Wednesday, March 27, 2013

የኢሕአዴግ ጉባዔ ---- የጫካ ፖለቲካን በሰለጠነ ፖለቲካ መተካት ! አማኑኤል ዘሰላም

የኢሕአዴግ ጉባዔ ---- የጫካ ፖለቲካን በሰለጠነ ፖለቲካ መተካት ! አማኑኤል ዘሰላም amanuelzeselam@gmail.com መጋቢት 17 2005 ዓ.ም ሰሞኑን በመንግስት መገናኛ ሜዲያዎችና አንዳንድ ጋዜጦች የምንሰማዉና የምናነበው «በኢሕአዴግ ዉስጥ እየተካሄደ ነዉ» የሚባለውን የመተካካት ሂደት ነዉ። «ኢሕአዴግ አንጋፋ አመራሮቹን አሰናብቶ 9ኛ ጉባኤዉን እያካሄደ ነዉ» በሚል ርእስ ሪፖርተር አንድ ዘገባ በእሑድ መጋቢት 15 2005 ዓ.ም እትሙ አቅርቧል። ኢሕአዴግ የአራት ግንባሮች ስብስብ ነዉ። ከነዚህ አንዱ በአቶ ደሳለኝ ኃይለማርያም የሚመራው ደኢሕዴን ሲሆን፣ አንዳችም የአመራር ለዉጥ አላደረገም። ከጥንት ፣ ከጅምሩ የምናወቃቸው እንደ አቶ አዲሱ ለገሰ፣ በረከት ሰምኦን የመሳሰሉቱ አሁን በአመራር ላይ ናቸዉ። «ብአዴን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ቁጥር ከመጨመር ውጪ ምንም ዓይነት የአባላት መተካካት አላደረገም፡፡ መተካካት በብአዴን ውስጥ አለመካሄዱ አስገራሚና የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል» ሲል ነበር ሪፖርት የዘገበዉ። አቶ ግርማ ብሩ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳና አባ ዱላ ከሥራ አስፈጻሚነት ወደ ማእከላዊ ኮሜቴ አባልነት ከመወርዳቸው በስተቀር፣ ይሄ ነዉ የሚባል የመተካካት ለዉጥ በኦሕድድ ዉስጥ አልታየም። እንደ ብአዴንና ደኢሕዴንም በኦሕድድ የተሰናበተ የአመራር አባል የለም። እርግጥ ነዉ ወደ ሕወሃት ስንዞር ትንሽ የተለየ ሁኔታ እናያለን። እንደ አቶ አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ብርሃነ ክርስቶስ የመሳሰሉ አንጋፋ የሕወሃት አመራር አባላት ተሰናብተዋል። ከ12 በላይ የሚሆኑ ጫካ ያልነበሩ፣ አዳዲስ አባላት ወደ አመራሩ ተካተዋል።
እንደዚያም ሆኖ ግን እንደ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ አባይ ጸሐዬ፣ አቶ አባይ ወልዱ፣ ዶር ደብረጽዮን የመሳሰሉ፣ ቁልፍ ሃላፊነቶችን የያዙ፣ ትልቅ ዉስጣዊ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉ፣ በርካታ ነባር አመራር አባላት አሉ። በመሆኑም አዲስ የገቡ አመራር አባላት፣ የነባሮቹ ተከታዮች እንጂ የጎላ ሚና በራሳቸው ሊጫወቱ የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል ብሎ ማሰብ ትንሽ ያስቸግራል። እንግዲህ በግለሰቦች መተካካት ረገድ የምለውን በዚህ ላቁምና በዚህ ጽሁፍ ለማቅረብ ወደ ፈለጉት ዋና ሃሳብ ልመለስ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በነባር አመራር አባላት ላይ በግለሰብ ደረጃ ችግር የለዉም። ብዙዎቻችን በኢሕአዴግ ላይ ተቃዉሞ የምናሰማዉ መሪዎቹ ላይ ተቃዉሞ የምናሰማዉ መሪዎቹ አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ስዩም መስፍን ፣ አቶ አርከበ እቁባይ …ስለነበሩ አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ስዩም መስፍን ፣ አቶ አርከበ እቁባይ …ስለነበሩ አልነበረም። ችግራችን አልነበረም። ችግራችን የነዚህ ግለሰቦች ድርጅት ፣ የነዚህ ግለሰቦች ድርጅት ፣ የነዚህ ግለሰቦች ድርጅት ፣ ኢሕአዴግ የሚያራምዳቸዉ ፖሊሲዎቹ ላይ ነዉ። የሚያራምዳቸዉ ፖሊሲዎቹ ላይ ነዉ። በጠቅላላዉ የኢሕአዴግ አመራር አባላት በአዲስ አመራር አባላት ቢቀየሩም ፣ ኢሕአዴግ ጎጂና አፍራሽ የሆኑ ፖሊሲዎቹን እስካልቀየረ ድረስ ተቃዉሞ ማሰማታችንን፣ ኢሕአዴግን መታገላችንን አናቆምም። የ«መተካካቱ ፖለቲካ» መሰረታዊ የሆኑ የአስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት ለዉጦችን ካላመጣ ምን ዋጋ አይኖረዉም። ሕዝቡ እየጠየቀ ያለዉ «ማን ሚኒስቴር ሆነ ? የየትኛዉ ብሄርሰብ አባል የትኛዉን ስልጣን ያዘ ? ምን ያህል ትግሬ፣ ምን ያህል አማራ፣ ምን ያህል ኦሮሞ ተመረጠ ? የትኞቹ ነባር አመራር አባላት ለቀቁ ? …? የሚሉትን ጥያቄዎች አይደለም። «በየቀበሌዉና በየወረዳው ባሉ የኢሕአዴግ ካድሬዎች የሚደርሱ ግፎች መቼ ነዉ የሚያቆሙት ? ሃሳቤን በነጻነት በመግልጼ መቼ ነዉ ወደ ወህኒ መወርወሬ የሚያቆመው ? «የዚህ ብሄረሰብ አባል አይደለህም» ተብዬ ወይንም ለባለስልጣናት ጉቦ የሰጡ ኢንቨስተሮች ቦታዉን ስለፈለጉ፣ እስከመቼ ነዉ ከመንደሬ መፈናቀሌ የሚያቆመዉ ? የኢሕአዴግ አባል ስላልሆንኩኝ እስከመቼ ነዉ የዉጭ ትምህርት እድል፣ የሥራ ሹመት የመሳሰሉትን የማላገኘው ? ወይንም ከሥራዬ የምባረረው ? እስከመቼ ነዉ ዜጎች ባላጠፉት ጥፋት፣ ባልሰሩት ሐጢያት ፣ ሰላምን በመስበካቸው ሸብርተኛ ተብለው በወህኒ የሚማቅቁት ? እስከመቼ ነዉ በቀጥታ ከአራት ኪሎ ትእዛዝ እየተሰጣቸው ጥቁር ካባ የደረቡ ዳኛ ተብዬ የኢሕአዴግ ካድሬዎች ፍርድን የሚያዛቡት ? እስከመቼ ነዉ በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደሩ እንደ ኢቲቪ ያሉ የመገናኛ ሜዲያዎች በስድሳዎቹ በደርግ ጊዜ የነበረዉ አይነት ርካሽ፣ አሳፋሪና የኋላ ቀር ፕሮፖጋንዳ የሚረጩት ? እስከመቼ ነዉ ነጻ ጋዜጦች እንዳይታተሙ የሚታገዱት ? እስከመቼ ነዉ ዜጎች በሆቴል ቤቶች ስብሰባ እንዳያደርጉ የሚከለከሉት ? እስከመቼ ነዉ ጥቂት አራት ኪሎ ያሉ ባለስልጣናት «እኛ ብቻ ነን የምናውቅላችሁ» የሚሉን ? .. እና የመሳሰሉት ጥያቄዎችን ሕዝቡ እየጠየቀ ነዉ ያለዉ ። ሕዝቡ «ልማት፣ ልማት ፣ ልማት» የሚባለውን ቋንቋ መስማት እየሰለቸዉ ነዉ። አገራችን መልማት እንዳለባት ሁላችንም እናውቃለን። አራት ኪሎ ያሉት፣ እነርሱ የበለጠ አገር ወዳድ ሆነዉ፣ አገራችንን ማልማት እንደሚያስፈልግ እክስንደነቁር ድረስ ሊነግሩን አይችሉም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የልማት