ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም ብለን ዝም ስንል ዝም ባልንበት አፍ ወንጀለኛ ተባልን።
ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም ብለን ዝም ስንል ዝም ባልንበት አፍ ወንጀለኛ ተባልን።
“አማራ መሆን ወንጀል ነው? የሌሎች ብሔረሰብ አባላት በፈለጉበትክልልና ስፍራ ይኖራሉ። አማራ ክልል ውስጥ ሰፊ መሬት ወስደው የሚኖሩአሉ፤ የሚነካቸው የለም። አማራው እየተመረጠ ለስደት፣ ለመከራ፣ለእንግልት ይዳረጋል? እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል? የአማራ ክልሉንእንመራለን፣ የአማራ ህዝብ ወኪል ነን የሚሉ የት ናቸው? ያሳዝናል! ግንወኪሉም ተብዬው ለካ የወያኔ ስራ አስፈፃሚሆች ናቸው ለካ ምን ይደረግ፣ለአማራው አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አማራው አለቀ፣ልጆቻችንየሚቀበለን በጉዲፈቻ እያሉ …” ሲሉ በስልክ ለተለያዩ ሬዲዮ ጣቢያ በስልክ ሲቃ ልሳናቸውን አንቆ አስተያየታቸውን የሰጡ የአማራ ተወላጆች ሲናገሩ አልሰማንም የሚል የለም ካንም እኔ አይመለከተኝም ሊሆን ይችላል ግን ነገ ደግሞ በሌላው ብሔረሰብ መደገሙ የማይቀር ነውና ዛሬ ይኽንየወያኔን ስራ መቃወም አለብን ።
ሰሞኑን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል አማራውን የማፅዳት ዘመቻ ወይምየማፈናቀል ዘመቻ መጀመሩ ይፋ ሆነ እንጂ ችግሩ የቆየና ማዕከላዊአገዛዙም ሆነ የክልሉ መስተዳድር ጠንቅቀው የሚያውቁት ጉዳይእንደሆነም ይታወቃል። የካቲት 28፤2005 የተላለፈው የኢሳት አማርኛክፍል ያነጋገራቸው የችግሩ ሰለባ አሁን ያለውን ችግር የሚገልጹትበተማጽኖ ነበር።
ከዚህ በፊትም ከዓመታት በፊት መተከል ዞን ፓዌ የተካሄደውን ማስታወስይቻላል። 1984 – 85 ፓዌ መንደር አራት በሚባለው የገበያ ቦታእየገበዩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ያላሰቡት ደረሰባቸው።በድንገት ገበያውታወከ። የቻሉትን በቀስት፣ ሌላውን በጥይት ለቀሙት። 56 ሰዎችበቅጽበት ሲረሸኑ። ይህ ሁሉ ሲደረግ አገር የሚመሩት ባለስልጣኖችድምጻቸውን አላሰሙም ነበር ሆን ብለው ያደረጉት ስለነበረ።
በጉራፈርዳ በክልሉ መንግስት ትዕዛዝ የከፋ ወንጀል ሲሰራ፣ አንደኛ ክፍልለሚማር ህጻን ጭምር “ክልሉን ልቀቅና ውጣ” የሚል ደብዳቤ ሲሰጥተቆጣጣሪና ተቆርቋሪ አለመኖሩ መጨረሻ የሌለው ግፍ አማራው ላይእንዲካሄድ ስምምነት ያለ የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም።
በቤንሻንጉል መተከል ዞን ቡሎን ወረዳ የሰፈሩና ከ20 ዓመት በላይ ይኖሩየነበሩ ሰዎች በረሃውን አልምተው፣ ወልደው ከብደውና ንብረት አፍርተውይኖሩ የነበሩ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከየካቲት19 እስከ 30 ቀን2013 ዓም መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዝዘዋል የሚገርመው ግንከ 20 ሺ በላይ የአማራ ተወላጆች የሚኖሩ ሲሆን ቀስ በቀስ የማጣራትዘመቻም እንደሚደረግ ይታወቃል።
የአማራ ተወላጆቹ “ሰሚ አጣን” ድምጻችንን የሚሰማን አጣን በአገራችን“ለክልሉ መንግስት ሲናገሩ፣ ሲያመለክቱ አመለከታችሁ በሚልስለምንታሰር፣ስለምንደበደብ እባካችሁ ለፌደራሉ መንግስት አሳውቁልን”ሲሉ በተለያዩ መገናኛ ተደምጠዋል። አገር ቤት የመንግስትም ሆነ “የግል”የሚባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ጆሮ የነሷቸው ይመስል ሰምተው ዝምብለዋል። ጥያቄ ያቀረቡት ሰዎች “ፈልሶ የመጣ፣መጤ፣ውጣ አማራ”እየተባሉ የውጭ አገር ዜጋ እንኳን በማይጠራበት ሁኔታ ክብረ ነክ ስድብእንደሚሰደቡ ተናግረውም ነበር ተበዳዮቹ። የሚያሳዝነው ባፋጣኝ ክልሉንለቀው ካልወጡ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ምን ሊከሰት እንደሚችልየዛቱባቸውን ሰዎች በሚዲያም ተናግረውም ጭምር ነበር።‹‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡›› የሚሉት እነዚህ ዜጎች “በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ ከኖርንበት መሬት ተፈናቅለናል፡፡ ከአውሬ ጋር እየታገልን ያለማነውን መሬት ተነጥቀናል፡፡ እነሱ የሚሉን እናንተ አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል መኖር አትችሉም፡፡ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ይሉናል፡፡ አማራ ክልልን እንኳን ሰርተን የምንበላበት መሬት ቀርቶ ጎጆ ቀልሰን የምንኖርበት ቦታ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡” ባስቸኳይክልሉን ለቀው ካልወጡ “የፌደራል ፖሊስ ደብድቦ ያስወጣሃል” የሚልማስፈራሪያ የደረሳቸው ሰዎች ጭምር ነበሩ።
የአማራ ክልል ለምና ሰፊ መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት፣ ሁመራንናወልቃይት ገባውን ለትግራይ ክልል አሳልፎ በማስረከብ የሚታወቀውንብአዴን ዛሬ ዝም ቢል አይገርምም እኮ ከዝንብ ማር ይጠበቃል እንዲ? አቶደመቀ መኮንን በአማራው ወያኔ ስም “ቅምጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር”ሆነው በውለታ መሾማቸው የሚታወስ ነው።
ግን ይዄ ሁላ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ማለቱ ነገ ዋጋ እንደሚያስከፍለውስ ሳያቀው ቀርቶ ነው።መቼም የአማራ ክልል ብአዴን ለምን ዝም አለ አንልም ምክንያቱም የወያኔ ጀሌ፣ሎሌ ሆኖ እያገለገለ ያለ እንጂ ለህዝቡ እያገለገለ እንዳልሆነ ይታወቃል።
ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም ከሆነ ታዲያ ዝም ብንልም ወንጀለኞች ሆነናን። ዝምታው ይሰበር በአንድነት የጉዳዩ ተጠቂ ነን እንበል! ኢትዮጵያ የሁላችንም ነች! ኢትዮጵያ የዚህ የዚያ ብሄር አይደለችም የሁላችንም ነች። ከጠባብ የብሄር ጎጠኞች ኢትዮጵያን እንታደጋት!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
No comments:
Post a Comment