን ስልጣን ነው ያገኙት በማለት እና ለነገ የፖለቲካ ኪሳራ ያመጡብናል የሚያዘነብሉት ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ነው ለኛ አደጋ ስለሆኑ ከአሁኑ ልናሶግዳቸው ይገባል በማለታቸው የወያኔ የውስጥ ቀውስ ግሎ ይገኛል:: በአሁን ሰኣት የደህንነት መዋቅሩን እና የጦር ሰራዊቱ ባለስልጣናት አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት እየሰሩ የሚገኙት ደብረጺሆን አቶ ሃይለማርያም ያላቸውን ሃይል ተጠቅመው የወሳኝነት ሚና እንዲጫወቱ እያደፋፈሯቸው ሲሆን ከጎናቸው እንደሚሆኑ እና ምንም እንደማይመጣ እየመከሯቸው ሲሆን ለሁለት አመት ነው ያስቀመጥንህ የሚለውን የአለቃ ጸጋይ ዛቻ ከአሁን በኋላ ሰሚ የሌለው ጩሀት እንደሆነ መናገራቸውን ምንጮቹ አስቀምጠዋል:: የደቡብ ባለስልጣናት ማሰብ/ድፍረት መጀመር; የህወሃት ክፍፍል መጋል; የኦህዲድ አህያዊ ሞኝነት; የብኣዴን በዝምታ ነገሮችን መከታተል; የኢሕኣዴግ ባልተጠበቀ መልኩ ቀውስ ውስጥ መግባት እና ሌሎች ተደማምረው የወያኔን ውድቀት የሚያመላክቱ ሲሆን በሃገሪቷ ላይ የፖለቲካ ለውጥ እንዲኖር ለማየት የሚጓጓውን ህዝብ ስል ነቀል ለውጥ እንዲያደርግ መስራት ደሞ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ነው:: MINILIK SALSAWI

የኢሕአዴግ ጉባዔ ---- የጫካ ፖለቲካን በሰለጠነ ፖለቲካ መተካት ! አማኑኤል ዘሰላም

የኢሕአዴግ ጉባዔ ---- የጫካ ፖለቲካን በሰለጠነ ፖለቲካ መተካት ! አማኑኤል ዘሰላም amanuelzeselam@gmail.com መጋቢት 17 2005 ዓ.ም ሰሞኑን በመንግስት መገናኛ ሜዲያዎችና አንዳንድ ጋዜጦች የምንሰማዉና የምናነበው «በኢሕአዴግ ዉስጥ እየተካሄደ ነዉ» የሚባለውን የመተካካት ሂደት ነዉ። «ኢሕአዴግ አንጋፋ አመራሮቹን አሰናብቶ 9ኛ ጉባኤዉን እያካሄደ ነዉ» በሚል ርእስ ሪፖርተር አንድ ዘገባ በእሑድ መጋቢት 15 2005 ዓ.ም እትሙ አቅርቧል። ኢሕአዴግ የአራት ግንባሮች ስብስብ ነዉ። ከነዚህ አንዱ በአቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም የሚመራው ደኢሕዴን ሲሆን፣ አንዳችም የአመራር ለዉጥ አላደረገም። ከጥንት ፣ ከጅምሩ የምናወቃቸው እንደ አቶ አዲሱ ለገሰ፣ በረከት ሰምኦን የመሳሰሉቱ አሁን በአመራር ላይ ናቸዉ። «ብአዴን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ቁጥር ከመጨመር ውጪ ምንም ዓይነት የአባላት መተካካት አላደረገም፡፡ መተካካት በብአዴን ውስጥ አለመካሄዱ አስገራሚና የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል» ሲል ነበር ሪፖርት የዘገበዉ። አቶ ግርማ ብሩ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳና አባ ዱላ ከሥራ አስፈጻሚነት ወደ ማእከላዊ ኮሜቴ አባልነት ከመወርዳቸው በስተቀር፣ ይሄ ነዉ የሚባል የመተካካት ለዉጥ በኦሕድድ ዉስጥ አልታየም። እንደ ብአዴንና ደኢሕዴንም በኦሕድድ የተሰናበተ የአመራር አባል የለም። እርግጥ ነዉ ወደ ሕወሃት ስንዞር ትንሽ የተለየ ሁኔታ እናያለን። እንደ አቶ አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ብርሃነ ክርስቶስ የመሳሰሉ አንጋፋ የሕወሃት አመራር አባላት ተሰናብተዋል። ከ12 በላይ የሚሆኑ ጫካ ያልነበሩ፣ አዳዲስ አባላት ወደ አመራሩ ተካተዋል።

ጥቃት በየተራ እስከመቼ?

ጥቃት በየተራ እስከመቼ? March 7, 2013 | Filed underG7 Editorial,Slider Post | Posted by admin ባለፉት 21 የወያኔ የግዛት አመታት አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንደሆነ እንጅ ጥቃት፣ ግፍ፣ በደልና እብሪታዊ የመብት ገፈፋ ያልደረሰበት ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ክፍል የለም። ገበሬው፣ የመንግስት ሰራተኛው፣ የፋብሪካ ሰራተኛና በየዘርፉ የእለት ጉርሱን አሳዶ የሚኖረው ሁሉ የወያኔን የሰቆቃ ግፍ በትር በየተራ አይቶታል፣ እያየውም ይገኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት አንጀቱ ለፍቶ ያቋቋማቸው ተቋሞቹ እየፈራረሱ ለወያኔ አገዛዝ እንዲመቹ ሆነው ሲጨፈላለቁም አይተናል። ወያኔ ይህን ሁሉ ያደረገው “አንዱን በአንዴ” በሚል ስልት ነው። መምህራንን ሲያጠቃ የፋብሪካውን ሰራተኛ ተመልካች ያደርገዋል፤ ገበሬውን ሲያጠቃ ከተሜውን ዝም ይለዋል፤ ከተሜው ላይ ሲዘምት ገበሬው ተመልካች ይሆናል፤ ቤተክርሰቲያን ላይ ሲዘምት ቤተ ሙስሊሙ ይመለከተዋል፤ የቤተ ሙስሊሙ የበደል ተራ ጊዜ ቤተክርስቲያን ተመልካች ትሆናለች። ይህ ወያኔን እስከዛሬ ያደረሰው ስልት ነው። አራዊታዊው የወያኔ አገዛዝ በተመቸውና ይጠቅመኛል ብሎ በአሰበ ሰአት ሁሉ የውብ ህዝብነት ምልክታችን የሆነውን የባህልና የቋንቋ ስብጥርነታችንን እርስ በርስ ለማናከሻነት ሊጠቀምበትም ሞክሯል፤ በተወሰነ ደረጃ አልሰራላቸውም ማለት ያስቸግራል፡፡ ወያኔዎች ከፋፍሎ መግዛትንና በየተራ ማጥቃትን በኪነ ጥበብ ደረጃ አሳድገነዋል ብለው ያምናሉ። በህዝብ ወገን ያለነውም የዲሞክራሲና የነጻነት ሃይሎች ለዚህ አልተመቸንም ማለት ያስቸግራል፡፡ ይህንን ከፋፍሎ የማጥቃት ግፍ በጋራ ለመመከት ያደረግነው ጥረት ህዝባችን ላይ እየደረሰ ካለው ጥቃት ጋር ቢያንስ የሚመጣጠን አይደለም። የወያኔ መሪዎች ዛሬ ስልታቸውን በማሻሻል አደገኛ ጭዋታ በቤተ እምነቶቻችን ዙሪያ መጫዎት ጀምረዋል። የቤተክርስቲያን እና የአቢያተ መስጊዶችን አስተዳደር በካድሬዎቻቸው ለመቆጣጠር ከሚያደርጉት ሳይጣናዊ ተግባር በተጨማሪ ህዝቡ ሃይማኖት ለይቶ እንዲባላ ለማድረግ በእጅጉ የሚቀፍ ፕሮፖጋንዳ እያካሄዱ ነው። ፍጹም ምሳሌያዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሲቪል መብት ጥያቄ እንደባዕድ መሳሪያነትና እንደ ሽብርተኝነት ለማሳየት እየሞከረ ይገኛል። በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙሉ እጁን በማስገባት የተጀመረውን እርቀ ሰላም በማፍረስ የራሱን እንደራሴ ሰይሟል። ይህም አልበቃ ብሎት ለዘመናት በመከባበር የኖረውን ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን እርስ በርስ ለማጋጨት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ዛሬ ከመቸውም በበለጠ ሀገራችን ወደማትወጣው አደጋ እየተገፋች ነው። ይህንን ወያኔ ያዘጋጀልንን የክፍፍልና ግጭት ድግስ ለመመከት ይበልጥ በአንድነት የምንቆምበት እና የምንታገልበት ግዜ ዛሬ ነው፡፡ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለወያኔ የ”ከፋፍለህ በየተራ ቀጥቀጥ” ፖሊሲ መድሃኒቱ አንድ ሆኖ በአንድነት አሻፈረኝ ብሎ መነሳት መሆኑን ያምናል፡፡ ወያኔ ጉልበቱ የኛ መከፋፈልና ለክፍፍሉ መመቸት መሆኑን ያምናል፡፡ እኛ ስንተባበርና ልዩነታችንን ለመጠቀም የሚያደረገውን ሙከራ ስናከሽፍና አንዱ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሁላችንም ነው ብለን የተነሳን እለት ወያኔ የለም። ግንቦት 7 ንቅናቄ ወያኔ በፈቃዱ የማይታረም ፋሺስታዊ አምባገነን መሆኑን ከተረዳ ሰንብቷል። በመሆኑም ወያኔን በማስገደድ ወይም በማስወገድ ነጻነታችንን መቀዳጀትና ነጻ ሀገር እንዲኖረን ማድረግ አለብን ብለን እናምናለን። ለዚህ ትግልም ማንኛውንም መሰዋእትነት ለመክፈል ተነስተናል። ነጻነትና ኮርተህ በነጻነት የምትኖርባት ሀገር እንድትኖርህ የምትወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተቀላቀለን። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

የወያኔ/ኢህአዴግ ጉባኤ ውሃ ቢወቅጡት እሞቦጭ

የወያኔ/ኢህአዴግ ጉባኤ ውሃ ቢወቅጡት እሞቦጭ March 21, 2013 | Filed underG7 Editorial,Slider Post | Posted by admin ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይና በተለምዶ ተለጣፊ እየተባሉ የሚጠሩት ሎሌ ድርጅቶቹ ሰሞኑን በጉባኤ ሽርጉድ ላይ ተጠምደዋል። የድግሱ፣ የፌስታውና የካርኔባሉ አይነትና ብዛት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት በሚቸገሩበት ሀገር ውስጥ የሚደረግ አይመስልም። ይሔው የፈረደበት የኢትዮጵያ ድሃ ግብር ከፋይ ይህን በብዙ መቶ ሚሊየኖች ብር የሚቆጠር ወጭ ይሸፍናል። ማን ከልካይና ጠያቂ አለ? ሌሎች በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች ለአንድ ደቂቃ እንኮን በአጠገቡ ዝር እንዳይሉ የሚከለክለው የመንግስት ሚዲያ ይህንን የግፈኞች የውሸት ዲስኩርና ፌሽታ በቀን 24 ሰአት ያጋፍራል። እንጨት እንጨት የሚል ፕሮፖጋንዳ ሊግተን፣ ሊያደነቁረን ይታገላል፡፡ ልብ ብሎ ለተመለከተው ጠቅላላው የወያኔ የጉባኤ ሽርጉድ ከጆርጅ ኦርዌል “የእንስሳት እርሻ” (Animal Farm) የስላቅ ድርሰት ተወስዶ የሚሰራ ትያትር ይመስላል። የወያኔ መሪዎችና ሎሌዎቻቸው ለሆድ አደሮች እግዚያብሄር እንደ ፀጋ ሰጥቷቸዋል። እፍረትና ይሉኝታ የሚባል ነገር ከልክሎ ፈጥሯቸዋል። ትዝብት አይፈሩም። ህዝቡ አንጀቱ እያረረ እብሪታቸውን ሲመለከት በደስታ ፈንድቆ የሚጨፍር ይመስላቸዋል። ኢትዮጵያን ወደ ፖሊሲያዊ መንግስትነት ቀይሮ የሞተውን አለቃቸውን ለአፍሪካና ለአለም የሚያጎድል መሪ ነው ይሉናል።
አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ” ፍኖተ ነጻነት መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡ በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው? አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ አቶ ታዲዎስ ታንቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡ ተቃወቅሞውን ለማቅረብ ያነሳሳችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን ነበር? አቶ ታዲዎስ፡- ብዙውን ጊዜ እኔ በጋዜጦች ስለ አርበኞች ታሪክ ያነበብኩትንና ያወቅሁትን እፅፋለሁ፣ እመረምራለሁ፡፡ የጣሊያኑ ፋሽስት ግራዚያኒ ሀገራችንን በመውረር በአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አሰቃቂ እንደነበር ስለተረዳሁ፤ ያ ሲቆጨኝ ደግሞ አሁን በጣሊያን ሀገር ለእሱ ሙዚየምና ሐውልት የመሰራቱን ወሬ ከኢንተርኔት ምንጮች ስላየሁ በጣም ተናድጄ እንደውም ተቃውሞ ማሰማት አለብን ብዬ ተነሳሁ፡፡ በኋላ ደግሞ እኛም የአንተ ዓይነት ሐሳብ ነበረን ብለው የባለ ዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር አነጋገሩን፡፡ ከዛ በመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንስራ የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያት ሶስቱ አካላት በጋራ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ጣሊያን ሀገር ጨረቃም ላይ ቢሆን ሀውልት እንዲሰራ አንፈቅደም፡፡

ኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የመደራደር አቅማቸው (ክፍል 1) በዳዊት ተ. ዓለሙ ምንጭ፣ ዞን ዘጠኝ ጦማር

የፖለቲካ ፓርቲዎች የመደራደር አቅም (Bargaining power) ለዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ ስርአት ግንባታም ሆነ በዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ላይ ተመስርቶ ለሚደረጉ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ስኬታማነት ወሳኝ ነው:: ሁሉን የፖለቲካ ቡድኖች ያማከለ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ምስረታም ሆነ የተቋማቱ ዘላቂነት በዋናነት የሚወሰነው የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚኖራቸው የመደራደር አቅም ልክ ነው:: ሚዛናዊ ያልሆነ የመደራደር አቅም ባላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መሀካል በሚደረግ ስምምነት የሚፈጠሩ ተቋማትና ስርዓቶች በአመዛኙ ሊያስጠብቁ የሚችሉት ይበልጥ ጠንካራ የመደራደር አቅም ያለውን የፖለቲካ ኃይል ፍላጎቶች ነው:: ይበልጥ የዴሞክራሲ ስርአት ሰፍኖባቸዋል በሚባሉ ሀገራት ውስጥ በትንሹ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑና የተቀራረበ የመገዳደር አቅም ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚገኙባቸው ናቸው:: የተቀራረበ የመገዳደር አቅም ባላቸው ፓርቲዎች (መሪዎች) ድርድር የሚመሰረቱ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት በአብዛኛው የሁሉንም ፖለቲካ ኃይሎች ፍላጎቶች የማንጸባረቅ እዳላቸው የሰፋ ነው:: ለምሳሌ ያህልም ሮበርት ፑትናም Making Democracy Work ብሎ በሰየመው የምርምር ስራው ለ20 አመታት የኢጣሊያንን ፖለቲካ በቅርብ ከተከታተለ በኋላ ይህንን እውነታ በሰፊው አመልክቷል:: ስለዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቀራረበ የመደራደር አቅም ለሰላማዊ ፖለቲካና ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ወሳኝ ነው:: በሀገራችን የፖለቲካ ቡድኖች (ፓርቲዎች) የመደራደር አቅማቸው የማይመጣጠን በመሆኑ የመገዳደር ፖለቲካ ባህላችን በአፈሙዝ የበላይነት የሚደመደምበት እንዲሆን አድረጎታል:: በዚህም የተነሳ በየወቅቱ ሲገነቡ የነበሩት ተቋማት በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን ጥቅምና ህልውና የሚያስጠብቅ ባህሪና ቁመና የተላበሱ ሆነዋል:: የፖለቲካ ፓርቲ እሳቤና ተሞክሮ የሀገራችን የፖለቲካ ባህል ከተዋወቀበት ጊዜ አንስቶ የተመሰረቱ ፓለቲካ ፓርቲዎች ሁሉም ሊያስብል በሚችል መልኩ የመደራደር አቅማቸው በጉልበት ላይ ወይም በተወሰ ጉዳዮች ላይ ብቻ የተነጠለጠለ ነው::