እንቅስቅሴን ይደግፋል። በርካታ የኢሕአዴግ ፖሊሲዎችን ቢቃወምም፣ ሕዝቡ ኢሕአዴግ ያስቀመጣቸውን የልምትና የትራስፎርሜሽን እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን፣ የተቻለዉን እያደረገ ነዉ። ዜጎች በፍቃደቸው የአንድ ወር ደሞዛቸዉን እያበረከቱ ነዉ። በዉጭ ያለዉም ኢትዮጵያዊ፣ እንደሚጠበቀዉ ባይሆንም፣ ቦንድ እየገዛ ነዉ። ክሊኒኮች ፣ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ኩባንያዎች በግል ኢንቨስተሮች እየተገነቡ ነዉ። ነገር ግን ኢሕአዴግ ልማትን በመጠቀም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚያደርገዉን ነገር ግን ኢሕአዴግ ልማትን በመጠቀም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚያደርገዉን ርክሽ ፕሮፖጋንዳ መቆም ርክሽ ፕሮፖጋንዳ መቆም አለበት። ይልቅ ለልማቱ ከሰጠዉ ትኩረት ባልተናነሰ ለዜጎች መሰረታዊ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ትኩረት መስጠት አለበት። ኢሕአዴግ በባህር ዳር በሚያደርገው ዘጠነኛ ጉባዔ፣ በአብዛኛው ስለ ልማት ብቻ አውርቶ፣ በሌሎች የፖለቲካ መስኮች ምንም አይነት መሻሻል ሳያደርግ፣ ለመቀጠል ዉሳኔ ሊያሳፍል እንደሚችል የሚገምቱ ጥቂት አይደሉም። እነዚህ ወገኖች እንደገመቱት ከሆነ ግን በርግጥ ኢሕአዴግ ትልቅ የታሪክ አጋጣሚ አመለጠው ማለት ነዉ። እርግጥ ነዉ ለሰው ልጅ ዋናዉ ቁምነገር በልቶ ማደሩ ነዉ። ጋዜጣኛ አበበ ገላው አንድ ወቅት አቶ መለስ በተካፈሉበት ስብስበ ላይ «ከምግብ በፊት ነጻነት» የሚል መፈክር አስምተዉ ነበር። ለምን እንደዚያ እንዳሉ ይገባኛል። ግን ይህን አስተያየት አልጋራም። «ዳቦም ነጻነትም» ቢሉ ኖሮ ያስኬድ ነበር። ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አንድ ወቅት ከቃሊቲ በጻፉት ጽሁፍ ደግሞ «ሰው ያለነጻነቱ ምንድን ነዉ ?» ነበር ያሉት። በሰው ዉስጥ ሶስት አካላት አሉ። ስጋ ፣ ነፍስና መንፈስ። በስጋዉ ሰው ከእንስሳ አይለይም። እንደ እንሳሳ ምግብ ካላገኝ ሰው በስጋዉ ይሞታል። ስለዚህ ምግብ ከሁሉ በፊት ይቀድማል። ነገር ግን ሰው በእግዚብሄር አምሳል የተፈጠረ ፣ የእግዚአብሄር መንፈስ ያለው እንደመሆኑ፣ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ነ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ነጻነት አለ። ይህ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ነጻነት አለ። ይህ ጻነት አለ። ይህ ነጻነት ነዉ፣ ነጻነት ነዉ፣ ሰዉን ሰው የሚያደርገዉ፣ በመንፈስም ከእንስሳ የሚለየዉ። ስለዚህ ለስዉ ልጅ ዳቦ ሰዉን ሰው የሚያደርገዉ፣ በመንፈስም ከእንስሳ የሚለየዉ። ስለዚህ ለስዉ ልጅ ዳቦ ለስጋው እንደሚያስፈልገዉም ነጻነት ለመንፈሱና ለነፍሱ ያስፈልገዋል። እንደሚያስፈልገዉም ነጻነት ለመንፈሱና ለነፍሱ ያስፈልገዋል። የኢሕአዴግ ጉባዔ ይሄን ተረድቶ፣ «ለሕዝቡ እንደ ዉሻ አጥንት ከወረወረንለት ይበቃል፤ ልማት ብቻ ካየ ይበቃል» ማለትን አቁሞ፣ መሰረታዊ የሆኑ ለዉጦችን ማስቀመጥ አለበት። በተለይም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ፣ በዚህ ረገድ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይገባቸዋል። ይችላሉም የሚል ተስፋ አለኝ። የቃሊቲና የተለያዩ ወህኒዎች ከሕሊና እስረኞች ነጻ መሆን አለባቸው። አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዋለም አራጌ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ወ/ት ርዮት አለሙ የመሳሰሉ ጋዜጠኞችና የሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በሙሉ መፈታት አለባቸው። የፈጸሙት ወንጀል ሆነ የሽብር ተግባር የለም። ከፍተኛው ፍርድ ቤት እነ እስክንድርን ወንጀለኛ ብሎ ፈረደ። እነ እስክንድር ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አሉ። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደዘገበዉ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት መሃል ዳኛ፣ አቶ አማረ አሞኘ ፣ አቃቢ ሕግ ያቀረባቸው መረጃዎች ዉሃ እንደማይቋጥሩ ይገልጻሉ። «ይህን ሰው (እስክንድር ነጋን) አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህምሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ» ይላሉ። አቃቢ ሕጎቹ በደፈናው «ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅናበት» የሚል ከሕግ ባለሞያ ስነ-ምግባር የማይጠበቅ የካድሬ ንግግር ለዳኛው ይናገራሉ። እንግዲህ ይህ በዳኛዉና በአቃቢ ሕጉ መካከል የምናየው ምልልስ የሚያሳየን እነ እስክንድር ነጋ አንዳችም አይነት ሕገ መንግስቱን የሚጻረር ወንጀል እንዳልፈጸሙ ነዉ። ሰኔ 15 ቀን 2004 የተደረገ ፣ በአቶ መለስ ዜናዊ የተመራ፣ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሰብሰባ ቃለ-ጉባዔን፣ የያዝ አንድ ሰነድ በድህረ ገጾች ተለቋል። ሰነዱ በርካታ ነጥቦችን የያዝ ቢሆንም የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ፣ በተለይም ስለሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተናገሩትን መጥቀስ እፈልጋለሁ። «««ኮሜቴው … ተቃዉሞዉ «ኮሜቴው … ተቃዉሞዉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥልና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ በተለይም ወደ አመጽ እንዳይሄድ ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተመለክቷል» በማለት