Friday, October 17, 2014

የስሞኑ የወያኔ ነጠላ ዜማ !!!! ማን ነበር ባንዲራ ጨርቅ ነው ያልው?

                                         
             ሰሞኑን የወያኔ ባለስጣንና ካድሬዎቻቸው ሰንድቅ አላማን አልማክበር ቡዙሃንነትን አለመቀበል ነው የብሄር ብሄረስቦችን መብትና ጥቅም ካለመቀበል የተፈፀመ ነው በማልት ከመንግስት ኮሚኬሽን ጽ ቤት ሚንስትሩ አስክ ጠቅላይ ሚንስትሩ እየተቀባበሉ ብሔር ብሔረስቦች በሚል ማጭበርበርያ ሲያራግቡት ከርመዋል
አቶ መለስ ከዚህ በፊት አንዴ ሲዘቀዝቁት አንዴ ባንድራ ጨርቅ ነው ሲሉት የነበረውን ባንዲራ የሞቱ ግዜ ይባስ ብሎ ከአስክሬን ጋር እንዲቀበር ተደረገ አይ ይሄ ሚስኪን ባንዲራ

በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንድቅ አላማ ላይ የብሔሮች መፈቃቀድ የሚገልፅ አርማ መኖር አለብት አርማውስ ምን አይነት ይሁን የሚል ሐሳብ ያቀርባሉ የታሪክ ፕሮፌስር የሆኑት ላጲሶ ጌ ዴሌቦም ሐሳባቸውን አንድሚክተልው ሰንዘሩ  የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ተጨቁኖ የኖረ ህዝብ ነው ሰለዚህ ሰንደቅ አላማ ላይ የሚቀመጠው ዓርማ ይህን ጭቆናውን የሚገልጽ መሆን አለበት ለዚህም ደግሞ  ከአህያ  ምሰል የተሻለ  አርማ የለም ህዝቡ ለዘመናት አምባገነንነት ተጭኖበት በጭቆና ውስጥ ነበርና

ፍትህ እኩልነት ከመንግሥትም ይሁን ከማንም ነፃ የሆነ ዳኝነት ፍትሀዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል እንዲሁም እኩል የሆነ የሥራ እድል ሣይኖርና ጥቂት ካድሬና ወሮበሉችን ለሚያገለግል ሥርአት ባንዲራ ምኑ ነው!? ሥለጨርቅ ከምትለፈልፍ ትላንት በወገኖቻችን ላይ የደረሠን ግፍ ሥንቃወም ሥለተደበደቡት እንዲሁም በግፍ ከነበሩበት ወያኔ ራሡ በሸረበው ሤራ ሥለተጎዱ ሠዎች ብትጨነቅ ምን ነበር ይህ ሥርአት ሆድ እንጂ ህሊና በሌላቸው ሠዎች ሥለተሞላ ከዚህ የተሻለ ነገር አንጠብቅም ባንዲራውን ያወረዱት ወያኔንም ያወርዱታል!!! በሕዝባዊ እንቢተኝነት ወያኔም የሚወርድበት ግዜ አሩቅ አይሆንም።

የወያኔ ባለስልጣንና ካድሬዎቻቸው የተለወጠው ባንዲራው ሳይሆን አርማው መሆኑን ሳይውቁት ቀርተው ሳይሆን አሸባሪ የሚለውን ነጠላ ዜማ በየግዜው በመልቀቅ ህዝቡን በፕሮፖጋንዳ ለማወናበድ የሚያደርጉት ሙከራ ነው፦

 ዳንኤል አምዶም

No comments:

Post a Comment