Refugee from Ethiopia sings in front of Parliament in Oslo

Endal Getaneh, a refugee from Ethiopia sings a hymn of hope in front of Parliament in Oslo.
Norway is the first and only European countries signed an agreement on the return of refugees to the authoritarian regime in Ethiopia. Amnesty International, Human Rights Watch and several other human rights organizations in a strongly critical of the agreement.
Many of the Ethiopian refugees are actively politically in opposition to the Ethiopian regime. They fear for their lives, torture and imprisonment forcibly returned to Ethiopia.

አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች “እንቅልፍን” በተመለከተ አማኑኤል ዘሰላም



አማኑኤል ዘሰላም
amanuelzeselam@gmail.com
መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓ.ም
«የተቃዋሚ ድርጅቶች ሰላማዊ ትግል ? ወይንስ ሰላማዊ እንቅልፍ ?» በሚል ርእስ፣ ስማቸዉን ያልጠቀሱ
አንድ ኢትዮጵያዊ የጻፉትን ጽሁፍ አነበብኩ። አገር ቤት ባሉ «የተቃዋሚ ፓርቲዎች ነን» በሚሉ
ድርጅቶች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ ነዉ። አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች እያሉ፣
 እስከመቼ ሕዝብ መብቱና ነጻነቱ ተረግጦ እንደሚኖር ያሳሰባቸው ይመስላል። ተቃዋሚዎች በሥራ ላይ
ሳይሆን በእንቅፍል ላይ እንዳሉም በመግልጽ ተቃዋሚዎቹ ሊመስልሱት የሚገባ ጥያቄዎችን
አስቀምጠዋል።1
«የሕዝብ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንታገላለን የሚሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ምን እየሰሩ ነው? ሕዝብን
አስተባብረው ወደሚፈለገው ለውጥ መጓዝ ያልቻሉበትስ ምክንያት ምንድነው?» የሚሉት ጥያቄዎች
በዋናነት የተቀመጡ ናቸዉ፡፡
ይመስለኛል እኝህ ጸሃፊ በዉጭ አገር የሚኖሩ፣ በሕዝባቸው ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደረሰ ባለዉ ግፍ
ያዘኑና የተቆጡ፣ አገራቸዉን የሚወዱ ኢትዮጵያዊ መሰሉኝ። ጊዜ ወስደው፣ ካላቸው አገራዊ ተቆርቋሪነት
የተነሳ፣ ይህን መልካም ጽሁፍ ስላበረከቱልን ምስጋናዬንና አክብሮቴን ላቀርብ እወዳለሁ።
ስለተቃዋሚዎች በምናነሳበት ጊዜ ተቃዋሚዎችን በተለያዩ ክፍሎች ልንመድባቸው እንችላለን። መስክረም
2005 ፕ/ር አል ማርያም “Ethiopia’s opposition at the dawn of democracy?” በሚል
ጽሁፋቸዉ ተቃዋሚዎችን ጽሁፋቸዉ ተቃዋሚዎችን በአምስት ከፍለዋቸዋል። በአምስት ከፍለዋቸዋል። በአምስት ከፍለዋቸዋል። ታማኝ ተቃዋሚዎች፣ ዝምታን የመረጡ ወይም ዝም
እንዲሉ የተገደዱ ተቃዋምዊዎች፣ ያልተደራጁ ተቃዋሚዎች፣ የተከፋፈሉ ተቃዋሚዎች፣ አንድ ሆነው
መርህ ያላቸዉ ዴሞክራቲክ ተቃዋሚዎች። ፕ/ር አል ማሪያም ከዘረዘሩት አምስቱ በተጨማሪ፣
 በስድስተኛነት ፣ በዉጭ አገር ያሉትን ተቃዋሚዎች እጨምራለሁ። እንግዲህ የትኛዉ አይነት ተቃዋሚች
እንደሆኑ ሳንለይ፣ በጅምላ በተቃዋሚዎች ላይ ትችት ማቅረብ ትንሽ የሚያስቸግር ይመስለኛል።
በዉጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎች በዉጭ አገር ያሉ ተቃዋምዊች ናቸው። ከሕዝቡ እንደመራቃቸው፣
 ሕዝብን መርተዉና አደራጀተዉ የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣት ይችላሉ ብሎ ማሰብ ትንሽ አሰቸጋሪ
ነዉ። አንዱ ትግሉን የጎዳዉ ትልቁ ችግር፣ አገር ቤት የሚኖረዉ ሕዝብ፣ በነዚህ ዉጭ አገር ባሉ
ድርጅቶች ላይ ብቻ ተስፋ ማድረጉ ነዉ። በስፋት ትግሉን በአገር ቤት ከመቀላቀል ይልቅ፣ ዉጭ ያሉ
ድርጅቶች ታግለዉና ተዋግተዉ ነጻ እንዲያወጡት ይጠበቃል። ይህ ትልቅ ስህተት ነዉ።
እዉነትን እና የተጨበጠ መረጃ ይዘን የምንነጋገር ከሆነ፣ እንኳን የሚጠበቀዉን ለዉጥ፣ ፈረንጆች
እንደሚሉት በሪሞት ኮንትሮል ከሩቅ ሆኖ ሊያመጣ ቀርቶ፣ ጭላንጭል ተስፋ የሚሰጥ ድርጅት በዉጭ
አገር አለ ለማለት ይቸግራል። (ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ ) መሰረቱን አሰመራ ያደረገዉ የግንቦት
ሰባት እና የኦነግ ትብብር፣ እንደ ኢሕአፓ-ዴ ያሉ ድርጅቶችን ያቀፈው ሸንጎ፣ በነዶር እሸቱ የሚመራዉ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት የመሳሰሉ በዉጭ አገር በርካታ ድርጅቶች አሉ። እናውቃቸዋለን።
አብረዉን ነዉ ያሉት። ጥረታቸውን ድካማቸውን እናከብራለን። ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች ፍቃደኛ
ሆነዉ፣ ከአገር ቤት የተነጠለ ትግል ምንም ሊያመጣ እንደማይችሉ ተረድተዉ፣ አገር ቤት የሚደረገዉን
1
http://www.ethiomedia.com/addis/selamawi_enqilf.pdfሰላማዊ ትግል በማገዝ አስተዋጽኦ ሊያብረክቱ ይችላሉ እንጂ በራሳቸዉ ምንም ሊያመጡ አይችሉም።
ይሄን ሐቅ ኢትዮጵያዉን በጥንቃቄ መገንዘብ ያለብን ይመስለኛል።
አገር ቤት ወዳሉት ተቃዋሚዎቾ ስንመለስ፣ ፕ/ር አል ማርያም እንዳሉት ታማኝ ተቃዋሚዎች አሉ።
እነዚህ ለይስሙላ «ተቃዋሚዎች አሉ ለማስባል» በገዢዉ ፓርቲ የተጠፈጠፉ የዉሽት ተቃዋምዊች
ናቸው። የአየለ ጫሚሶን ቅንጅት እንደምሳሌ መጥቀስ እንችላለን።
ታማኝ ተቃዋሚ ያልሆኑ፣ ነገር ግን እንደሚገባው ያልተደራጁ ፣ በመካከላቸው ክፍፍል የነበረባቸዉና
ያለባቸዉ በርካታ የተቃዋሚ ድርጅቶች አሉ። የአንድነት ፓርቲ፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የመላዉ ኢትዮጵያ
አንድነት ድርጅት፣ አረና ትግራይ የመሳሰሉ ፣ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች የመከፋፈሉን እና
የመደራጀቱን ጉዳይ ትኩረት ሰጥተዉት በአንድ ላይ ለመስራት ጥረት እያደረጉ ነዉ። የጋራ የመግባቢያ
ሰነድ ፈርመዉ፣ የዲሞክራሲ ተቋማት ጻና ገለልተኛ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግል
ጀምረዋል። እንግዲህ ይህ በአንድነት ለመስራትና ለመንቀሳቀስ የሚደረገዉ ጥረት በራሱ ትልቅ ሥራ
ነዉ።
እህል ሳይዘራ አይታጨድም። ሳይታጨድ አይወቃም። ሳይወቃ አይፈጭም። ሳይፈጭ አይቦካም።
ሳይቦካም አይጋገርም። ብዙዎቻን የምንጠበቀው ዉጤት እንዲመጣ ከፈለገን፣ ብዙ መሰራት ያለብን ሥራ
አለ። በአቋራጭና በአንዲት ጀንበር ድል አይገኝም። አገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች አይመስለንም
እንጂ፣ በዉጭ አገር ያሉ ሜዲያዎች እየተከታተሉ በስፋት አይዘግቡትም እንጂ፣ እጅግ በጣም ከባድና
ዉስብስብ በሆነ ሁኔታ ሕዝቡን ለማደራጀትና ለማስተማር እየሞከሩ ነዉ። አቶ በቀለ ገርባ የኦፌኮ
አመራር አባል ናቸዉ። በእሥር ቤት ይገኛሉ። አቶ አንዱዋለም አራጌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል
ናቸው። በእሥር ቤት ይገኛሉ። ወ/ት ርዮት አለሙ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ቅርበት ያላት ናት። በእሥር ቤት