ነበር እኝህ ባለስልጣን የታሰሩ ሙስሊም የኮሚቴ አባላት፣ ሰላማዊ እንደነበሩ የገለጹት። የሚያራምዱትን እንቅስቃሴዎች፣ የያዟቸውን የተለያዩ አጀንዳዎችንና አቋሞችን ላንደግፍ ወይንም ልንቃወም እንችላለን። ነገር ግን አቋሞቻቸውን በሰላም መግለጻቸው፣ የሚነሱት ጥያቄዎችም፣ ዶር ሽፈራዉ እንዳሉት፣ ወደ አልተፈለገ ደረጃ እንዳይደርስ ጥንቃቄ ማድረጋቸው፣ እንደ ሐጢያትና ሽብር ተቆጥሮ ወደ ወህኒ ሊያስወስዳቸው አይገባም ነበር። በመሆኑም የሙስሊም ኮሚቴዉ አባላት፣ በዶር ሽፈራዉ እንደተመሰከረላቸው፣ እነ እስክንድር ነጋም ዳኛ አማረ አሞኘም በግልጽ እንዳስቀመጡት፣ ሰላማዊ ናቸዉና፣ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው። ዜጎችን በማሰርና በማሰቃየት የሚገኝ ምንም መፍትሄ የለም። ዜጎችን ማሰር የጫካ ፖለቲካ እንጂ የሰለጠነ ፖለቲካ አይደለም። ሁለት በሉ። ሁለት በሉ። ኢሕአዴግ አገር ቤት ካሉ ድርጅቶች ጋር በአስቸኳይ ለመነጋገር መዘጋጀት አለበት። እንደ ምርጫ ቦርድ፣ እንደ ኢቲቪ የመሳሰሉትን ነጻና ገለልተኛ በማድረግ ሕዝቡ በዲሞክራሲ ሂደቱ ላይ እንደገና ተስፋ እንዲኖረው ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ የመፍጠር ሃላፊነት አለበት። አገር ቤት ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር መምከር መቻል አለበት። እልህና ግትርነት የትም አያደርሰንም። ሶስት በሉ። ሶስት በሉ። ኢንተርኔትን ማፈን፣ ነጻ ጋዜጦች እንዳይታተሙ ማድረግ የመሳሰሉ ጸረ-ዴሞክራሲያዊ ተግባራት በራስ ካለመተማመን የመነጩ፣ የኢሕአዴግን ድክመት የሚያሳዩ እንደመሆናቸው በዚህ ረገድ መሰረታዊ ለዉጦች ያስፈልጋሉ። የማስታወቂያ ሚኒስቴር የሚባለው መስሪያ ቤት መፍረስ አለበት። በምትኩ እንደ ቢቢሲ፣ ባለሞያዎች ያሉበት ኢቲቪን የኢትዮጵያ ራዲዮን እንዲሁም አዲስ ዘመን ጋዜጣ የመሳሰሉትን የሚያስተዳደር ገለልተኛ ቦርድ በማቋቋም ሕዝብ ነጻ መረጃ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል። አራት በሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢሕአዴግን አይጠላም። ኢሕአዴግ ድክመቶቹን አስተካክሎ ፣ ጎጂ ፖሊሲዎቹን ቀይሮ ከወጣ በሕዝብ ዘንድ ያስከብረዋል እንጂ ጉዳት አያመጣበትም። ይኸው ሕዝቡ፣ የልማት እንቅስቃሴዎችን ደግፎ ከኢሕአዴግ ጎን ቆሞ የለም እንዴ ? በሰብዓዊ መብት መከበር፣ በሕግ የበላይነት መስፈን፣ በዜጎች እኩልነት፣ በሜዲያ ነጻነት በመሳሰሉቱ፣ ኢሕአዴግ መሻሻሎችን ቢያደርግ ፣ እንዴት የበለጠ የሕዝብ ድጋፍ አያስገኝለትም ? እንግዲህ በዚህ የኢሕአዴግ ጉባዔ መተካካት ይኑር እላለሁ። አቶ አርከበ እቁባይን በወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያም መተካት ሳይሆን፣ የጫካ ፖለቲካን በሰለጠነ ፖለቲካ የመተካት እንቅስቃሴ ይጀመር እላለሁ።

No comments:

Post a Comment