የርዕዮት ሽልማትና የእኛ ዝምታ
ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮትአለሙ የቤተሰቦቿ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኗ መጠንሃላፊነት ነበረባት፡፡ይህንን ሃላፊነት ለመወጣትም ርዕዮት ከማስተማር ሞያዋጎንለጎን በትርፍ ጊዜዋ ህጻናትን ታስተምር ነበር፡፡ከዚህ የሚገኘው ገቢ ደግሞየቤተሰቡን ኑሮ ይደጉማል፡፡በሩጫ የተሞላው የጋዜጠኛዋህይወት በአንድ ማለዳቀለም ወደ ምትመግባቸው የምስካዬ ህዙናን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍልለመግባት ስትዘጋጅ የእስር ማዘዣባወጡባት የፌደራል ፖሊሶች እጅ ወደቀች፡፡ርዕዮት ታስራለችና ቤተሰቡ ከእርሷ ያገኘው የነበረውን ድጉማ ማጣቱ ግድ ሆነ፡፡
አምላክ ሳይደግስ አይጣላምእንደሚሰኘው እስከዳር የርዕዮትን ፍኖት በመከተልየቤተሰብ ግዴታዋን ለመወጣት በሞያዋ ስራ ማፈላለጉን ተያያዘችው፡፡እናም ተሳካ፡፡በጥሩደሞዝ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጠረች፡፡ይህ ከርዕዮት መታሰር በኋላለቤተሰቡ የተደመጠ የመጀመሪያው መልካም ዜና መሆኑ ነው፡፡ቹቹ(የእስከዳርየቤት ስም ነው)ባገኘችው አዲስ ስራ ብዙም መቀጠል አልቻለችም፡፡ቀጣሪዋ ወደቢሮው ጠርቷት‹‹የሆኑ ሰዎች ትናንት አንቺከቢሮ ከወጣሽ በኋላ መጥተው ነበር፡፡
ይህቺን ልጅ ካላስወጣችኋት ድርጅታችሁ ከመንግስት አንዳች ነገር ቢፈልግ ትብብርአይደረግለትምብለውኝ ወጡ፡፡ስለዚህ እባክሽ ምን እናድርግ?››እስከዳርአላመነታችም‹‹ምንም ችግር የለም በእኔ ምክንያት እናንተ መጉላላትየለባችሁምስለዚህ ስራውን መልቀቅ እችላለሁ››ቢሮውን ለቅቃለት ወጣች፡፡ከትንሽመውጣትና መውረድ በኋላ ቹቹ ሌላ ስራ አገኘች፡፡የዚህን ስራየአንድ ወር ደሞዝእንኳን መብላት ሳትችል አሰሪዋ ‹‹ውጪልኝ ሰዎች መጥተው ከእሷና ከድርጅትህአንዱን ምረጥ ብለውኛል ››አላት፡፡እየሳቀችስራውን ለቀቀችለት፡፡
በቅርቡ ግን ያጋጠማትለየት ያለ ነው፡፡ጥሩ ስራ በመገኘቱ ያለሽን የትምህርትና የስራልምድ አስገቢ ተብላ በጓደኞቿ በመወትወቷ ነገ ሊያሥወጡኝ በሚልስሜት ወደተባለው ቦታ አመራች፡፡ለስራው ብቁ የሚያደርጋትን ማስረጃ አስገብታ ከገባችበትቢሮ ስትወጣ አንድ ጉስቁስቁል ያለ ወጣትከአፉ የሚያወጣቸውን ቃላት ጠንከርናረገጥ እያደረገ‹‹አትልፊ እኔ እያለሁ አንቺ ስራ አትቀጠሪም››ብሏት ሊቀጥራትወዳናገራት ድርጅትመሰስ ብሎ ገባ ይሄው ድርጅቱም እስካሁን ድረስአልደወለላትም፡፡ቹቹ አሁን በዚህች አገር ሰርታ መኖር እንዳትችል የሆነየፈረደባትአካል እንዳለ ማመን በመጀመሯ ከአሁን በኋላ ስራ ፍለጋ እግሬን ንቅንቅአላደርገውም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሳለች፡፡
ብዙዎቻችን እንደምናውቅየርዕዮት አባት አቶ አለሙ የህግ ባለሞያ ናቸው፡፡ልጃቸው ቃሊቲ ከመውረዷ በፊት የተለያዩ የፍርድ ቤት ጉዳዩችን በመያዝ ገቢአግኝተዋል፡፡አሁንግን ጥብቅና እንዲቆሙላቸው የሚጠይቁ ደምበኞች ወደእርሳቸው ቢሮ እንዳይመጡ አንድ ስውር እጅ ሆነ ብሎ እየቀሰቀሰባቸውይገኛል፡፡‹‹እርሳቸውየሚይዙት ጉዳይ ፍርድ አያገኝም››ወደ አቶ አለሙ ቢሮለማምራት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚነገር ማሸማቀቂያ ነው፡፡እናም የስራ ነገርለአቶአለሙ አሁን እጅግ ከባድ ሆኗል፡፡
የርዕዮት የሞያና የፍቅርአጋር የሆነው ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ ከእጮኛው መታሰርበፊት ህይወትን ለማሸነፍ በሁሉም አቅጣጫ የሚታትር ብርቱ ነበር፡፡ ቃሊቲፍቅሩንከነጠቀችው በኋላ ግን የህይወት ትግሉ ላይ በረዶ እንደተደፋበት ስሜቱቀዝቅዟል፡፡የጸሀይ ብርሃንን የፈራ ያህል ለቃሊቲ ጉዞ ካልሆነበቀር ከቤቱመውጣትን አይፈቅድም፡፡የርዕዮት መታሰር ስንቱን እንዳሰረ አያችሁን?
እርግጥ ነው እኛ ኢትዮጵያዊያንጀግኖች እንዲወለዱ እንጸልያለን እንጂ የተወለዱትጀግኖች መከራ በደረሰባቸው ጊዜ አብረናቸው አንቆምም፡፡ርዕዮት፣እስክንድር፣ውብሸት፣አንዷለም፣ናትናኤልናሌሎቹም ከራሳቸው ርቀው ስለ ህዝብ በመጮሃቸውየቃሊቲ ደጃፍ ተቆልፉባቸዋል፡፡የእነዚህ ሰላማዊ ታጋዮች መታሰርበቤተሰቦቻቸው፣በሚረዷቸውሰዎችና በልጆቻቸው ላይ ከሚያደርሰው የህሊና እናየስነ ልቦና ቀውስ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ምስቅልቅሉ በቃላት ሊገለጽ የማይችልነው፡፡የታጋዮቹአሳሪዎችም ከምንም በላይ የህዝቡን አለመደጋገፍ የሚገነዘቡበመሆናቸው የሚያቀርቡት የመጀመሪያ ጥያቄ‹‹ለምን ለልጆችህ ለመኖርአትፈልግም››የሚል ነው፡፡
የውብሸት ልጅ ውብሸትበመታሰሩ ምክንያት ለትምህርት ቤት የሚከፍልለት አጥቶወደ ዝቅተኛ ትምህርት ቤት እንዲሸጋገር መደረጉ ስድቡ ውብሸትንአደንቀዋለሁለምንለው እኛ እንጂ ለእርሱ አይደለም፡፡ይህንን እያዮና እየሰሙእንዴት ሌሎች ውብሸቶች ይፈጠሩ?ውብሸት የታሰረ ሰሞን እኔና ጋዜጠኛነብዮሀይሉ ከውብሸት ጋር አብሮ ይሰራ የነበረን አንድ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣባልደረባ ቀጥረን አገኘነውና‹‹ውብሸት በመታሰሩቤተሰቡ ችግር ላይ ሊወድቅይችላል፡፡ስለዚህ ለምን የሆነች መዋጮ በማድረግ የምንችለውን አናደርግም››አልነው፡፡ምላሹ ያልጠበቅነውነበር‹‹መንገስት እርሱን መንግስት ያሰረውበሽብርተኝነት ጠርጥሮት በመሆኑ አሁን እገዛ ብናደርግ እኛንም ተባባሪ ሊያደርገንይችላል››አለን፡፡ውብሸትይቅርታ ጠይቆ ሊወጣ ነው በተባለ ሰሞን ይህ ጋዜጠኛየፌስ ቡክ ገጹን በውብሸት ፎቶግራፍ ሞልቶ ማየቴም እፍረት አሳድሮብኝ ነበር፡፡
ለማንኛውም ዛሬ ማለዳያደመጥኩት ዜና ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ፈጥሮብኛል፡፡ፈረንጆች ለእኛ የመብት ተሟጋቾች እውቅና በመስጠት ሽልማት እያበረከቱ ነው፡፡በዚህመነሻነትም ርዕዩት ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ በከፈለችው መስዋዕትነት የተነሳየ25.000 ዶላር አሸናፊ ሆናለች፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር በርዕዮት ዙሪያ ላሉ ሰዎችበሙሉ ይህትልቅ ማበረታቻ ነው፡፡እናም የርዕዮት እህት፣ አባትና እጮኛበመሆናቸው ብቻ ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን በሙሉ በዚህ አጋጣሚ እንኳንደስ አላችሁማለት ወደድኩ፡፡ከወሬ የዘለለ ማድረግ ላልቻልን ከቃሊቲ በመለስ ላለን ለእኛ ግንአፈርኩ፡፡
ከዳዊት ሰለሞን
No comments:
Post a Comment