የጎዳና ተዳዳሪዎችን ማሰልጠንና በአንድ አካባቢ አሰባስቦ የማኖር እቅድ እንዳለውምኢህአዴግ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ገልጿል። አንዳንድ የጎዳና ተዳዳሪዎች ”በምርጫተሳትፈን ስለማናውቅ እንዴት እንደምንመርጥ አናውቅም ፣ ቀኑንም አናውቅም፣ማንን እንደምንመርጥም አናውቅም ” በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ “መቼ እና ማንንእንደምትመርጡ እኛ እናሰለጥናችሁዋለን፣ እናሳውቃችሁዋለን፣ ኢህአዴግንከመርጣችሁ ችግሮቻችሁ ይፈታሉ” በማለት መድረኩን ይመሩ የነበሩ ባለስልጣናትመልሰዋል።
አንድንድ የጎዳና ተዳዳሪዎች ምንም አይነት ቋሚ አድራሻ እና የቀበሌ መታወቂያእንደሌላቸው የገለጹ ሲሆን ፣ ሰብሳቢው እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ተወክለውየመጡት የፖሊስ ባልደረባ ” ችግር የለም ስማችሁን በትክክል አስፍሩ እንጅበአቅራቢያችሁ በሚገኙ ቀበሌዎች የመታወቂያ ወረቅትይዘጋጅላችሁዋል ፣ ፎቶምትነሳላችሁ “የሚል መልስ ሰጠተዋቸዋል።
በእረፍት ሰአት ወጣቶች የተሰጣቸውን የታሸገ ውሀ በሲጋራ ሲለውጡ እና በርካሽዋጋ ሲሸጡ መታዘቡን ዘጋቢያችን ገልጿል።
በቅርቡ በሚካሄደው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ 33 የፖለቲካ ድርጅቶችለመሳተፍ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ይታወሳል። “አስገራሚው ነገር” ይላልዘጋቢያችን ሪፖርቱን ሲያጠቃልል፣ “የምርጫ ካርድ የመውሰጃ ጊዜ እንዳለፈከተነገረ ከወራት በሁዋላ የጎዳና ተዳዳሪዎች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱናእንደሚርጡ አሁንም እየተቀሰቀሱ ነው።”

ኢህአዴግ በ2002 ዓም ለተደረገው ብሄራዊ ምርጫ 52 ሚሊዮን ብርማውጣቱን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment