አበዉ እንደሚሉት አቅሙን የማያዉቅ ሞቱን አፋጠነ እንደሚሉት በተቃዋሚዉ ባንጻሩ የሚታዉ ደሞ፤
1ኛ. እኛ ከወኔ ወኔ የለን፤ መስእዋትነት ለመክፈል ዝግጁነት የለንም
2ኛ. ከአንድነት አንድነት የለን
3ኛ. ከአቅም አቅም የለን
4ኛ. ነጻነትን በምጽዋት ለማግኘት እንፈልጋለን (በዉጭ ሃይሎች)፤ ሌሎች በታገሉትና መስእዋትነትበከፈሉት ተጠቃሚ መሆን እንፈልጋለን
5ኛ. የስርአቱ አራማጆች ወድቆ መነሳትን ሲችሉበት እኛ ግን የወደቅንበት ቀርተናል፤ ከዚህ በፊት በደረሱብንሽንፈቶች ለምሳሌ በቅንጅት ሽንፈት ተስፋ ቆርጠን ተበታትነናል
6ኛ. ጠላታችን ማን እንደሆነ ማወቅ ተስኖናል፤ ከስርአቱ ይልቅ እርስ በራሳችን ጦር መማዘዙን መርጠናል
7ኛ. በጭንቅላታችን ሳይሆን በስሜታዊነት የምንመራ ሆነናል፤ በአላማ ሳይሆን በጥላቻ የምንመራ ሆነናል
8ኛ. የረዥም ግዜ ዉጤት ሳይሆን አጭር ዉጤት እንፈልጋለን፤ በዚህም ምክንያት ቶሎ ተስፋ እንቆርጣለን
9ኛ. ሁሉም ፈላስፋ፤ አዋቂ፤ መፍትሄ ሰጪ ሆኖ፤ መደማመጥ ጠፍቷል፤ ሁሉም አዋቂ፤ ተናጋሪ፤ ሆኖየሚታገለዉ ግን ጥቂት ሆኗል – ወሬ ወሬ ወሬ -ሀሜት ሀሜት ሀሜት – ኩነና ኩነና ኩነና – ተናጋሪ ተናጋሪተናጋሪ – አድራጊ ጠፋ (የኢንተርኔት፡ ፓልቶክና ሬድዮ፤ ስብሰባ ታጋዮች ሆነናል)
10ኛ. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አብዛኛዉ ህብረተሰብ ያለዉን ስርአት በአያገባኝም ወይም በፍራቻ ወይንምበጥቅም ተቀብሎ አሜን ብሌ መገዛቱን መርጧል
11ኛ. ከዚህ በፊት በነበሩን ችግሮቻችን ተተብትበን ወደፊት መራመድ ተስኖናል
12ኛ. ሁሉም ጠያቂና ተሳዳቢ እንጂ ደጋፊ፡ አይዞኝ ባይ፤ አብሮ ታጋይ ጠፍቷል
13ኛ. ይሀ ሁሉ በእንዲህ እያለ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፤ ከዚህ በፊት ያልነበረ
አዲሱ ፈሊጥ ደሞ አዲሱን ጠቅላይ ሚንነስትር ጊዜ እንስጠዉ የሚለዉ ሆኗል፤ አይ መዘናጋት፤ ራስንማታለል፤ ሰዉየዉ እንደሆነ ለዉጥ እንደማይኖር እቅጩን ነግረዉናል።
14ኛ. የመቃወም ትርጉሙ ግራ ገብቶናል መቃወም ማለት ሁሉንም የምንቃወምበት በተለይም አዲስ ሀሳብአዲስ ራእይ የተለየ አካሄድ ይዘዉ ትግሉን የተቀላቀሉትን እንደጠላት ተረባርበን መማዉገዝና፤ እንደ እባብጭንቅላታቸዉን ቀጥቅጠን ያለ የሌለ ሀይላቸንን በመጠቀም አንገታቸዉን እናሰደፋለን፡ ሀሳባቸዉንእንዲሞክሩ እንኳን እድሉን አንሰጣቸዉም። በዚህም ድልን ተግናጽፈን ተደስተን እርስ በእርስ እየተጠፋፋንእንገኛለን።
በኛ ካምፕ
ወይ አንታገል
ወይ አናዋጣ
ወይ ዝም አንል
ወይ አንረዳዳ
ወይ አናዋጣ
ወይ ዝም አንል
ወይ አንረዳዳ
ነገሩ ሁሉ ግራ ሚያጋባ ዘመን ላይ እንገኛለን።
ሰላማዊ ሰልፍ ለመዉጣት ልመና
ስብሰባ ለመገኘት ልመና
ሰላማዊ ሰልፍ ለመዉጣት ልመና
ስብሰባ ለመገኘት ልመና
ለክብር፤ ለህሊና፤ ለነጻነት ለመታገል ለምኑኝ ሚባልበት ዘመን ላይ እንገኛለን።
ባንጻሩ ዘመን ተለዉጦ ስለ እዉነት መቆም፤ ለክብር፤ ለህሊና፤ ለነጻነት ለሀገር መታገል ሚያሳፍርበት፤ስለነጻነት መናገር ጀግና ወንድ፤ የሀገር ልጅ፤ ሀገር ወዳድ ማስባሉ ቀርቶ፤ እንደ ቁምጥና ሚያሳፍርበትናአንገት የሚያስደፋበት፤ ስለ ክብርም መናገር የሚያስኮንንበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡
ዛሬ ያልታደለችዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ ልጆችዎ በሁለት ተከፍለዋል
1) በአንድ ወገን ያለዉ ስርአት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንዲቀጥል አስተዋጽኦ እያደረጉ ያሉ አብላጫዎቹ (99.999%) ሲሆኑ
በዚህ ምድብ፡
1. የስርአቱ ዋና አራማጆች
2. ስርአቱን በመደገፍ በቆራጥነት የቆሙለት
3. ከማያዉቁት መላክ የሚያዉቁት ሴይጣን ይሻላል ብለዉ በፍራቻና አንገት በመድፋት የተቀመጡ፤
4. ስለ ኢትዮጵያ አያገባንም ከራሳችንና ጥቅማችን በላይ ነፋስ ብለዉ ክብራቸዉን፤ ስብእናቸዉንና፤ ህሊናቸዉንዘግተዉ ምን ያገባናል ብለዉ የተቀመጡ
5. ሌሎቹ ደግሞ መታገል እየፈለጉ ግን በፍራቻና ከዚህ በፊት በደረሰባቸዉ መከራ እምነት በማጣት ትግሉን እርግፍአድርገዉ ተስፋ ቆርተዉ የተቀመጡ
6. ባፋቸዉ ተቃዎሚ ነን የሚሉ ነገር ግን ለዘመናት ምንም ለትግሉ ስተዋጽኦ ሳያደርጉ ለመታገል የመጣዉን ሁሉነገር ግን በነሱ አመለካከት የማያምነዉን፤ ለነሱ ያላጎበደደዉን፤ ሁሉ በመቃወም የትግሉን ጎራ በማዳከምየስርአቱን እድሜ እያራዘሙ ያሉ የሚገኙበት ሲሆን
2) በሌላ ጎራ ደሞ ቁጥራቸዉ እጅግ አናሳ ቢሆንም ስርአቱን ሌት ተቀን በመታገል በሀገር ቤትና በዉጭበአላማ ጽናት፤ በወኔ በመታገልና መስእዋትነት እየከፈሉ ያሉ የቁርጥ ቀን ወገኖች ሲሆኑ ዛሬ ቁጥራቸዉ አናሳቢሆንም ዉለዉ አድረዉ ግን ማሸነፋቸዉ አይቀሬ ነዉ። ምክንያቱም እዉነት ከነሱ ጋር ናትና። እነዚህምዛሬ በየጫካዉ ለኛ ነጻነት እየተዋጉ፤ ለኛ ክብር ወህኒ ቤቶች ተወርዉረዉ የሚገኙ፡ ለኛ ክብር ባሉበት ቦታሁሉ ለሃገራቸዉ እየታገሉ ያሉትን ጀግና ዜጎች ሁሉ ያካትታል።
እነዚህ ዜጎች ሀገራቸዉን በቁርጥ ቀን ያልከዱ፤ ለእዉነት በመቆማቸዉ ህሊናቸዉን የማይቆረቁራቸዉ፤ ነገስማቸዉና ታሪካቸዉ ዘላለማዊ የሆነ፡ ነገ የልጅ ለጆቻችን የሚዘክሩላቸዉ ብርቅዬ ወገኖቻችን ናቸዉ።
ለሀገር የሚያኮራ ስራ ሰርቶ ስምና ዝና አትርፎ ከማለፍ በላይ ምን የሚያስደስት ነገር ይኖራል። ኖሮ ኖሮበልቶ፤ ተኝቶ፤ ማለፍማ እንኳን ሰዉ ተብዬዉ እንስሳም ያደርገዉ የለም። ዋናዉ ጥያቄ ግን እያንዳንዳችንየትኛዉ ምድብ ዉስጥ ነን የሚለዉ ሲሆን የህሊናዉን ሙግት ለናነተዉ እተዎለሁኝ።
ከላይ ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ በዝርዝር ካስቀመጥኩኝ ለዉጥ ከልባችን የምንፈልግ ከሆነ መፍትሄዉምንድን ነዉ ወደሚለዉ ሁላችንም ወደ ምንጠይቀዉ ጥያቄ እመጣለሁኝ።
1. ለዉጥ ከልባችን እንፈልጋለን ወይ? ? ? የሚለዉ ጥያቄ በእያንዳንዳችን እዉነትኛ ህሊና መልስ ማግኘት አለበት?በእዉነት ለዉጥ እንፈልጋለን ወይ? ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም እንደሚባለዉ – ለዉጥን ከልቡ በጽናትየሚፈልግ ፍላጎቱን ለሟሟላት የማይፈነቅለዉ ድንጋይ ስለማይኖር ዉጤት ማግኘቱ አይቀሬ ነዉ
2. የትግሉን ክብደትና ጥልቀት ማወቅ ይጠበቅብናል በዚያዉም ልክ የአቅማችንን መጠን ማወቅ አለብን – ንቀታችንናጥላቻችን የትም አላደረሰንም
3. ዉጤት የምንፈልግና አቅማችንን የምናዉቅ ከሆነ ከሆነ ለዉጤቱ የሚፈለግብንን ሁሉ ሳናመነታ ኢንቨስትማድረግ አለብን፤ ጊዜ፤ገንዘብ፤ጉልበት፤እዉቀት፤ሞራል ወዘተ – ነጻነት በምጽዋት አይመጣም – መሄድየሚገባንን መንገድ ሁሉ መሄድ ይጠበቅብናል
4. ትግሉ የማንም እንዳልሆነ መገንዘብ ይጠበቅብናል (የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ነዉ – ምክንያት ድርደራ የትምአላደረሰንም – ስለትግሉ አዲሱ ፈሊጥ
· እኔ ፖለቲካ ዉስጥ የለሁበትም – ጀግንነት ሆኗል
· የምናምናቸዉ ሰዎች የሉም – እገሌ ማነዉ እሱ
· ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች አይረቡም
· ዉጭ ያለዉ ሐይል ምንም አያደርግም
· ሀገር ቤት ያለዉ ካልተነሳ የትም አንደርስም
ሁሉም ጣቱን ሲጠቋቆም – ትግሉ ግን እያንዳንዳችን ትከሻ ልይ መሆኑን ዘንግተናል። ስለዚህ
· መሪዎቹንና ድርጅቶቹን ካላመናችሁ ግቡና አስተካክሉ
· ወይንም የራሳችሁን ጠንካራ የተሻለ መንገድ አምጡ – ብቻ በዚህም በዚያም ትግሉን ተቀላቀሉ –አማራጩ ሽንፈትን በጸጋ ተቀብለን – አቅማችንን አዉቀን እየታገሉ ያሉትን ትተን አርፈን መቀመጥይኖርብናል – እባካችሁ ባንደግፋቸዉ አናዳክማቸዉ
1. የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ሁኔታ የዶሮና የእንቁላል ሆኗል። ህዝቡ ፖለቲካ ድርጅቶች ካልተጠናከሩ ዉጤትካላሳዩን አንደግፍም ብሎ አኩርፎ ተቀምጧል – እነሱ ደሞ ሊጠናከሩ የሚችሉት ህዝቡ ሲደግፋቸዉ ነዉ። ግራየሚያጋባ ሁኔታ። ይህ ካልተቀየረና ህዝቡ በተሳትፎ ካላጠናከራቸዉ የትም አይደረስም።
2. ሌላዉ ሁሉም ፖለቲካ ድርጅቶች አንድ ይሁኑ የሚለዉ ለሀያ አመት የተሞከረዉ ፈሊጥ መቼም አይሰራም –አግባብነት የለዉም – ልዩነት የጥንካሬ መሰረት ነዉ – ዋናዉ ቁም ነገር እርስ በእርስ በመጨራረስ የስርአቱንእድሜ አለማራዘም ነዉ። ስርአቱ እጁን አጣምሮ ደስ ሲለዉም የቤት ስራ እየሰጠን የእርስ በእርስ ሽኩቻድራማችንን እያየ ይገናል – መፍትሄዉ ቢቻል ተባብረን ካልተቻለም እርስ በእርስ ሽኩቻችንን አቁመን፤ የተሻሉናቸዉ የምንላቸዉን በሙሉ ሀይላችን መደገፍ የትግል አቅማቸዉን ማሳደግ ይኖርብናል – በዚያዉም ልክማናቸዉንም ተቃዋሚ ሀይሎችን የሚቃወምን ሁሉ ባለ በሌለ ሃይላችን በጋራ ማዉገዝና መዋጋት ይኖርብናል
3. ትግሉ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን መረዳት በሂደትም መዉደቅና መነሳት መኖሩን መገንዘብ የኖርብናል፤ (ቅንጅትቅንጅት እያልን መቀመጡ የት አደረሰን)? አየር ባየር ዉጤት ፈላጊነት የትም አላደረሰንም፤ ዋናዉ ቁምነገርየፈጀዉን ጊዜ ይፍጅ ካላማችን ንቅንቅ ማለት የለብንም – የኩርፍያ ትግል የትም አላደረሰንም – ያላማ ጽናትከሌለን አርፈን እንቀመጥ
በዚህ ጉዳይ ብዙ መናገር ለማጠቃለል ያክል ወደድንም ጠላንም
ዉጤት ያለ አዉነተኛ ፍላጎት
ዉጤት ያለ አቅም
ዉጤት ያለ መስእዋትነት
ዉጤት ያለ ጊዜ
በፍጹም አይገኝም፤
ዉጤት ያለ አቅም
ዉጤት ያለ መስእዋትነት
ዉጤት ያለ ጊዜ
በፍጹም አይገኝም፤
ፍላጎት አቅምና መስእዋትነት ሳይከፍሉ ዉጤትን መጠበቅ የዋህነት ነዉ። ይህንንም የያዝነዉን ፈሊጥና ባህልእስካልቀየርን ድረስ ስርአቱም በአሸናፊነቱ መቀጠሉ አይቀሬ ነዉ።
የብዙዎቻችን ችግር የትግሉ ድል መፍትሄ በእጃችን ላይ መሆኑን መቀበል አለመፈለጋችን ወይምአለማወቃችን ነዉ። የወደቅነዉ መፍትሄ ከሌላ ቦታ መፈለጋችን ነዉ። ይህ እስካልተወጠ ድረስ ስርአቱለዘመናት መግዛቱን እንደማያቆም በእርግጠንነት ላረጋግጥላችሁ።
ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልግ ዛሬ ነገ እያለ በቀጠሮ ሳይሆን ከልቡ ለዉጥን የሚፈልግ ከሆነ ዛሬ ካሁኗ ደቂቃጀምሮ ለራሱ ለህሊናዉ ለሀገሩ ለወገኑ ቃል መግባት ይኖርበታል።
ስለሌላዉ ማሰባችንን ትተን ስለራሳችን እናስብ። በድርጅቶች ችግር አለ ብለን ካሰብን ገብተን እናሻሽላቸዉ፤አሊያም የኛ አማራጭ የተሻለ ነዉ የምንል ከሆነ የተሻለ ድርጅት መስርተን ትግሉን እንቀላቀል። በዚህምበዚያም ገብተን እንታገል። የትም እንፍጨዉ ዉጤቱን እናምጣዉ።
እኔ ይህንን ስናገር የሽግግር ም/ቤቱ ግቡ ብዬ አይደለም፡ ለእናንተ ትግል ዉስጥ መግባት የድርጅቶች ጥንካሬቅድመ ሁኔታ አይደለም ወሳኙ። የራሳችሁ የህሊና ዉሳኔ ነዉ። ያንን የዉሳኔ ደረጃ ካለፋችሁና ለራሳችሁ ቃልከገባችሁና ያለማወላወል ወደተግባር ከለወጣችሁ ሌላዉ ሁሉ ይስተካከላል። የተገላቢጦሹን ከፈለጋችሁ ግንምን አለ በሉኝ ምንም ለዉጥ እንደማይመጣ በድጋሚ አረጋግጣለሁ።
ስለዚህ ብቸኛዉ ያለን የአካሄድ ቀመር በግልጽ እንዲህ ነዉ
1. እያንዳንድችን ዛሬ ትግሉን በቆራጥነት መቀላቀልና ሚከፈለዉን መስዋትነት ሁሉ መክፈል፤ በተጨማሪም ትግሉ የወሰደዉን ጊዜም ቢወስድ በቁርጠኝነት ለመታገል መዘጋጀት
2. በግል የትም ለመድረስ ስለማይቻል ያሉትን ድርጅቶች መርምሮ የተሻለ ነዉ የምንለዉን ዛሬዉኑ ተቀላቅሎበሙሉ ሀይል መግባትና መታገል
ስለዚህ እመኑኝ የድሉ ቁልፍ እያንዳንዳችሁ ናችሁ። ሌላ ምንም አማራጭ የላችሁም።
ይህንን ለማድረግ ከፈቀድንና ለራሳችን በእዉነተኝነት ቃል ከገባን ምንገነባዉ አቅም የምንመኘዉን ዉጤትይዞልን ይመጣል። ስለዚህ
የፍላጎት አቅም
የዉሳኔ አቅም
የሞራል አቅም
የአላማ ጽናት አቅም
የማቴርያል አቅም
የድርጅት አቅም
የዉሳኔ አቅም
የሞራል አቅም
የአላማ ጽናት አቅም
የማቴርያል አቅም
የድርጅት አቅም
ለድላችን ወሳኝ መሆኑን ተረድተን ዛሬ ነግ ሳንል ትግሉን እንቀላቀል። በኛ በኩል እዉነቱን መራራም ቢሆንተናግረናል፤ ለህሊናችን የሚቆጨን ነገር የለም፡ የህሊና ትግሉን ለናነት ትተናል።
እኛ በራሳችን በኩል የተሻለ ነዉ ያልነዉን አማራጭ አቅርበን ትግላችንን ተያይዘነዋል። በማናቸዉም መንገድለማንም ሳንል፤ ለእዉነት ብቻ ብለን፤ ለክብራችን ብለን፤ ለነጻነታችን ብለን፡ ትግሉ ጊዜ እንደማይሰጥተረድተን ቀጠሮ ሳንሰጥ የድሉን ጽዋ እስክንጎነጭ፤ ማንም ምንም የበል ምን፤ በቁርጠኝነት እየታገልንእንገኛለን።
ልዩነቱ የህሊና እርካታ፤ የመንፈስ የማንነት ጽናትን ሰጥቶናል። ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነዉ ችግርናመከራን ለመጋፈጥ ትግሉን በቆራጥነትና በኩራት እያከናወንን እንገኛለን። በስራችንም ኩሩ ኢትዮጵያዉያንእንደምንሆን አንጠራጠርም፤ ለእዉነት በመቆማችንና አምላክም ከቅኖች ጋር በመሆኑ አሸናፊዎችእንደምንሆን ሙሉ እምነት አለን። ከዚህ በላይ ታዲያ ምን የሚያስቀና ነገር ይኖራል።
ሀገራችን ክብራችን፤ የማንነታችን መለያ፤ የነጻነታችን ምልክት ናት። ማንም ይህንን ሊነጥቀን አይገባዉም፤በትግላችንም የተነጠቅነዉን ማንነታችንን ያለጥርጥር እናስመልሳለን!!!
ድርጅታችንን በተመለከተ ግን አቋማችን ንጥር ያለና ግልጽ ነዉ
1. የማንም ኢትዮጵያዊ ክብርና፤ ነጻነት፤ በማናቸዉም ሁኔታ ሳይሸራረፍ መረጋገጥ ይኖርበታል እንላለን።አምላካችን የሰጠንን መብት ለማንም አሳልፈን አንሰጥም። ስርአቱ የሚሰራዉን ግፍ ያለምንም ቅድመ ሁኔታእስካላቆመ ድረስ በፍጹም አለማመንታት መቀየር አለበት በሚለዉ አቋማችን ጸንተን ትግላችንን እንቀጥላለን –ይህም ስርአት ሁሉን ኢትዮጵያዊ አካላትን ባካተተ የሽግግር መንግስት እስኪተካ ትግላችንን በጽናት እንቀጥላለን
2. ህዝባዊ የለዉጥ እንቅስቃሴ በመፍጠር ስርአቱን በህዝባዊ ትግል ለመገርሰስና ትግሉን በድል ለማጠናቀቅ ህዝቡትግሉን እንዲቀላቀል ትግላችንን ሌት ተቀን እንቀጥላለን
3. ስርአቱም ሲገረሰስ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ ቀድሞ መሰናዳት የተሻለና ብልህነትን የተላበሰ ማራጭመሆኑን ስለምናምን የሽግግር ሂደቱ ምን መምሰል እንደሚኖርበት ቅድመ ዝግጅቶችን እንደርጋለን
4. ይንንኑም ለማከናወን የሚያስችል ድርጅታዊ አቅም እንገነባለን በዚህም አካሄድ ያለማወላወል እንቀጥላለን።
5. ከሌሎች ሁሉም አሁንም እደግመዋለሁ ከሁሉም የተቃዋሚ ሀይሎች ጋር በጋራ እንሰራለን፤ ተቃዋሚ ሀይሎችምበጋራ እንዲሰሩ ማናቸዉንም ሁኔታዎች እናመቻቻለን
ስለዚህ የድርጅታች የነጠረና ግልጽ ያለ አማራጭን ያቀረበ ሲሆን፡ ይሻላል ብላችሁ ካመናችሁ ተቀላቀሉን።አለበለዚያ ሌላ የተሻለዉን ድርጅት ዛሬዉኑ ተቀላቀሉ። አንድ ነገር ላረጋግጥላችሁ ትግሉ ይቀጥላል።ተጠናክሮ ይቀጥላል። ባቡሩን በጊዜ ተቀላቅሎ የለዉጡን ሂደት ማፋጠኑ የናንተ ሀላፊነት ነዉ። በታሪክተጠያቂነት ምርጫዉን ለናንተ እተዋለሁ። የሚሻለዉን የጽናት መንገድም አምላክ ያሳያችሁ ዘንድ ሁሌምእጸልያለሁ።
ሀገራችንን ኢትዮጵያን አምላክ ይባርክ!!!
ፍስሀ እሸቱ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
No comments:
Post a Comment