ትገኛለች።
«የተቃዋሚ ድርጅቶች አያሌ አባሎቻቸውና መሪዎቻቸውንም ጨምሮ በወያኔ የሃሰት ውንጀላ በየ እስር
ቤቱ ውስጥ ታጉረው እየማቀቁ ቢሆኑም ድርጅቶቹ ህዝብን አስተባብረው ጫና በመፍጠር ለማስፈታት
ያደረጉት ሙከራ የለም» ሲሉ ከላይ የጠቀስኳቸው ጸሐፊ ትችት አቅርበዋል። አንድ የዘነጉት ጉዳይ ቢኖር
ግን ፣ እነዚህ ዜጎች መጀመሪያዉኑ የታሰሩት፣ ድርጅታቸው ሥራ እየሰራ ስለነበረና መታሰራቸውም
ከሥራ የተነሳ እንደሆነ ነዉ። ጸሃፊዉ እንዳሉት፣ ሕዝብ ሆ ብሉ መሪዎችን ለማስፈታት እንዲነሳ ደግሞ
መደራጀት አለበት። ህዝብን ለሰላማዊ ትግል ለማደረጀት መረጃ ቁልፍ ነዉ። ያለ መረጃ ፣ ያለ ንቃት
ሕዝብን ማደራጀት አይቻልም። ሕዝብ ከፍርሃት እንዲላቀቅ፣ በራሱ እንዲተማመን ለማድረግ ሕዝብን
ማስተማርና ማሳመን የግድ ነዉ። የአንድነት ልሳን የሆነችዉ የፍኖት ጋዜጣም በአገዝዙ እንዳትታተም
እስከተደረገችበት ጊዜ ድረስ፣ በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫዉታለች; የፍኖት ጋዜጣ አዘጋጆችም ሆነ
የአንድነት ፖርቲ አመራር አባላት ፣ ሊታሰሩ እንደሚችሉ እያወቁም፣ ሳይፈሩ መረጃዎች ለሕዝብ
ለማቅረብ ሞክረዋል። ይህ አይነቱ ሕ ይህ አይነቱ ሕዝብን የማስተማርና የማንቃት እንቅስቃሴ ሌላዉ ዝብን የማስተማርና የማንቃት እንቅስቃሴ ሌላዉ ዝብን የማስተማርና የማንቃት እንቅስቃሴ ሌላዉ ትልቅ ሥራ ነዉ ትልቅ ሥራ ነዉ ትልቅ ሥራ ነዉ።
ገዢዉ ፓርቲ ግን በብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ፍኖት እንዳትታተም አደረገ። የአንድነት ፓርቲ ግን ዝም
ማለትን አልመረጠም። ጫና በበዛ ቁጥር ግፊቱን ቀጠለ። የፍኖት ማተሚያ ማሽንን ለመግዛት እንቅስቃሴ
ላይ ይገኛል።
ከአንድነት ፓርቲ ጋር በቅርበት የሚሰራ አንድ የፖለቲካ ድርጅት አለ። ሰማያዊ ፓርቲ ይባላል። (በጣም
ተስፋ አደርጋለሁ ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድነት ፓርቲ ጋር እንደሚዋሃድ) ሰማያዊ ፓርቲ ፣ አገራዊ አጀንዳ
አንግቦ ከ30000 ሺህ በላይ ለሆነው ወገናችን ደም መፍሰስ ምክንያት የነበረዉ፣ የግራዚያኒ ሓዉልትን
በተመለከተ፣ በአዲስ አበበ ስድስት ኪሎ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ነበር። የዜጎች የመሰብሰብ መብት በአገዛዙ
ተረግጦ፣ ከአርባ በላይ ኢትዮጵያዉያን ታስረዉ ነበር። ዶር ያእቆብ ኃይለማሪያም እንዲሁም በርካታ
የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ወህኒ በመውረድ የአገዛዙን አምባገነንነት አጋልጠዋል። ለካቴና
እጆቻቸዉን በመስጠት ለሕዝቡ ድፍረትን በተግባር አስተምረዋል። ይሄ ትልቅ ሥራ ነዉ። ይሄ ትልቅ ሥራ ነዉ።በዋቢ ሸበሌ በተደረገ ሥነ ስርዓት፣ ገንዘብ ከፍለዉ እንዳይገቡ የታገዱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና
ደጋፊዎች፣ ከሆቴሉ አስተዳደር ጋር ሲከራከሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በበርካታ ድህረ ገጾች ተለቆ አይተናል።
የተወሰኑ ወደ ሆቴል ቤቱ ሲገቡ ፣ የተወሰኑቱ ግን እንዳይገቡ ሲከለከሉ ነዉ ያየነዉ። ምን ያህል
የአፓርታይድ አይነት ሥርዓት በአገራችን እየተስፋፋ እንደሆነ ነዉ በይፋ ለማረጋገጥ የተቻለዉ።
ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ እኩል የሆነች ሳይሆን፣ አንዱ የሌላዉ የበላይ ሆኖ፣ አንዱ ሌላዉን እየረገጠና
እየጨቆነ የሚኖርባት አገር እንደሆነች ነዉ፣ የሰማያዎ ፓርቲ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያስተማረዉ። ይሄም
እራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ እራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ ነዉ።
እንግዲህ እነዚህን ምሳሌ የምጠቀሰው «በአገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ያንቀላፉ ናቸዉ» ለሚለዉ
የተሳሳተ አባባል እርማት ለመስጠት ነዉ። የድርጅቶች ልሳኖች እንዳይታተሙ እያታገዱ፣ ያን አልፎ
በመሄድ የማተሚያ ማሽን ለመግዛት ጥረት እየተደረገ፣ ኢትዮያዊ አጀንዳዎች ተይዘው ተቃዉሞ
ለማሰማት እየተሞከረ፣ በዚያም ምክንያት ዜጎች እየታሰሩ ምንም ነገር አልተሰራም ማለት ትንሽ
ያስቸግራል። ያለ ማጋነን፣ በዉጭ አገር አለን ከሚሉና በብዙ ሺህ ዶላሮች ከሚደገፉ ድርጅቶ ጋር
ሲነጻጻሩ፣ አገር ቤት ያሉ ደርጅቶች ከሃያ በላይ እጥፍ ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ ናቸዉ።
ይህን ስል መሰራት የነበረባቸውን ሥራዎች በብቃት ሰርተዋል ማለቴ አይደለም። ይህን ስል መተቸት
የለባቸውም ማለቴ አይደለም። በቅርቡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያቀረባቸውን ጠንካራ ገንቢ ትችቶች
መመልከት ይቻላል። በርግጥ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ብዙ ማስተካከል ያላባቸዉ አሰራሮች፣
መስራት ያላባቸዉ ተግባራት አሉ።በተለይም መድረክ የሚባለው ስብስብ ትልቅ ችግር አለበት።
ነገር ግን አልተሰሩም የምንላቸውን ተግባራት ለምን አልሰሩም ብለን ዳር ሆነን ከምንከስ፣ ለምን መሰራት
ያላባቸውን እንዲሰሩ አናግዛቸውም ባይ ነኝ። አገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ አመራር አባላት ብቻቸዉን
ሁሉንም ሊሰሩ አይችሉም።
ሕዝቡን ለማደራጀት ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራት ይጠይቃል። ለዚህም ቴለቭዥን፣ ራዲዮ፣
ጋዜጣ፣ ኢንተርኔት የመሳሰሉ አስፈላጊ ናቸዉ። በአገራችን ቴሌቭዥኑን እና ራዲዮዉን እንርሳው ። ገዢዉ
ፓርቲ ከቻይና ባገኘዉ ቴክኖሎጂ በቀላሉ አፈና በማድረግ መረጃዎች ለሕዝብ እንዳይደርሱ ማድረግ
ይችላል። ኢንተርኔትን በተመለከተ ከሶማሊያና ከኬንያ በባሰ መልኩ ኢንተርኔት በኢትዮጵያ እንዳያድግ
ተደርጓል። የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ክፍል ከ0.1 % ያነሰ ነዉ። በመሆኑም በፌስቡክ በመሳሰሉ
ሜዲያዎች በብቃት የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለመስራት ያስቸግራል።
የቀረዉ እንድ መንገድ ጋዜጣ ነዉ። ይችኑ የቀረችዋን ለማፈንም ገዢው ፖርቲ ማተሚያ ቤቶችን
 በመጠቀም ነጻ ጋዜጦች እንዳይወጡ እያደረገ ነዉ። ፍትህ ጋዜጣ ተዘግታለች። ፍኖት ጋዜጣ አትታተም።
የአንድነት ፓርቲ ግን ዝምታን አልመረጠም። እየተንቀሳቀሰ ነዉ። የማተሚያ ማሽን ገዝቶ ሕዝብን
ለማስተማርና ለማደራጀት እየጣረ ነዉ። እንግዲህ ከኛ የሚጠበቀዉ የሥራዉ አካል መሆን ነዉ።
የማተሚያ ማሽኑን ለመግዛት 50 ሺህ ዶላር አካባቢ ያስፈልጋል።በዉጭ አገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ 2
ሚሊዮን ይጠጋል። 50 ሺ የሚሆኑቱ አንድ ዶላር፣ 5 ሺህ የሚሆኑቱ አሥር ዶላር፣ 5 መቶ የሚሆኑቱ
አንድ መቶ ዶላር፣ አምሳ የሚሆኑቱ አንድ ሺህ ዶላር ቢያዋጡ ይሄ ማሽን በቀላሉ ሊገዛና ለጥቅም
ሊዉል ይችላል። አንድ ተብሎ ነዉ ወደ ሁለት የሚኬደው። መቶ ሜትር መሮጥ ሳንችል የማራቶን ወርቅ
መጠበቅ የለብንም። መደመር ሳይቻል ማባዛቱ የማይሞከር ነዉ።
እንግዲህ አገር ቤት ያሉ ትግሉን ወደፊት እንዲወስዱ እንደምንጎተጎታቸው ሁሉ፣ እኛም የድርሻችንን
ለመወጣት እንዘጋጅ። ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት !

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው


የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው


ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡
የትምህርት ጥራት መጓደል፣ የአስተዳደራዊ ችግሮችና በምግብ ጥራት መጓደል ምክንያት ጥያቄያቸውን ለኮሌጁ አስተዳደር ቢያቀርቡም ምላሽ በማጣታቸው የትምህርት መቆም አድማ ለማድረግ የተገደዱት ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሀብ ተጎድተው ራሳቸውን በመሳት በመጀመራቸው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰድ መጀመራቸውን ስምቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡
ፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛም በቅድስት ስላሴና በየሆስፒታሎቹ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው አባ እያሱ ሰብስቤ የተባሉ ተማሪ በየካቲት 12 ሆስፒታል እንዲሁም ደቀመዝሙር በኃይሉ ሰፊ ምኒሊክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን አረጋጧል፡፡ አመሻሹ ላይም ገ/እግዚያብሄር የተባሉ ተማሪ በአምቡላንስ ከኮሌጁ ተወስደዋል፡፡ ተማሪዎቹ በደል አድርሰውብናል ከሚሉዋቸው የኮሌጁ ሀላፊዎች ውስጥ መምህር ፍስሀፂዮን ደሞዝ አካዳሚክ ዲን እና መምህር ዘላለም ረድዔት የቀን ተማሪዎች አስተባባሪ በዋነኝነት ተጠቅሰዋል፡፡
ደረሰ ስለተባለው ችግር ለማጣራት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፁዕ አቡነ ህዝቅኤል በኮሌጁ ጉዳይ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ተናግረው የነበረ ቢሆንም ተሰብሳቢ ባለመሟላቱ ስባሰባው እንዳልተደረገ ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

Sunday, March 24, 2013

ስዩም መስፍን፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና አርከበ ዕቁባይ ከሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴአባልነት ተሰናበቱ፡፡



የኢህአዴግ አራቱ አባልድርጅቶች በሳምንቱ ውስጥ ባካሄዷቸው ጉባኤዎች የየድርጅቶቹንማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና የኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚዎችን መርጠዋል፡፡ እንዲሁም ዛሬመጋቢት 14ቀን 2005 .ም በባህርዳር በሚከናወነውየኢህአዴግ /ቤት መደበኛጉባኤ ላይየሚሳተፉ አባላቶቻቸውን እንደመረጡ ለመረዳት ተችሏል፡፡በዚህ መሰረትሕወሐት በፊት የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አባይወልዱ በሊቀመንበርነትእንዲቀጥሉሲወስን፣ በምክትል ሊቀመንበርነት ደግሞ/ ደብረፅዮን ገብረሚካኤልንመርጧል፡ በጉባኤው ለዓመታት ያህል በፓርቲውበማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነትሲያገለግሉከቆዩ ነባር አባላት ውስጥ አምባሳደስዩም መስፍንን፣ አምባሳደር ብርሃነ/ክርስቶስን፣ አቶ አርከብ እቁባይን እናአቶ ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ ዘጠኙባቀረቡትጥያቄ መሰረት ከማዕከላዊኮሚቴ አባልነታቸው ተሰናብተዋል።

ኢህአዴግ ከ700 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ ቅስቀሳ አደረገ

ትናንት ሀሙስ መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓም የኢህአዴግ መንግስት 740 በላይየጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ስድስት ኪሎ በሚገኘው ስብሰባ ማእከል ለአንድ ሙሉ ቀንበመሰብሰብ በመጪው የአዲስ አበባና አካባቢ ምርጫ ኢህአዴግን እንዲመርጡቀስቅሷል። ለእያንዳንዱ ተሳታፊ 100 ብር ከመስጠት በተጨማሪ  የምሳ፣ የቡና እናየሻ ግብዣም አድርጓል።የጎዳና ተዳዳሪዎች ትናንት 230 ላይ ነጭ ቲሸርትለብሰው እና  የኢህአዴግ አርማ ያለበት የወረቅት ኮፍያ አድርገው ወደ ስብሰባውአዳራሽ የገቡ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይ  ኢህአዴግ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ካለፉትመንግስታት በተሻለ እንደሚያስብላቸው፣ የሙያ ስልጠና ሲሰጣቸው መቆየቱን እናበዚህም እንቅስቃሴ ለቁም ነገር የበቁ የጎዳና ተዳዳሪዎች መኖራቸውን ገልጿል።
የጎዳና ተዳዳሪዎችን ማሰልጠንና በአንድ አካባቢ አሰባስቦ የማኖር እቅድ እንዳለውምኢህአዴግ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ገልጿል። አንዳንድ የጎዳና ተዳዳሪዎች ”በምርጫተሳትፈን ስለማናውቅ እንዴት እንደምንመርጥ አናውቅም  ቀኑንም አናውቅም፣ማንን እንደምንመርጥም አናውቅም ” በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ “መቼ እና ማንንእንደምትመርጡ እኛ እናሰለጥናችሁዋለን፣ እናሳውቃችሁዋለን፣ ኢህአዴግንከመርጣችሁ ችግሮቻችሁ ይፈታሉ” በማለት መድረኩን ይመሩ የነበሩ ባለስልጣናትመልሰዋል።

“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል

“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ባንኮችና የተለያዩ ግለሰቦች በትዕዛዝ አክሲዮን መግዛታቸውን ያስታወሱት እኚሁ ዲፕሎማት “በግድቡ ዙሪያ ከሚፈራው የጸጥታ ችግር በላይ አስጊው ጉዳይ የባለድርሻዎች ምስጢር መሆን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።መንግስት ለግንባታው የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ከአውሮፓዊቷ አገር ማግኘቱን ያመለከቱት የጎልጉል ምንጭ፣ “ከአገር ውስጥ በአክሲዮን ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአገር ውስጥ በጀት ማሟያና ለመንግስት የስራ ማከናወኛ የሚውል ነው” ብለዋል።